የታላቁ አምላክ ሀይል(1..)

የእግዚአብሄር ሀይል ወይም መለኮታዊ ሀይል ከእግዚአብሄር ባህሪያት መሀል አንደኛው ነው፡፡ እግዚአብሄር አምላክ ነው፣ ጌታ ነው፣ መድሀኒት ነው፣ ሁሉን የሚችል፣ ሁሉን የሚገዛ፣ በሁሉ የሚኖር፣ ሁሉን በራሱ፣ ለራሱና ከራሱ ያደረገ ድንቅ አምላክ ነው፡፡ ይህ አምላክ ሁሉን በሀይሉ ያደርጋል፡፡ ሀይሉ ጉልበቱን የማንቀሳቀሻ ብርታቱ ነው፡፡ ዘዳ.10:16፤17”እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም …
Continue reading የታላቁ አምላክ ሀይል(1..)

ስለ መስቀሉ ቃል ‹1..›

የእግዚአብሄር ቃል ስለ መስቀሉ ቃል በ1ቆሮ.1:18 ላይ እንዲህ ይላል፡- ”የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” በመስቀሉ ቃል እውቀት ላይ የሚቀርቡ አሳቦች ወይም የሚንጸባረቁ አቁዋሞች የአማኝን የእምነት ይዘት ይወስናሉ፣ ያም ብቻ አይደለም የዘላለም አድራሻውን ጭምር ይወስናሉ፡፡ ለሚያምኑት ቃሉ የእግዚአብሔር ኃይል ሲሆን ለማያምኑት ሞኝነት (ከንቱና የማይረባ አሳብ ብቻ) ይሆንባቸዋል፡፡ ሰዎች ከንቱና የማይረባ ብለው …
Continue reading ስለ መስቀሉ ቃል ‹1..›

የጠላትን መንገድ እወቅ[3…]

የነህሚያ ተግዳሮት ነህሚያ ለእግዚአብሄር ህዝብና ለመቅደሱ የቀና አገልጋይ ነበር፡፡ የኢየሩሳሌም ፈርሳ መቅረትና የመቅደሱ ስርአት መቆም እያስጨንቀው በባእድ አገር ለብዙ ዘመናት ኖሮአል፡፡ በእግዚአብሄር ሰአት ከሚኖርበት የምርኮ ምድር ተነስቶ ወደ ገዛ ምድሩና ህዝቡ በመጉዋዝ አገሩ ደረሰና ቀጥታ ወደ ስራ ገባ፡፡ የነህሚያ ተግዳሮት የሚጀምረው ገና እግሩ ኢየሩሳሌምን ከረገጠ ጊዜ አንስቶ ነበር፡፡ ጠላቶች በእግዚአብሄር አምልኮና ስርአት ስለማይደሰቱ የከተማይቱና የመቅዱስ …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[3…]

እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜ ይፈጽማል‹1..›

እግዚአብሄር ሲናገር፡-”ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም” ይላል (ኢሳ.45:23)፡፡ እግዚአብሄር ይናገር እንጂ የተናገረው መሆኑ/መፈጸሙ አይቀርም፡፡ ስልጣን ያለው ቃል አሳቡን ማከናወን እንደማይሳነው እንኩዋን ህያው አምላክ ከሰው የሆነ ባለስልጣንም በችሎታው አይጠረጠርም፡፡ የእግዚአብሄር ንግግር ለመከናወኑ እርግጠኛ/እውነት በመሆኑ ሲናገር የሰሙት ሰዎች የተናገረውን ቃል በደስታና በተስፋ ይዘው ይጠባበቁታል፡፡ መጠበቅ እንዲህ እንደምንለው ቀላል አይደለም፡- ትግስት ይጠይቃል፣ እምነት ይጠይቃል፣ ጊዜም ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም የታመኑት …
Continue reading እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜ ይፈጽማል‹1..›