አለማዊነት(2..)

በዳኑ ሰዎች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በብዙ አቅጣጫ የሚታዩ ሲሆን ተግዳሮቶቹም በዋናነት ለመንፈሳዊ ህይወት ችግሮች ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ነፍሳት በጌታ ኢየሱስ ቤዛነት ብቻ ከጥፋት በመዳን ህያዋን ሲሆኑ ቤዛነትን በሰጣቸው ጌታ ታምነው መኖር እንዲገባቸው የዳኑበት መሰረት ያሳያል። ሰዎች ንስሐ ስንገባ፣ ኃጢአታችንን ስንተው፣ ክርስቶስን በልባችን ስንቀበልና በዳግም ልደት ከውሃና ከመንፈስ ስንወለድ በእውነት ድነናል፤ አሁንም ግን በህይወት ዘመናችን ስንኖር …
Continue reading አለማዊነት(2..)

ጸጋ የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ (1…)

‘’የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።’’ (2ቆሮ.8:9) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው በእግዚአብሄር ፊት ብቁ አድርጎ የሚያቆመንን ጸጋ ሊሰጠን ነበር፤ ጸጋው ዋጋ የማይተመንለት፣ ሰዋዊ ያልሆነ መለኮታዊ ቸር ስጦታ ነው፤ እምነታችንም የሚጸናው ይህን መለኮታዊ ስጦታ በመረዳትና በመቀበል ላይ ነው። ቃሉም ሲናገር፦ ‘’እኛ ሁላችን ከሙላቱ …
Continue reading ጸጋ የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ (1…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(6… )

የእውነተኛው ሃይማኖት ብቸኛ መሳርያ ወንጌል ነው፤ የወንጌል ምስጢርም ክርስቶስ። ወንጌል የጌታን ድል ስለሚያውጅ ነፍሳትን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ይሰበስባል፣ ሃይል ያለው የትንሳኤ መንፈስ ስለሚሰራም ሃሰተኛ ትምህርቶችን ይዋጋል፣ በቃሉ አስተማማኝ ቃል-ኪዳን የገባ አምላክ ለሰው ልጆች አይዋሽምና በሙሉ የጸና የእምነት መሰረት ሆኖ ይኖራል። ወንጌል የሚታመን ዘላለማዊው የእግዚአብሄር አሰራር የተገለጠበትም አዋጅ ነው። ወንጌል በተለያዩ ዘመናት ከተነሱ የሃሰት ሃይማኖቶች በኩል …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(6… )

የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)

እግዚአብሄር ያመለከተንን አይተን ባንወደውም፣ ከፊታችን ያኖረውን ትእዛዝ ሰምተን ባንመርጠውም፣ ሃሌሉያ አሰኝቶ ባናመሰግንበትም እርሱ ያዘዘውና የተናገረው ነገር በሙሉ በጎ ውጤት አለው። የእግዚአብሄር ንግግር የተሻለ መንገድ አመልካች ነው፣ የተሻለ ህይወት አለው፣ የተሻለ መጨረሻም አለው። እግዚአብሄር ነገሮች ከመምጣታቸው አስቀድሞ ይናገራልና፣ ሁኔታዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ስለ እነርሱ ያመለክታልና፣ የድርጊቶቻችንን ውጤት እንድናውቅም ያመለክታልና፦ ስለዚህ እምቢታ ካሳየን ያለማስተዋላችንና ድምጹን ለመቀበል ያለመፍቀዳችን እጅግ …
Continue reading የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)