የፍቅር ግዛቶች [6..]

ስለእግዚአብሄር ማንነት በሚወራበት ስፍራ ሁሉ ከእርሱ ጋር ስለፍቅር ሳይነሳ መታለፍ አይችልም፤ ፍቅር የእግዚአብሄር ታላቅ ባህሪ በመሆኑ በተለይ ለእኛ የእግዚአብሄር ፍቅር ማለት እጅግ ብዙ ትርጉም አለውና እርሱን አንስተን ብናወራ፣ ደጋግመን እግዚአብሄር ስለእኛ የገለጠውን የፍቅር ብርታት ብናስታውስ ሲያንስ እንጂ አይበዛም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ፍቅር እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ፍቅር እንደመሆኑ ሁሉ ይመኩበታል፣  ሁሉ ይጠጉታል፣ ሁሉም ያምኑበታል፡፡ ፍቅሩ ረቂቅና ጥልቅ …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [6..]

ለመመለስ መንቃት

የአምነት ጉዞንና የባህር ጉዞን የሚያመሳስሉ ሰዎች አሉ፤ ምክኒያታቸውን ሲያስረዱ አንድ ሰው የእምነት ጉዞን ሲጉዋዝ  አገኛለሁ ብሎ የሚጠብቀውን መንፈሳዊ ነገር ተስፋ አድርጎ እንጂ በእጁ ጨብጦ የሚጉዋዝ አለመሆኑ፣ በባህር ላይ የሚደረግ ጉዞም የሚታይ ነገር ከፊት ሳይኖር በእምነት ብቻ መዳረሻን አልሞ ወደተገመተ አቅጣጫ የሚቀዝፍበት መሆኑ ነው፤ ባህርተኛው በእምነት ከሆነ ጊዜ በሁዋላ እደርሳለሁ ወዳለው ሩቅ ስፍራ እንደሚደርስ በማሰብ የሚጉዋዝም …
Continue reading ለመመለስ መንቃት

አዲስ ኪዳን ምልክት  (2..)

​​​​​​​​የአዲስ ኪዳን ምልክት ሰው በብሉይ ኪዳን የነበረ አንድ ነቢይ በህይወቱ የተከናወነ አዲስ ልምምድ ማስተናገዱ ከግርምት ባለፈ ለትውልዱ የሚያበስረው ትልቅ ምልእክት ነበረው፡፡ ​​​​ነቢዩ ዮናስ  ይባላል፣ ይህ ነቢይ በአንድ ወቅት ከእግዚአብሄር ፊት የሚኮበልልበት ሰበብና ጥሪውን ወደ ሁዋላ የሚያደርግ ድካም ገጥሞት ነበር፤ እግዚአብሄር ግን መኮብለሉን አይቶ ሳይተወው በመከታተል እስከተደበቀበት ስፍራ እስከ ጥልቅ ድረስ ወርዶ የሚያስተምረውን እርምጃ ሲወስድበት ይታያል፡፡ …
Continue reading አዲስ ኪዳን ምልክት  (2..)

የአይን ነገር(2…)

 አይን፣ ጆሮና ልብ ተቀናጅተውና በበጎ ልቦና ቁጥጥር ስር ሆነው በህይወታችን ቢሰሩ ህሊና ውጤታማ ስለሚሆን የጽድቅ ፍሬ ያሳያል፤ ለምሳሌ አይን በተገቢው መንገድና በተገቢው ስፍራ ተገቢ ነገር እንዲያይ ቢቃኝ ከፈተና ይጋረዳል፤ ጆሮም ከሚፈትን ድምጽ ቢጠነቀቅ ልብን ከክፉ ውሳኔ ይመልሳል፣ ዛሬም ቀድሞም ከሚሰማው ያልተገባ ነገር የተነሳ ልባችን በተሳሳተ ውሳኔ ሲመራ ስለኖረ ብዙ የህይወት ውጣ ውረድ፣ ፈተናና ስብራት በሰው …
Continue reading የአይን ነገር(2…)