እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜው ይፈጽማል‹2..›

እግዚአብሄር የተናገረውን እንደተናገረው ልክ/ ፍጹም አድርጎ በትውልድ መሃል በጊዜው እንዲገልጠው የተመቻቸ ስፍራ/ማረፍያ ልብ ይፈልጋል፡፡ በአዲስ ኪዳን ሊሆን የተጠበቀው፣ የሆነውም ይህ ነበር፤ ስለዚህ የእግዚአብሄር መልአክ የእግዚአብሄርን ስራ ሊያውጅ ሲገለጥ ወደ ሁለት ቤተሰቦች ዘንድ ሄደ፡- ወደ ካህኑ ዘካርያስና ወደ ማርያም ቤት፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ እልሳቤጥ በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ። ማርያም ለዮሴፍ …
Continue reading እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜው ይፈጽማል‹2..›

የውሳኔና ስምምነት አግባብ‹1…›

ወሳኝነት አባት የሆነው እግዚአብሄር ለፈጠራቸው የሰው ልጆች ያስተማረው ስልጣን ነው፡፡ ውሳኔ ከትእዛዝ ሰጪ አካል ይወጣል፣ ስልጣን በውሳኔ ተግባራዊነት ይገለጣል፣ እንዲሁም የእግዚአብሄር ውሳኔ ፍጹምና ሊታዘዙት የተገባ ሲሆን የእኛ ግን የሚዋዥቅና አቅም የሌለው ነው (በተለያዩ ምክኒያት ሰው ውሳኔውን ይለዋውጣል)፡፡ ለምሳሌ በዘጸ.9:5-7 ውስጥ ስለእግዚአብሄር ወሳኝነት ሲናገር፡- ”እግዚአብሔርም፡- ነገ እግዚአብሔር ይህን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል ብሎ ጊዜን ወሰነ። እግዚአብሔርም …
Continue reading የውሳኔና ስምምነት አግባብ‹1…›

የታላቁ አምላክ ሀይል(2..)

እግዚአብሄርንና ሀይሉን የሚያውቁ ሰዎች በሁኔታዎች አካሄድና በነገሮች መፈጠር አይደናገጡም፣ በአጋጣሚዎች ድንገት መከሰት አይርበተበቱም፤ ምክኒያቱም ከእነርሱ በላይ ያለውን ስለሚያወቁ፣ ከርሱ በቀር ማንም እንደሌለ ስለሚረዱ፣ ያለ እርሱ ፈቃድ የሚሆን ነገር እንደሌለ ስለሚያውቁ፣ ደግሞም የእርሱ አሳብ ለሰው ልጆች ሁሉ መልካም መሆኑን ስለሚያስተውሉ ነው፡፡ ነቢዩ ኤልሳ በአስጨናቂ ጠላቶች ተከቦ ሳለ የተናገረውን እንመልከት፡- 2ነገ.6:15-17 ”የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ …
Continue reading የታላቁ አምላክ ሀይል(2..)

ስለ መስቀሉ ቃል ‹2..›

የመስቀሉ ቃል የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መቀበልና በሀይል ከሞት መነሳት የሚሰብክ የወንጌል ክፍል ነው፡፡ በዕብ.9:28 እንደተጻፈው፡- ”እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።” ይላል፡፡ የሚበላ የህይወት እንጀራ ክርስቶስ ህያው በሆነው ስጋውና ደሙ ሊቀድሰንና ህይወትን ሊሰጠን ተገልጦአል፡፡ ወንጌልን አስደሳች የሚያደርገው በእርሱ መከራ የእኛ ደህንነት በመረጋገጡ፣ …
Continue reading ስለ መስቀሉ ቃል ‹2..›