ያለ እውነተኛ አምላክ ኑሮ

እውነተኛ አምላክ ባልተገለጠበት ስፍራና ዘመን የሃሰት አማልክት ተገልጠው ይሰራሉ (2ዜና.15:3)።በዚያን ጊዜ አጋንንት በድፍረትና በግልጽ ስለሚንቀሳቀሱ ተጽኖአቸው ከፍተኛ ነው።የጣኦታት ወረራም ነፃነት አሳጥቶ ማስተዋል እስኪሳን ድረስ ክፋት ይነግሳል፡፡የፍጥረታት ሁሉ ጌታ ግን ፍጥረቶቹ በርሱ ጥላ ስር ተማምነው እንዲኖሩ እንጂ ባለቤት ወዳልሆኑ አማልክት ፊታቸውን እንዲመልሱ አይሻም። እውነተኛ አምላክ የሌለው ትውልድ በክፉ መናፍስት የተጠቃ እንደሆነ የንጉስ አሞጽ ታሪክ ያሳየናል፦ 2ነገ.21:19-22 …
Continue reading ያለ እውነተኛ አምላክ ኑሮ

ወደ ኢየሱስ የመጡ፣ የተሰበሰቡ

ማቴ.4:3-20 “እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም።ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ …
Continue reading ወደ ኢየሱስ የመጡ፣ የተሰበሰቡ

ከእምነት መንሸራተት

በማቴ.8:237 ውስጥ ያሉ ደቀመዛሙርት በሁኔታዎች አስቸጋሪነት ምክኒያት ልባቸው በፍርሀት ተያዘና አብሮአቸው ያለውን ጌታ እስከመርሳት ደረሱ፡-”ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀመዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፡- ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉአስነሡት። እርሱም፡- እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም …
Continue reading ከእምነት መንሸራተት

አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[1/2]

ሮሜ.8:5-12 ስለ እኛ ስለ ሰዎች ሲናገር፦ “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ …
Continue reading አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[1/2]