ስለ ፍቅር፡- ፍቅር የሚባል ስጦታ ከመለኮት የመነጨና ልዩ ባህሪ ያለው፣ ከነገሮቻችን መሀል ከፍ ያለ የተሰጠን የማንነታችን ገዢ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ፍቅር ጥልቅ በመሆኑ አእምሮን ያልፋል፣ የልብ ፈቃድን ያልፋል፣ የነፍስ ምኞትን ያልፋል፣ ከመንፈስ ይዘትም ይልቃል፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ሲገባ ሁሉ ነገራችንን ያሸንፋል፣ ይቆጣጠራልም፡፡ እውነተኛ ፍቅር ልብ፣ አእምሮና አሳብን በመግዛትና ወደ ፈለገው አቅጣጫ በመምራት የደስታ ስሜትን በሁለንተናችን ያፈልቃል፡፡ …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [2…]
Month:December 2020
እስራኤልም ወደ ያእቆብ
እስራኤል ወደ ያእቆብ ወይስ ያእቆብ ወደ እስራኤል ነበር ለውጡ ? ወንድሙን ያታለለው ያእቆብ የእግዚአብሄርን አላማ ያስፈጽም ዘንድ ማንነቱ በእግዚአብሄር ተቀይሮ ስሙ እስራኤል ተብሎ ነበር፡፡ አባቱን ሳይቀር በመመሳሰል ያሳተው ይህ ያእቆብ በፈቃዱ ብኩርናውን ካቃለለው ከወንድሙ ከኤሳው የፈለገውን ብኩርና በወጥ ገዝቶ ይቀበል እንጂ የፈጸመው አመጽ ችግር ላይ የሚጥለው ነበር፤ በወቅቱ አባቱና እናቱ ስለራሩለት ብቻ ከተግሳጽ አምልጦአል፡፡ እግዚአብሄር …
Continue reading እስራኤልም ወደ ያእቆብ
ባለመቻል ማንከስ/ማነስ
ያለመቻል አቅም ማጣት፣ መጉደል፣ ማንከስ፣ ወደ ሁዋላ ማለት፣ ፍጥነት መቀነስ፣ ጥንቃቄ ያለማድረግ፣ በመሳሰለው ነገር ይገለጣል፡፡ አቅም ያጣንባቸው ጊዜያቶች በውስጣችን ያለውን አሳብ ወይም ራእይ እንዳንፈጽም ወደ ሁዋላ ይጎትቱናል፣ ወይም እቅዳችንን እንዳናከናውን ያደርጉናል፡፡ አቅማችን በራእያችን ልክ ወይም ከዚያም በላይ ካልሆነ ልንደርስበት የምንፈልገው ግብ ይርቃል፡፡ አንዳንዴ አቅም ማጣት በጥበብ ቢያዝ ችግሩ ሊታለፍ ይችል ይሆናል፤ ሆኖም በውስጥ የማይኖር እምቅ …
Continue reading ባለመቻል ማንከስ/ማነስ
ለማን ብዬ ልስማ?[2…]
ለማን ብዬ ልስማ – ለማን ብዬ ልሰማ ነው፣ ለራሴ ስል ካልሆነ፡፡የሚያጠፋኝ ብዙ ብዙ ነገር በአለም ውስጥ ስላለ እራሴን ለማዳን ስል ለራሴ ብዬ ቃሉን ልሰማ ተገቢ ነው፤ አለፍ ሲል ደግሞ ሌሎችን አድን ዘንድም ስለሚባለው ነገር ተጠንቅቄ ልሰማ ተገቢ ነው፣ ጠንቅቆ ያለመስማት ሰሚውንም አድማጩንም እኩል የሚያጠፋበት ጊዜ ስላለ ማለት ነው፡፡ በአለም ውስጥ የሚሰሙት እጅግ የበዙ፣ የተወሳሰቡና ሊያጠፉ …
Continue reading ለማን ብዬ ልስማ?[2…]
