በእግዚአብሄር ፊት በአገልግሎት በቆሙ ሰዎች ላይ ከተፈጠሩት ስብራቶች አንደኛው አስደንጋጭ ክስተት ኦዛ ላይ የደረሰው ስብራት ነበር፡፡ኦዛ በእግዚአብሄር ታቦት ፊት እየሄደ ባለበትና በደስታ እግዚአብሄርን በሚያገለገልበት በዚያች ወቅት ድንገት በስህተት የፈጸመው ድርጊት በመላው እስራኤል መሀል እስከወዲያኛው የሚታወስ መቅሰፍት አምጥቶበታል፡፡ይህን ክስተት ያስተዋለ ሁሉ እግዚአብሄርን እንዴት ማገልገል እንዲገባው ቆም ብሎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄርን ማገልገል እንዴትና እስከምን ድረስ የሚለውን ጥያቄ የሙሴና …
Continue reading የአገልጋይ ስብራት[1/2]
Month:September 2020
እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]
ተፈጥሮአችን ስለሆነ ሰዎች እንደሚመስለን እንገምታለን፡፡እንደሚሰማንም እንናገራለን፣ሊሆን ይችላል ብለን፡፡መሰለኝን አምነን እንቀበላለን፡፡ብዙ ጊዜ መስሎን የነበረ አሳብ ውስጣችን ከርሞ ወደ ምስል ይለወጥና የአስተሳሰባችንን አቅጣጫ ይቀይረዋል፡፡መሰለኝ እያልን ፣ፈራ ተባም እያልን እንጀምራለን፣ ነገራችንን፡፡ከጊዜ ወደጊዜ እያሳደግነው ከሄደና በታናሽነቱ ካልገዛነው አድጎ ወደ እምነት በመቀየር በተራው ይገዛናል፣ደግሞም ይመራናል፡፡ የመሰለኝ ጉልበት የሚገለጠው በዝግታ ነው፡፡ እውነት በሚገኝበት ስፍራ ላይ ልብን በሙላት ማዘንበል ከግምት አስተሳሰብ ያወጣል፡፡”እከሌ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]
ቀርሜሎስ እንገናኝ [1/2]
ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በዘመኑ የእግዚአብሄርን ህዝብ ካሳተው አጋንንታዊ አሰራር ጋር ሲዋጋ የኖረ፣ ህዝቡን ወደ አምላኩ ሊመልስ የታገለ እንዲሁም በፍጻሜው ወዳገለገለው አምላክ በክብር የተሰበሰበ የእምነት ሰው ነበር፡፡ነቢዩ በዘመኑ በእስራኤል ምድር ላይ በነገሰው የባእድ አማልክት ምክኒያት በህዝቡ ላይ የመጣውን የእግዚአብሄር ተግሳጽ ለንጉሱ አመልክቶታል፡- ”በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፡- በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል …
Continue reading ቀርሜሎስ እንገናኝ [1/2]
መመለሰ – ለእውነት ንሰሀ
መታረቅ፣ መስማማት፣ ሰላም ማውረድ፣ መቀራረብና የመሳሰሉት የሰላም ማስቀጠያ መንገዶች በማህበረሰብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡ የሰው ልጅ የአብሮነት እሴትን በልቡ አትሞ ስለያዘ በተለይ እርቅ በሚባል የአንድነት ማሰሪያ ላይ ትልቅ አትኩሮት አለው ሊባል ይቻላል፡፡ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ መታረቅን ይሻና መታረቂያውን የማይስማማበት አጋጣሚ ይገጥመዋል፡፡ሁላችን ብንሆን እርቅ ሰላም እንደሆነ ይገባናል ስለዚህ እንስማማበታለን፡፡የእርቁን ሂደት ወይም አላማ ግን ልንወድደው ካልቻልን አንቀበለውም፡፡ለምሳሌ …
Continue reading መመለሰ – ለእውነት ንሰሀ
