የፍቅር ክልል በስፋት፣ በርዝመትና በጥልቀት የማይለካ ግን ልብን አእምሮንና ነፍስን የሚቆጣጠር ብርቱ ሀይል፣ ሰውንም ያለጉልበት መግዛት የሚችል ታላቅ መለኮታዊ ስጦታ ነው፡፡ ክፉ የተባለውን የሰው ልብ ሌላ ምን አይነት ጉልበት ሊያቆመው ችሎአል? እርሱን ለመለወጥ የሚችል ፈቃድስ ምን ነበር? እግዚአብሄር ለብዙ ዘመናት ቃሉን፣ ህጉን፣ ስርአቱንና መንገዱን ቢሰጥም የሰው ልብ እሺ ብሎ የተገዛው መቼ ነበር? እግዚአብሄር ግን ያን …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [5..]
Month:August 2021
እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
የጌታ ደቀመዛሙርት ቅድሚያ ሊሰጡዋቸው ከሚገቡ ነገሮች ፊት የሚገኘው (አውራና መሰረት የሆነው) የመንፈሳዊ ህይወት ጤንነት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወት እንደ ስጋ ያለ ቁመና፣ ፍላጎት ወይም ስሜት ስለማይኖረው የጤንነቱ መለኪያ በስጋ ከሚደረገው ጋር አይመሳሰልምና የተለየ መፍትሄ የሚሻ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወታችንን የሚመረምርና የሚያክም የእግዚአብሄር መሳሪያ የሆነው ህያው ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ ስለሚሰራው ስራ መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ”የእግዚአብሔር …
Continue reading እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
ፊትህን አሳየን{3..}
ከፊቴ ያለ ጠላት ከፊት የሚወጣ ጠላት እስካልተቐቐምኩት ድረስ ከእርምጃዬ የሚፈጥን፣ ከጅማሬዬ ቀድሞ ያሻውን የሚፈጽም፣ ከጉዞዬ ፊትም ወጥቶ መሰናክል የሚሆን ነው፣ በእቅዴና በስራዬ እንዳይቀድመኝና እንዳያሰናክለኝ ምኞቴ ቢሆንም እኔ ያን ማሳካት እንደምችል በራሴ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ የሚያደባ ጠላት መንገዴ ላይ የሚያተኩረው ከእውነት ሊያስተኝ እግሬንም ሊያሰናክለው ካልሆነ ለሌላ ለምንም አይሆንም፡፡ በዚያ ተልእኮው ስንቴ ወጥመድ አጠመደብኝ? ስንቴ ማሰናከያ ድንጋይ አኖረብኝ? …
Continue reading ፊትህን አሳየን{3..}
ሰላም ለናንተ ይሁን[3ኛ…]
ምክረ ሰላም ”እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።”(1ቆሮ.14:33) ግን አንዳንዴ ሁከት ሲያስጨንቀን፣ ሰላም አጥተን ስንባዝንና እፎይ ያልንበት ጊዜ እስካይታወሰን በፈተና ስንቅበዘበዝ ወደ እኛ ተመልሶ የመምጣቱ ነገር ያጠራጥረናል፤ በእውነተኛ ትርጉሙም ላይ ጥያቄ በማንሳት ሰላምን እንነቅፋለን፤ እርሱ ማን ነው? እስከማለት እንደርሳለን፡፡ በእርግጥስ ሰላም ለእኛ ምንድነው? አንጻራዊውን ሰላም ለማለት አይደለም፤ …
Continue reading ሰላም ለናንተ ይሁን[3ኛ…]
