ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ በሰራው መንፈሳዊ ስራ ድልን ያገኘው ነህምያ እግዚአብሄር ረድቶት ያሸነፈበትን ጥበብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡- ነህ.4:1-9 ”ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ። በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፡- እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።አሞናዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ። በድንጋይ …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[1…]
Month:March 2021
ምን እንስራ?[3…]
• እግዚአብሄር ምን እንድንሰራ ነው የሚፈልገው? ሮሜ.12:11-12 ”ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ…” የእግዚአብሄር ልጆች ቀዳሚ ስራ እግዚአብሄርን ማመንና መከተል እንዲሁም ሲሰራ መንገድ እንጂ እንቅፋት ያለመሆን ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በአባትነቱና በአምላክነቱ ካልወደደው ትክክለኛው የህይወት ይዘት ውስጥ ሆኖ ሊመላለስ አይችልም፡፡ አይሁድን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡- ዮሐ.8:39-42 ”መልሰው ፡- አባታችንስ …
Continue reading ምን እንስራ?[3…]
ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]
በጎውን፣ መልካሙንና የተሸለውን የጌታ ምህረት ለማግኘት የአለምን ፍቅር፣ የስጋን ምኞትና ሰይጣናዊ ልምምድን መተው፣ መሸሽና መጸየፍ ግድ ይላል፡፡ አመጽን ማቆም፣ ከክፉዎች መለየት፣ ወደተውነው ክፉ ልማድ ዳግም ያለመመለስ ውሳኔን በራስ ላይ ማሳለፍ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከተከለን ስፍራ ያለመልቀቅ፣ ከክፋት መራቅ፣ የራስን ለርሱ አሳልፎ መስጠትና የጌታን ፈቃድ መከተል የፈለግነውን የጌታ ምህረት እንድንቀበል ያግዘናል፡፡ ጌታን መከተል፣ ቃሉን በፈቃደኝነት መቀበል፣ …
Continue reading ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]
አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ (በእብራይስጥ ሲጠራ መሲህ/የተቀባ) የተባለ፣ ሁለተኛው ሰው ሲል ቃሉ የጠራው፣ የሰው ልጅ ሲል እርሱ ራሱን ያስተዋወቀው ለእግዚአብሄር አላማና የዘላለም ፈቃድ አስፈጻሚነት የተቀባ ሰማያዊ ሰው ነው፡፡ ሰዎች እርሱን ማን ሲሉ እንደሚጠሩት ጠየቀ፡- ” ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፡- ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም መልሰው፡- መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፡- ኤልያስ፥ …
Continue reading አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]
