ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

ሐ.የጌታን ምርጫ በተመለከተ፡-እነርሱን ብቻ እንድንሰማ ጌታ እንዳዘዘ ማስተዋል ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጅ በሙሉ ለእነርሱ የወንጌል ስብከት ክብር እንዲሰጥ አጥብቆ ወደ እኛ ትእዛዝ ስድዶአል፡፡ ሉቃ10:16 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።”ሲል ተናግሮአል፡፡ ይህን ጥቅስ ካስተዋልን ጌታ ኢየሱስ እኔን የሚሰማ እናንተን ይሰማል አላለም፣ለምን? የጌታ ፍቃዱ በመረጣቸው ሀዋርያት አድሮ መስራት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

የህግ ሁነኛ ችሎታና በህግ የተሰጡ እድሎች

ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት፣ ሕግ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለንና፤ በሮሜ.7:9-14 ላይ እንደተገለጸው፦ ‘’እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤ ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤ ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል። ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት። እንግዲህ …
Continue reading የህግ ሁነኛ ችሎታና በህግ የተሰጡ እድሎች

የዮሴፍ በረከት ያግኝህ (1…)

የእግዚአብሄርን ቃል የሚያውቅ ሁሉ የዮሴፍን በረከት በደስታም በጥንቃቄም ያስተውላል፤ በእርግጥ እግዚአብሄር የረዳው፣ በባእዳን ምድር ከፍ ከፍ ያደረገው፣ በባለጠግነትና በማረግ ያገነነውም እንደርሱ ያለ ሰው የለምና። ዮሴፍ እዚህ ከፍታ እስኪደርስ ግን ምን ገጠመው፣ እንዴት ባለስ ሁኔታ ውስጥ አለፈ? ብሎ የሚጠይቅ ከዚህ ትሁት ሰው ህይወት የሚቀበለው ማስተዋል አስተሳሰቡንና እምነቱን ደግሞ ደጋግሞ እንዲቃኝ ያደርገዋል። በእርግጥ እንደ ዮሴፍ ያለ በረከት …
Continue reading የዮሴፍ በረከት ያግኝህ (1…)

ተግዳሮት ተሸንፎአል(2..)

ተግዳሮት ተሸንፎአል የሚለውን ትልቅ ርእስ ከማየት በፊት ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች ለምሳሌ ተግዳሮት ምንድነው? ተግዳሮትስ ከማንና ለማን(ማን ላይ) የሚሆን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በአጭር ትርጉዋሜ ለማየት መሞከር ተገቢ ነው። ተግዳሮት በህይወት መንገድ ላይ የምናገኘው ፈታኝና አሰናካይ ነገር ሁሉ ነው፤ እርሱ፦ የሚገዳደር ነገር፣ የሚከለክል ነገር፣ ወደ ሁዋላ የሚስብ ነገር፣ የሚያደናቅፍ ነገር፣ የሚይዝ ነገር፣ የሚያፍን ነገር፣ ከመንገድ የሚያስቀር ነገር፣ …
Continue reading ተግዳሮት ተሸንፎአል(2..)

በሚሠራበት ቀን (2…)

እግዚአብሄር በምህረት በሚጎበኝበት ቀን (ዘመን) ትውልድ ተዘጋጅቶ ይጠብቅ ዘንድ ይፈለጋል፤ እግዚአብሄር መቼ ይሰራል? ለማን ይሰራል? እንዴት ይሰራል? የሚል ማስተዋል ያለበት ምርመራ ይገባልም። በእስራኤላውያን ዘንድ ዘመንን ማወቅ ትልቅ ስፍራ ስላለው ጠቢባን ያማክሩ ነበር፤ በንጉስ ዳዊት ዘመን ጊዜን የሚመረምሩና የሚያስተውሉ ከህዝቡ መሃል የተመረጡ ሰዎች ስለነበሩት የእግዚአብሄር ህዝብ ዘመኑንና በዘመኑ ላይ የሚገለጠውን የእግዚአብሄር ፈቃድ በመረዳት የህይወት ይዘታቸውን ያስተካክሉ/ይቃኙ …
Continue reading በሚሠራበት ቀን (2…)

መጨረሻው ዘመን (3…)

