የእግዚአብሄር ቸር ስጦታ

የዳዊት መዝሙር። ‘’ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል። እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፥ አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት። አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፤ የእግዚአብሔር ቃል ቅን ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና። ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች።’’(መዝ.33:1-5) እግዚአብሄር በበጎነቱና በሰጪነቱ የታወቀ አምላክ ነው፤ ከሰጪነቱ ታላቅነት የተነሳ ቸር አምላክ ይባላል፤ ሰጪነቱ ህያው አድርጎ …
Continue reading የእግዚአብሄር ቸር ስጦታ

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(10…)

ሰው ያለፈጣሪው መኖር እንደማይችል የሚያውቅ ሰይጣን ሰዎች እርሱ አምላክ እንደሆነና መመለክ እንደሚገባው አድርጎ በተለያየ መንገድ ያሳምናቸዋል፣ በአገልጋዮቹ አድርጎ ይናገራል፣ ብዙዎችን አሳምኖም በሚታዩ ጣኦታት በኩል እንዲያመልኩት ያደርጋል፤ ይህን በተመለከተ ንጉስ ዳዊት እንዲህ ብሎአል፦ መዝ.96:4-5 ‘’እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።’’ ዋናው ነገር ሰዎች …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(10…)

መንፈሳዊ ድካም(3…)

በመስማት ድካም እንደተያዝን በነፍሳችን ውስጥ ሃብት ሆነው የተቅመጡ ውድ መንፈሳዊ ነገሮችን ነፍሳችን እንደምታጣ አይተናል። መንፈሳዊ ድካም ውስጣችን ገንግኖ እንደሆንበተለይ የመስማት ጉልበትን በመብላት አማኝ ወገን ከእግዚአብሄር ጋር እንዳይቀራረብ ያደርጋልና ነገሩ ቸል መባል የሚችል አይነት አይሆንም፤ የችግሩ ጽናት ብዙ ጉድለታችንን አመልካች ነውና፤ በየትኛውም አቅጣጫ የሚፈጥረው ተጽእኖም ቀላል አይደለም፦ በርሱ የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ነገር መርጠን፣ ለእኛ የሚመጥን ነገር ለይተንና …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(3…)

ተስፋው ብርቱ ነው(1…)

የእግዚብሄር ተስፋ በእግዚአብሄር ላይ ላለን እምነት የጀርባ አጥንትና መሰረት ነው። እግዚአብሄርን የሚያምኑ እርሱን ተስፋ አድርገው ይጠብቃሉ፤ ተስፋ በሌለበት እምነት የለምና። ቃሉ የሚነግረን እንዲህ በማለት ነው፦ እብ.11:1-3 ‘’እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።’’ ተስፋ በማይታይ ግን ሊሆን ባለው …
Continue reading ተስፋው ብርቱ ነው(1…)