ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(3… )

እምነት በሃይማኖት ትምህርት ላይ መመስረት ይጠይቃል። ሃይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት እንጂ ቁሳዊ አይደለም፣ መደመርና መቀነስ ስሌት የሚመራውም አይደለም፣ ትምክህቱም ሳያይ መዘርጋት እንጂ ማስተማመኛ ሰብሳቢ አይሆንም፣ እምነትና ማስረጃ አብረው አይሄዱም፣ አማኝ የሰማውን መለኮታዊ ቃል ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል እንጂ ምረመራ አድርጎ ማረጋገጫን አያቀርብም። ‘’እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(3… )

ቃለ መለኮት(3…)

የህያው እግዚአብሄር ቅዱስ ቃል አመጸኛና ታዛዥ ላልሆኑ ሰዎች የትኩረት አቅጣጫ የተነፈገው፣ ቀዝቃዛ ስሜት በሚታይባቸው ቸልተኞች ተሸፍኖ ያለ፣ አሳቢነቱ ዝቅተኛና ትርጉሙ በማይሰማው ኢ-አማኝ አእምሮ ውስጥ ከንቱ የሚመስል ወይም ለፍጥረት ብዙም ፍላጎትና ጉጉት የማይፈጥርና የማይስብ ጉዳይ የሚመስል ነው። አለምም በማየት፣ በመዳሰስና በቀመር ስለምታምን በነዚህ ስጋዊ መታመኛ መሳሪያዎች የምትደገፍ ናት። እግዚአብሄር ግን ስለቃሉ በመናገር ያሳስባል፦ ‘’እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ …
Continue reading ቃለ መለኮት(3…)

የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (2..)

የመስቀሉ ቃል የመስቀሉ ቃል የወንጌል ማእከላዊ መልእክት ሆኖ ሳለ የበዙ አስተማሪዎች ያን ባለማስተዋል ትኩረታቸውን ወደ ሌላ አድርገው በደህንነት ትምህርት ላይ ብዙ ሰዋዊና አጋንንታዊ ትምህርቶች ጣልቃ እንዲገቡ ምክኒያት ሆነዋል። በሌላ በኩል በሃዋርያቱ በኩል ለአለም የደረሰው ወንጌል ያለመቀያየር እንዲቀጥል ከመስራት ይልቅ በተለያዩ ትምህርቶች እንዲበረዝ፣ በወግና በስርአት እንዲታሰር አድርገዋል። የመስቀሉ ቃል በትክክል በሚሰበክበት ስፍራ ሁሉ ነፍሳት ወደ ጌታ …
Continue reading የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (2..)

የመመለስ ትርፍ {1..}

መመለስ ከወጡበት፣ ከተዉት፣ ከተሰናበቱት፣ ከተጣሉት፣ ካኮረፉት እንዲሁም ከጣሉት ነገር ሊሆን ይችላል። መመለስ ከወጡበት ነገር ሲሆን ዳግም ወደ ቤት፣ ወደ አገር፣ ወደ ስራ፣ ወደ ልማድ፣ ወደ ካዱት፣ ወደ ረሱት፣ ወደ ጠሉትም ነገር ሁሉ ሊሆን ይችላል። በመመለስ አልፈልግም ብለው ከተዉት ነገር፣ ስራ ወይም ሰው ዳግም የመገናኘት እድል ይፈጥራል። የጠላነው ይሁን የወደድነው በሆነ አጋጣሚ ወይም ተጽእኖ ምክኒያት ትተነው …
Continue reading የመመለስ ትርፍ {1..}