ሰው የአምላኩን ቸርነት ያውቅና ስጦታውን ይቀበል ዘንድ የእግዚአብሄርን አሳብ ማስተዋል እንደፈቃዱም እርሱን መፈለግ ይገባዋል።ነገር ግን ሁላችን ያን ልናደርግ ባለመቻላችን ከዚያም በላይ ደግሞ እንድናገኘው ፍላጎት ባለማሳየታችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ሰጪው እንዳያመለክተን መቀበል የነበረብንንም የርሱን በጎ ስጦታ በአንድነት እንድናጣ አድርጎአል።በመጽህፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የእግዚአብሄርን ባህሪ ጠንቅቆ የተረዳው ንጉስ ዳዊት ግን እግዚአብሄርን በመፈለጉ የተቀበለውን መንፈሳዊ በረከት በመዝሙሩ ገልጦታል፦ …
Continue reading እርሱ ጠባቂዬ መጋቢዬም ነው
Month:September 2019
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
መዝ.23:3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። ነፍስ ከየት ወዴት ተጉዛ ወዴት ትመለሳለች? ወይስ ምን የሚያሳስባት ጉዳይ ቢገጥማት ከመንገድዋ ፊትዋን ትመልሳለች? በነፍስ ጉዳይስ የሚያሳስብ ጉዳይ ምን ኖሮ መመለስን ትመርጣለች? መቼም ቢሆን ከተቃናልን የህይወት እርምጃ መመለስ፣ከተሳካልን ድል ወደ ሁዋላ ማለት፣ከተጉዋዝንበት ርዝመት ያለው መንገድ ማፈግፈግ ወይም የማስጠንቀቂያ ደውል ሰምተን የእኛ የምንላቸውን ለመሸሸግ ሙከራ ማድረግ፣ እንዲህ ቀላል …
Continue reading እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
የእውነት እውቀት[3/3]
1.4 የወንጌል መጽሀፍት ስለኢየሱስ ሕይወት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ፣ ደቀመዛሙርት የእርሱን ወዲያው መመለስ ይጠባበቁ ነበር፣ በህይወት እያሉ እንደሚከሰት ገምተው ነበርና፡፡በዚህም ምክንያት ለወደፊት ትውልዶች የሚሆን የጽኁፍ መረጃ ለማስቀመጥ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው ቀረ፡፡ ነገር ግን የዐይን ምስክሮች እየሞቱ መሄድና የቤተክርስቲያን የሚስዮናውያን ተልእኮ ፍላጎት እያደገ ሲሄድ፣ የክርስትና መሰረት የሆነውን ጌታ ህይወት እና ትምህርቶች በፅሁፍ ማስፈር …
Continue reading የእውነት እውቀት[3/3]
የመጨረሻ ዘመን[3/4]
2ኛው የመጨረሻ ቀን ምልክት:- ሰዎች ከእግዚአብሄር ይልቅ ገንዘብና ተድላን ይወዳሉ በሰዎች ዘንድ (በተለይ በዚህ ዘመን)የምንኖረው ህይወት ሙሉነትመለኪያ የተድላ ጣርያ ወይም ከፍታውናየስኬቱ መጠን ማደግ ነው፡፡ለአለም ሰዎችገንዘብና ንብረት ካለ ህይወት ሙሉ ነው፡፡በዚህ አስተሳሰብ ምክኒያት ብዙዎችለተድላ ህይወት ከምንም በላይ ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ያንን ለማግኘትም ማንኛውንም መስዋእትነት ይከፍላሉ(ገላቸውን ይሸጣሉ፣ሰውን ለገንዘብ ይገድላሉ፣ባልሰሩት ስራ ጉቦ ይበላሉ፣የሰው አካል ሰርቀው እስከመሸጥ ይደርሳሉ…ሌላም ሌላም)፡፡ በሌላ …
Continue reading የመጨረሻ ዘመን[3/4]
ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]
ረ. የሀዋርያቱን የማይለወጥ ወንጌል በተመለከተ፡-ከእነርሱ ሌላ ወንጌልን አሻሽሎ የሚያቀርብ ቢኖር ሰማይ የሚቀበለው ሳይሆን እርግማን እንደሚያስረው ስለምታስተውል ነው፡፡ ሀዋርያቶች በመልእክቶቻቸው ውስጥ አጥብቀው ካነሱት ርእስ መሀል የሀሰት ትምህርት አንዱ ነበር፡፡ከሰውና ከአጋንንት የፈለቀ የሀሰት ትምህርት ከጌታ የተቀበሉትን ትምህርት እንደሚበርዝ አስቀድመው በመንፈስ ስላስተዋሉ አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ገላ.1:7-8 “እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።ነገር …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]
