የአይን ነገር የብዙ ነገር ጉዳይ ነው፡- አይንን አስበን ወደ ምንነቱ፣ ወደ አፈጣጠሩ፣ ወደ ግልጋሎቱ እያነጣጠርን ስናጠና የእርሱን አስፈላጊነት የምናጎላበት ምክንያት ተገቢ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ባለአይን/ አይናማ ሰው ይህችን አለም በማየት እውቀት ስለሚኖራት የማየት ችግር ካለባቸው አይነስውራን ይልቅ የእርስዋን ግፊት የመቁዋቁዋም አቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ እንቅፋቶችን አይናማው ሰው መሻገር የሚችላቸው ቢሆንም የእይታ ግርዶሽ ለገጠመው ግን ፈተና …
Continue reading የአይን ነገር(1…)
Month:February 2022
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር
የአምላክ ምስጋና ሊያውም በሰንበት ቀን (በእግዚአብሄር እረፍት ውስጥ) የሚቀርብ እጅግ የላቀ ደስታና ምህረት የሚያመጣ በመሆኑ ዘማሪው ንጉስ ያን አስተውሎ በመዝሙሩ ጅማሬ በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር ይላል፡፡ ሲቀጥልም፡- ”እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብርንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም ከዘላለም ነህ። አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ …
Continue reading በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር
የመለያችን ምልክት (1..)
እግዚአብሄር ምልክት የሚያኖርባቸው ሰዎች በእግዚአብሄር የታዩ ሰዎች ናቸው፤ በእርሱ ከለላ ውስጥ ያሉ በአላማው ውስጥ የተቀመጡም ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር እቅድ ላይ በክፋት የተነሳው ቃየን እንኩዋን ከሚያገኘው ክፋት ይጠበቅ ዘንድ በሰዎች ዘንድ የመጀመሪያ የሆነውን ምልክት ከእግዚአብሄር ተቀብሎአል፡፡ ይህ ምልክት እርሱን በሰራው ሀጢያት ከመጥፋት የሚታደገው የእግዚአብሄር ምልክት ነበር፡፡ እግዚአብሄር ለራሱ ለለየው ህዝብ ደግሞ የተለየ ጥበቃ በማድረግ ምልክት በላዩ ላይ …
Continue reading የመለያችን ምልክት (1..)
የማንበቃበትን እክል መሻር
የማንበቃበት ነገር፡- በእግዚአብሄር መገኛ አካባቢ ይዘን የምንመላለሰው ነገርና አካሄዳችን በማንነታችን የሚደነቃቀፍ ሲሆን፣ የምንመራበት የህይወት መርህ ደካማ ሆኖ ያለን የህይወት ይዘት የማይበቃ ሆኖ ሲቆጠር፣ የእግዚአብሄር ቃል የሚቃወመው የህይወት ይዘት ሲኖረን፣ መርሀችን የተተወ/መታሰቢያ የማይገኝለት መርህ ከሆነ ያም ከአለም ልማድ እንዳንወጣ ካነቀን፣ ከመንፈሳዊ የህይወት ደረጃ የተጣለ/በአለም ብቻ ተቀባይነት ያለው ቃሉ ግን የሚኮንነው ልማድ ካለን፣ የተወገደ/በእኛ ቁጥጥር ስር የሌለ …
Continue reading የማንበቃበትን እክል መሻር
