የፍቅር ግዛቶች [1…]

የፍቅርን ጉልበት ሊረታ ማን ይችላል? በሀይል ያልተደፈረ ጀግና ስለፍቅር እጅ ሲሰጥ በሶምሶም ታሪክ ውስጥ የምናየው ነው፤ የህዝብ ታላላቆችም ቢሆኑ በክፉ ቀን ስለሚመሩት ህዝብ ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡ በእስራኤል ነገስታቶች ታሪክ ውስጥ እናያለን፤ ወዳጆችም ስለባልንጀራቸው ፍቅር ሲሉ አክብረው የያዙትን አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ዮናታን ለዳዊት እንዳደረገው፡፡ይህ ሁሉ የሚሆነው በፍቅር የማስገደድ ጉልበት ምክኒያት ነው፡፡ ፍቅር ስጋዊ አይንን ከራስ ወዳድነት …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [1…]

እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]

የተሳሳተ ሀይማኖት ለምን ከመሰለኝ ይነሳል? መሰለኝ የስህተት መፈልፈያ ዋሻ በመሆኑ ነው፤ የጥርጥር መሰረት በመሆኑም የተሳሳተ ሀይማኖት ያስፋፋል፡፡ ሀይማኖቱ በሚመስል እውቀት ላይ በመመርኮዙና ግምታዊ ድምዳሜን በመቀበሉ ምክኒያት መንገዱን ይስታል፡፡ ቀጥ ብሎ ማደግ በሚገባው ወቅት ተንጋድዶ ከፍ ይላል፣ ከነአመሉ እንደተወላገደ ሽቅብ ይሄዳል፣ ያለእርምት ይጎለምሳል፣ ስርም ይሰዳል፣ በመጨረሻ ግን ማምለጥ በማይችለው የስህተት ወጥመድ ላይ ይቆማል፣ ይነከሳል፡፡ በተለይ ግምታዊ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]

ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]

ባላንጣዎች ሁሌም በቅራኔ ውስጥ ያሉ ወገኖች ናቸው፡፡በውጊያ ሜዳ ይገናኙ እንጂ ከመፋለም ወደሁዋላ አይሉም፡፡አሸናፊ ለይቶ አንዱ ለሌላው እጅ ሳይሰጥም ፍልሚያው አያቁዋርጥም፡፡ በሁለቱም ተዋጊዎች በኩል በየጊዜው ለውጊያ ዝግጅት አለ፤ ላለመሸነፍ እጅ ላለመስጠትና ላለመገዛት ትግል አለ፡፡የተያዘም እንዲሁ ያመልጥ ዘንድ እስከሞት በሚደርስ ትግል ሳያቁዋርጥ ለነጻነት ይታገላል፤ ይህ የውጊያ ተፈጥሮ ነው፡፡ ውጊያ መንፈሳዊም ስጋዊም ነው፡፡ ስጋዊ ውጊያ በማይግባቡ፣ በተጣሉና ጦርነትን …
Continue reading ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]

ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ በተባለበት አለም ውስጥ ስኖር ምን መስማት እንዳለብኝና እንደሌለብኝ ማስተዋል የለብኝምን? ለመንፈሳዊ ህይወቴ እንድጠነቀቅ የሚያሳስበኝ አምላክ የድምጾችን ምንጭና አቅጣጫ እንዲሁም ይዘትና ተጽእኖ ስለሚያውቅ ለእኔ ደካማ ሰው ጥንቃቄ ሲል ይህን ማሳሰቢያ አስተላልፎአልና፡፡ አለማችን ውስጥ የተለያየ መንፈስ ያላቸው ድምጾች ቢያንስ ቢያንስ በየሰከንዱ ይፈጠራሉ፤ ሰው ጆሮ የሚደርሱ፣ ተጽእኖ ያላቸውና የሰውን አስተሳሰብ ሊጫኑ የሚችሉ ድምጾችን እንደሰማሁ በግርድፉ …
Continue reading የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]