ያለና የሚኖር (1…)

‘’እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።’’ (ዘጸ.3:14) ያለና የሚኖር አምላክ የተባለው በራሱ የሚኖር፣ በሌላ የሚያኖር ሃይል የማይኖር፣ ለመኖር ጅማሬ የሌለው፣ ህያውነቱን የሚለካ የሌለ፣ ለህልውናው ድጋፍም መስፈርትም መመኪያም የሌለው፣ ለሌሎች መኖር መሰረት የሆነ፣ ፍጥረታት በርሱ በመፈጠራቸው ጅማሬያቸው ከርሱ የሆነ መሆኑን ያመለክታል። ይህን ታላቅ መልእክት እስራኤላውያን …
Continue reading ያለና የሚኖር (1…)

እምነት፣ተስፋና ድርጊት(3…)

ስለ እግዚአብሄር ቃል ምንነት ባለን እውቀት በኩል የተቀበልነው ትልቅ ስጦታ ቢኖር ተስፋው ነው፤ በተስፋው በኩል እግዚአብሄር በዚህ ጊዜና በዚህ ስፍራ ይህን አደርጋለሁ ብሎ ለሰዎች ቃል ይገባል። ቃሉ በዘመን ብዛት አይለወጥ፣ አያረጅ፣ አይቀየር፣አይታጠፍ ወይም አይጠፋም። ስለዚህ ይህ የእግዚአብሄር ተስፋ ጸንቶ እንደተነገረበት አውድ ትውልዶችን አልፎና አሳልፎ እስኪከናወን ያለመለወጥ ሲጸና ይታያል። አንዳንድ የእግዚብሄር ባሪያዎች የተቀበሉት የተስፋ ቃል ከነርሱ …
Continue reading እምነት፣ተስፋና ድርጊት(3…)

ህግ ሊያጸድቅ ያለመቻሉ

የህጉ ሰውን በእግዚአብሄር ፊት ለማቆም ያለመቻል ድካም ምንን ያሳየናል? – እግዚአብሄር ከህጉ የተሻለ መንገድ እንደሚከፍት ያሳያል – ህጉ ከሰው የሚጠብቀው ድርጊት፣ እንቅስቃሴና ውሳኔ እንደተጠበቀው እንዳልተሟላ ያሳያል – የሰው ልጅ ችሎታ ጎዶሎ፣ ደካማና ጽድቅን የማይሰራ መሆኑን ያሳያል – የሰው ልጅ በህግ እንደማይጸድቅ ያሳያል – እግዚአብሄር በህግ ፋንታ ጸጋን እንደሰጠ ያሳያል – ህግና ጸጋ ሁለቱም መንፈሳዊ ሲሆኑ …
Continue reading ህግ ሊያጸድቅ ያለመቻሉ

የመጨረሻው ዘመን (1…)

የመጨረሻው ዘመን የሚመጣበት ጊዜ በተለይ ለጌታ ደቀ መዛሙርት ዋና ጥያቄ ነው፦ ‘’እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፡- ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።’’ (ማቴ.24:3) ጌታም ለጥያቄያቸው ግልጽ መልስ ሰጥቶአል፤ በቃሉ እንደተመለከተው ከርሱ በስጋ በምድር መመላለስ ወቅት አንስቶ መጨረሻው እስከሚሆን ድረስ የሚገለጡትን ታላላቅ ነገሮች በምልክትነት ተቀምጠዋል፤ …
Continue reading የመጨረሻው ዘመን (1…)