እንደተከፈለልን ለመመላለስ ከወሰንን እግረመንገዳችንን ከእግዚአብሄር የተቀበልነውን ስጦታ እንደ ክብሩ መጠን መያዝ እንዲገባን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ የተሰጠን መዳን የተከፈለውስ የዋጋው ተመን ምን ያህል ነው? ስንል መጠየቅም ተገቢ ነው፡፡ በእርግጥ መዳን ሰዋዊ የዋጋ ተመን ከቶ የለውም፣ ስለዚህ ልኬት አይወጣለትም፣ ተመንም አይተመንለትም፤ የሰው ክፍያ ሊመጥነው ሆነ ደረጃ ሊሰጠው አይችልም፡፡ ሰው ግን ያን ያገኘውን ታላቅ ነገር እጅግ ተጠንቅቆና አክብሮ በእውቀት …
Continue reading እንደተከፈለልህ ተመላለስ (2..)
Month:October 2021
ኢያሪኮን መስራት? (2..)
ኢያሪኮ ፈርሶ እንደቀረ የተደመደመ ጉደይ ሆኖ ሳለ በአእምሮ ውስጥ ትዝታው አልለቅ ካለ የቀደመው ሀጢያት ከልብ ሊርቅ አልቻለም እንደማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ኢያሪኮን ለምን ረገማት? ኢያሪኮ ማለት ከተማዋ፣ አካባቢዋ ወይም የኑሮዋ ስርአት ብቻ ሳይሆን የአምልኮ ልማድዋን ተከትሎ የተፈጠረው ያልተገባ የህይወት አኑዋኑዋር ሁሉ ማለት ነው፡፡ ኢያሪኮ የአህዛብ ከተማ በመሆንዋ የአህዛብ ልማዶችን የተሞላች ስለመሆንዋ አያጠራጥርም፡፡ ልማዶችዋ እግዚአብሄርን የሚያስደስቱ አልነበሩም፡፡ …
Continue reading ኢያሪኮን መስራት? (2..)
አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)
እግዚአብሄርን በማወቅና ባለማወቅ መሀል ያለው ልዩነት የሞትና የህይወት ያህል ዋጋ እንዳለው ጌታ ኢየሱስ በአጽንኦት ተናግሮአል፡፡ ጌታ በዮሐ.17:3 የተናገረው እንዲህ ይላል፡- ”እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” በትንሹ ልባችን ስለርሱ ባወቅነው እውቀት ምክኒያት ያገኘነውን ታናሽ እምነት ይዘንና ወደ እርሱ ቀርበን አላፈርንም፤ እንዲያውም ከርሱ ጋር በምንኖርበት ዘመን ሁሉ ሳይነቅፈን …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)
ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]
ህዝቡን የሚያድን አምላክ ለሰው ልጆች የሆነ የማዳኑን ብስራት ሲገልጥ በሰማይ የተገለጠው ትእይንት ልብ የሚሞላ ነው፡- ”እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም …
Continue reading ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]