ያለነው በመጨረሻው ዘመን ላይ ሲሆን በምንኖርበት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚያሳስብ፣ የሚያስጨንቅ ደግሞ የሚያጸልይና ነቅተን እንዳይወርሰን ልንጠባበቀው የሚገባ በዚህ ጊዜም አለምን ተቆጣጥሮ ያለ የሚያስፈራ የአመጽ ብዛት አለ፦ በዚህ ዘመን በአይናችን እየሆኑ ከምናያቸው ጌታ ከሰጣቸው የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች መሃል የአመጽ መብዛት አንዱ አስፈሪ ድርጊት ነው። እግዚአብሄር ግን ለሰው ልጆች አስቀድሞ ያስቀመጠውን ትእዛዝ አልረሳም፦ ዘዳ.30:13-16 ’’ሰምተን እናደርጋት ዘንድ …
Continue reading መጨረሻው ዘመን (3…)

ለችግረኛው የቆመ(2…)

ችግር በብዙ መልክ ይገለጣል፤ ቢሆንም እጥረት፣ ማጣት፣ አለመሳካት፣ እንቅፋት፣ እክል፣ ድካም፣ አደጋ፣ ህመም የመሳሰሉት በአብዛኛው በስጋችን ላይ የሚሆኑ ችግሮቻችን ናቸው። ችግር ግን በስጋ ላይ ብቻ አይቆምም፣ ይልቁንም በመንፈሳዊ የህይወት አቋም ውስጥ ከፍ ባለ ሁኔታ ይገለጣል እንጂ። መንፈሳዊ ችግር በስጋ ላይ ሊንጸባረቅ የማይችል ከሆነ በለመድነው መንገድ ‘’ይህ በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ የሆነብን ነው’’ ብለን አስረግጠንና አምነን እንደ …
Continue reading ለችግረኛው የቆመ(2…)

ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ(1…)

የእግዚአብሄር ቃል በዮሃንስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ ለሰው ልጆች በሚገልጠው የምስራች ላይ እንዲህ ብሎአል፦ ‘’… ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።’’ (ዮሐ.1:9-11) ከአዳም የተገኘ ትውልድ ሁሉ በአንድ ስም ሰው ተብሎ ከርሱም ለእያንዳንዱ ትውልድ እውነትን ያሳውቅ ዘንድ እግዚአብሄር በተለያየ መንገድ …
Continue reading ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ(1…)

በሚሠራበት ቀን (1…)

እግዚአብሄር ወደ ሰው ልጆች ሲመለከት አብረሃምን አየና ከቤተሰቡ መሃል ለይቶ ጠራው፣ ለምን? እግዚአብሄር የአብረሃምን ማንነት ስላወቀ፣ መጀመሪያ ላይ መጨረሻውን ስላየ፣ የአህዛብ ወራሽ መሆን እንደሚችል መንፈሱን ስለመዘነና የእርሱን መለኮታዊ አሳብ መጠበቅና መፈጸም የሚችል ሰው እርሱ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ እንዲሁም የሰው ልጆች የእምነት አባት መሆን የሚችል እርሱ መሆኑን ስለወሰነ ነው። ያኔ በጥንት ዘመን በእግዚአብሄር ጊዜ ውስጥ የእግዚአብሄርን አላማ …
Continue reading በሚሠራበት ቀን (1…)

የወንጌሉ መሰረት (2…)

በኤፌ2:20፣3፡16 ላይ ቃሉ ሲናገር፦ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ …በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥… ይላል፡፡ ሀዋርያትና ነብያት መሰረት የሆኑት እውነተኛ የወንጌል አገልጋይ በመሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ኢየሱስ ክርስቶስ በእነርሱ አድሮ ለሚሰራው ስራ …
Continue reading የወንጌሉ መሰረት (2…)

ያለና የሚኖር (3…)

እግዚአብሄርን የተጠጉ ስለርሱ እንዲህ ይላሉ፡- ‘’እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? መንገዱን ማን አዘዘለት? ወይስ፦ ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው? ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ። ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ ሰውም ከሩቅ ያየዋል። እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።’’ (ኢዮ.36:22) እርግጥ ነው፣ ያለና የሚኖረው ህያው አምላክ …
Continue reading ያለና የሚኖር (3…)