ጥሪ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ለመንግስቱ ወራሽ የመሆን ግብዣን ቢያጠቃልልም በተለይ ለእግዚአብሄር ስራ ለመለየት ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚመጣ ግብዣ ግን የወንጌሉ አገልጋይ ከመሆን ጋር ይያያዛል። እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለመንግስቱ የተጠሩ የእስራኤል ህዝብን ከግብጽ ምድር አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር አፍልሶአቸዋል። ይህም በአዲስ ኪዳን ከአለም ወጥተው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለሚፈልሱ የእግዚአብሄር ልጆች ምሳሌ ነበረ። እግዚአብሄር እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ …
Continue reading ጥሪና አገልግሎት(1…)
Month:October 2022
እውነትን ፍለጋ(1..)
“ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳንዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?” (ሚል.2:10) አንድ አምላክ የፈጠረን መሆኑን መናገር በአንደበት ከመግለጽ ባለፈ አለማትን በሞላ የምንመረምርበትና የምናይበት የቃል ምስክር ነው። በቃሉ በኩል አለምን ለሚመለከተው ብዙ ነገር ያይበታል፣ የሚያጸና እውቀት ይገበይበታል፣ እውነትን የሚሻም ከሆነ ጥልቅና ሰፊ እውቀት ያገኝበታል። በአለማት ውስጥ ምን …
Continue reading እውነትን ፍለጋ(1..)
መልአክ የሚያሳርግ መሰውያ
እግዚአብሄርን የሚጸየፈው መስዋእት አለ፣ እግዚአብሄር የማያውቀው መስዋእትም አለ፣ ደግሞ እግዚአብሄር የሚቀበለው መስዋእት አለ (ይህን መስዋእት መልአክ ራሱ ይዞት ወደ ሰማይ ያርጋልና ታላቅ መስዋእት ነው) “ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፤ ማኑሄና …
Continue reading መልአክ የሚያሳርግ መሰውያ
ልክ ለልከኝነት(2…)
ልክ የመጠን ዳርቻ እንደመሆኑ ነገሮች ከልክ እንዳያልፉብን ብንጠነቀቅ ልክ ነን። የኛ የሆኑ ነገሮቻችንና የሌሎችም ነገሮች ጨምሮ ከልካቸው መስመር እንዳያልፉ እንደሚያሳስብ ቀጥሎም ማየት እንችላለን፤ በእርግጥ እነርሱን ማወቅ ለሚዛናዊ ህይወት ይጠቅማል፦ • የቅጣት ልክ 2ቆሮ.2:5-7 “ነገር ግን ማንም አሳዝኖ ቢሆን፥ እንዳልከብድባችሁ፥ በክፍል ሁላችሁን እንጂ እኔን ያሳዘነ አይደለም። እንደዚህ ላለ ሰው ይህ ከእናንተ የምትበዙት የቀጣችሁት ቅጣት ይበቃዋልና እንደዚህ …
Continue reading ልክ ለልከኝነት(2…)
