ዲያቢሎስን መቃወም

ክርስቲያኖች ጠላትን ስንቃወም በቃልም በስራም እንቃወመዋለን።የመቃወሚያ መሳሪያችን ደግሞ በመንፈስ የምንጠራው የኢየሱስ ስም ነው። ጠላትን ለመቃወም ስንነሳ ለምን እርሱን እንደምንቃወመውና ተቃውሞአችን ምን እንደሚሰራ/ውጤቱ ምን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።በቅድሚያ ለመቃወም ምክኒያታችን ዲያቢሎስ የሚያቅዳቸውና የሚሰራቸው የክፋት ስራዎቹ ናቸው። በተጨማሪ በክፉ ባህሪው ምክኒያትም እንቃወመዋለን። የህይወታችን ጥፋት መሰረቱ እሱ ነው፣የምንኖርበትን ማህበረሰብና የኑሮ ሲስተምም የተቆጣጠረው እሱ ነው። ለመቃወም መቃወሚያ መንገዱን መረዳት ይጠይቃል። …
Continue reading ዲያቢሎስን መቃወም

የቸርነቱን ደውል አስተውል

የእግዚአብሄርን ባህሪ የሚገልጥ አዋጅ እንዲህ ይላል፡- ዘጸ.34:6-8 ”… እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጐነበሰና ሰገደ።” የእግዚአብሄርን ምህረትና ቸርነት የሚያውቁ ቅዱሳን …
Continue reading የቸርነቱን ደውል አስተውል

የታላቁ ጠላት ጥቂቱ

ብዙ ጊዜ ጥቂት ያልነው አነስተኛ ወይም አይን የማይገባና ጉልበቱን ቸል ያልነው ኢምንት ነገር ብዙሀኑን ሰርስሮ በመግባት በክሎና ተሰራጭቶ በራሱ ባህሪ ሲውጠው እናያለን፡፡የእግዚአብሄር ቃል ጥቂት እርሾ ሙሉውን ሊጥ እንደሚያቦካ ያስረዳል፡፡ጥቂት እርሾ ውስጥ ያለ ኮምጣጣ ነገር የመሰራጨት ጉልበቱ ከፍተኛ በመሆኑ ንጹሁንና ትኩሱን (ያልከረመውን) ሊጥ በፍጥነት ያቦካዋል/ያኮመጥጠዋል፡፡ነገሩ በእኛም ህይወት ውስጥ ሲመጣ እንዲሁ ነው፡፡እንደ እርሾው የኮመጠጠና የማይመች ነገር ከእኛ …
Continue reading የታላቁ ጠላት ጥቂቱ

በእምነት መመላለስ

በእስራኤል ነገድ ውስጥ የእግዚአብሄርን ህግ ሊጠብቅ የቻለ ሰው አልነበረምና እግዚአብሄር በዚያ ባለመደሰቱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ “የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፥ በሕጉም ለመመላለስ እንቢ አሉ“ (መዝ.78:10) ያኔ የእግዚአብሄር የግርዘት ቃል ኪዳን በእስራኤል የምድረበዳ ጉዞ ወቅት ተዘንግቶ ነበር።በሌላ መልኩ እስራኤላውያን ከነአን ከገቡ በሁዋላም በሲና ተራራ ፊት ሆነው የተቀበሉትን ህግ እንዲሁ አልጠበቁም።ዛሬም ቢሆን እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ነው፡፡ እኛስ ራሳችን …
Continue reading በእምነት መመላለስ