እውቀተ መለኮት(1…)

ምድራዊ መንግስታት እውቀትን እንደ ስልጣኔ በር ቆጥረው ህዝባቸው ያውቅ ዘንድ ይለፋሉ። በሁሉን አቀፍነት አንጻር ይህ እውቀትን የማግኘት፣ የመረዳትና የመቀበል ዝንባሌ የትውልድ ማስቀጠያም ተደርጎ የሚቆጠር ነው፤ ምክኒያቱም ያላወቀ የማያስተውልና ወገንን ጠቃሚ ስለማይሆን ነው። በመንፈሳዊ ጉዳይም ከዚህ የላቀ አስፈላጊነት ባለው ሁኔታ እውቀት አትኩሮት ይሰጠዋል። በምድራዊ እውቀትና በሰማያዊው መሃል ግን ከፍተኛ ልዩነት ያለበት ነጥብ አለ፣ እርሱም የእውቀት መገኛው/ምንጩ …
Continue reading እውቀተ መለኮት(1…)

ለኛ የታሰበልን

በእግዚአብሄር ፈቃድ አካባቢ ያለውን የፍጥረት ስፍራ ሰው ማስተዋል ቢችል የምድር ፊት ዛሬ ላይ ምን ሊመስል ይችል ነበር? ሌላው ቀርቶ ሰው የታሰበለትን ቢረዳ፣ እግዚአብሄር ሲጣራ ቢሰማ፣ ለራሱ አሳብ ሳይሆን ለሰሪው ድምጽ ጆሮውን ቢያዘነብል የሰው ልጅ እንዴት ባለ ሰላምና ደስታ ይኖር ነበር? አለም መልኩዋም አሳቡዋም ምንም ቢያባብል በመጎተቻዋ ተጠልፈው እጅ ያልሰጡ ያተረፉት ነገር ብዙ ነው፤ በዚህ ሳያበቃ …
Continue reading ለኛ የታሰበልን

ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]

የነጻነት ትርጉም የነጻነት ህይወት ትክክለኛ ትርጉም በኢየሱስ የሚገኝ ነው፤ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጆች በነጻነት ከአምላካቸው ጋር እንዲኖሩ የነጻነት መንገድ ሆነ። ሰዎች በህሊና እየተመሩ ከሚኖሩበት ነጻ ህይወት ተገፍተው ወጥተው በዲያቢሎስ ጫና የእርሱን ፈቃድ ይከተሉና ይፈጽሙበት የነበረው ብዙ ሺ ዘመን ያበቃው በነጻነት የሚኖሩበትን መንገድ ጌታ ኢየሱስ ስለገለጠው ነበር፤ ያን የነጻነት ህይወት ሰዎች ሁላችን ልንኖር ክርስቶስ ሃጢያት ከሚባል …
Continue reading ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]

የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(2…)

ካለፈው የቀጠለ… – እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ… ይላል (1ቆሮ.14:9) በፍቅሩ ምክኒያት የተቀበልነውን ደህንነት በፍቅርና በሸክም ድህንነት ለተገባችው የሰው ልጆች ሁሉ ማሳለፍ ምህረት ካገኘ ወገን ይጠበቃል። ስለመዳን እያወሩ አዳኙን ያለመንገር አይቻልም፣ የተሰጣቸውን እያስተዋወቁና በሰፊው እየተናገሩ ሰጪውን ያለማስተዋወቅ ንፉግነት ነው። አይሁድ የአለም ሁሉ አዳኝ ጌታን ሊቀበሉ እጅግ አንገራግረዋል፤ ምህረትና ፈውሱን ከተቀበሉም በሁዋላ የተሸሸጉ አልጠፉም፤ …
Continue reading የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(2…)