ታዝዘው የቀረቡና የተጠጉ ልባቸው ከእምነት በዛለ ጊዜ ያለመታዘዝ እንደሚያሸንፋቸው ቃሉ ያስተምራል፡፡ታዝዘው ወደ ምድረ-በዳ የወጡት እስራኤላውያን ባልታዘዙ ወቅት በነበሩበት ምድረ-በዳ አልቀዋል፡፡ድምጹን እየሰሙ ለድምጹ ተግባራዊ ምላሽ የማይሰጡ በህይወት ላይ በሚፈጠር ጠንቅ ይጠቃሉ፡፡እግዚአብሄር በባሪያው በኢያሱ እጅ ምሪትን ብቻ ሳይሆን እረፍትን ሊሰጣቸው እቅድ ነበረው፡፡እስራኤላውያን ግን ባለመታዘዛቸው የታሰበላቸውን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ ዕብ.4:6-9 ”እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው …
Continue reading ያለመታዘዝ ጠንቅ
Month:August 2020
መንፈሳዊ ሪቫይቫል- ከሴኬም ወደ ቤቴል ተመለስ!
እግዚአብሄር ያእቆብን ስለወደደው ወደ በረከቱ ስፍራ እንዲመለስ አስታወሰው፡- ዘፍ.35:1-10 እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፡- ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ።ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ። እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፤ ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር …
Continue reading መንፈሳዊ ሪቫይቫል- ከሴኬም ወደ ቤቴል ተመለስ!
አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[2/2]
ሰው ህያው የሆነ ነፍስና የሚረግፍ ስጋ ውህደት ነው።ህያው ነፍስ ከእግዚአብሄር እፍ ከተባለ የህይወት እስትንፋስ ስለተገኘች የምትጠፋ አይደለችም፣ ረቂቅና መንፈሳዊ ስለሆነች የመታየትም የመዳሰስም ችሎታ የላትም።ስጋ ግን የአፈር(ምድራዊ) ነው፣ ግኡዝ፣ የሚታይና የሚዳሰስ ጭምር። ዘፍ.2:7 ይህን ያረጋግጥልናል፦ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።“ እውነታው እንደሚያሳየን የምድር አፈር ደቃቅ፣ …
Continue reading አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[2/2]
በዘመን መሀከል እግዚአብሄር
የባቢሎን ምድር በገነነችበት ዘመን ምድሪቱን ያሳወቁትና ዝናዋን ከፍ ያደርጉት ነገስታቶችዋ ብቻ አልነበሩም፡፡ምድሪቱዋ የመናፍስት መናሀሪያ እንደመሆንዋ በአማልክቶቹዋ ብዛትም የታወቀች ነበረች፡፡የመንግስታቶችዋ ዝና፣ ስመጥር ስራዎችና ወረራዎች እንዲሁም ጠቢባኖችዋ በዘመኑ ከፍ ያሉ ነበሩ፡፡በነዚያ ዘመናት መካከል ግን የእስራኤል አምላክና የባቢሎን አማልክት የሚወዳደሩበት አውድና አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡በአጋጣሚው መሀል ህያው አምላክ የመረጣቸው ህዝቦች ከአህዛብ መሃል ተገኙ፤ የአይሁድ በባቢሎን መገኘት ግን የእንግድነት ሳይሆን ይምርኮና …
Continue reading በዘመን መሀከል እግዚአብሄር
