በጸጋ ላይ ጸጋ ይጨመር ዘንድ (2…)

ባለጸጋ አምላክ በስጋ ሲገለጥ ቃሉ እንዳለው፦ ‘’ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። … እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።’’ ይላል (ዮሃ.1:14፣16,17)። ባለጸጋ አምላክ ከየትኛውም ፍጥረት መጀመሪያ አስቀድሞ፣ ማንም ሳይኖር ቃል የሆነ አምላክ …
Continue reading በጸጋ ላይ ጸጋ ይጨመር ዘንድ (2…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )

ብቸኛውና ፍጹሙ ሃይማኖት መለኮታዊ ምንጭ ስላለው ከአህዛብ እምነት የተለየ ስራ ይሰራል፣ የተለየ ባህሪም ያለው ነው፤ ይህ ሃይማኖት በጌታ መገለጥ ፍጹ ሆኖ ልስ ልጆች ተሰጥቶአል ስለዚህ ይህ ሃይማኖት ወደ እኛ ሲመጣ፦ 1.አዲስ ስርአትን ያበስራል በብሉይ ኪዳን የነበሩት እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሄር ፊት የሚቀርቡበትን መንገድ ለውጦ በአዲስ መንገድ በመተካት የአብረሃምን እምነት ፍጹም የሚያደርግ ስርአት በጌታ ተገልጦአል። አስቀድሞም ቢሆን …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )

መንፈሳዊ ድካም(1… )

​​​​​​​​መዝ.107:11-13 ‘’የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥ ልባቸው በድካም ተዋረደ፤ ታመሙ የሚረዳቸውም አጡ። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ በመከራቸውም አዳናቸው።’’ በእግዚአብሄር ላይ አመጽ የሚሆነው በእግዚአብሄር ምክር ሳንሄድ ስንቀር፣ ተግሳጹን ንቀን ችላ ስንል፣ ማስጠንቀቂያውን ምናምን ስናደርግ ነው። ይህን ባደረግንበት በፈንታው ግን በግልጽ ወይም በስውር የሚመጣ መከራ ያገኘናል፤ በግልጽ በስጋችን ላይ በሚሆን የተለያየ ህመም፣ ደዌ …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(1… )

ያለጊዜው አትፍረዱ(1… )

እግዚአብሄር ሁሉን የፈጠረው ነገሩ ከሚኖርበት ጊዜና ስፍራ አንጻር ነው፣ ስለዚህ ምንም በርሱ የተፈጠረ ነገር ይኑር እንደተጀመረ ሁሉ እርሱ ባለው ጊዜና በወሰነው ስፍራ ይፈጸማል፣ እርሱ በፈቀደው ስፍራ ይኖራል ያበቃልም ፣ ይህ የማይሻር እውነት አማኞች ሊጠብቁት የተገባ ነው፦ ‘’ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም …
Continue reading ያለጊዜው አትፍረዱ(1… )