ስልጣንና ባለስልጣን በምድር ስርአት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ የአስተዳደር፣ የስነ-ስርአትና የሰላም አብይ መሰረቶች ናቸው።ቃሉም በሮሜ.13:1-4 ላይ ሲናገር፦ “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን …
Continue reading ባለ ስልጣን አምላክ
ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ መርገም ሲሆን)
በአለም ውስጥ ለመልካም ስራና አገልግሎት የተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በዚያው ልክ ለአመጽ ውለው ይታያሉ።ቴክኖሎጂና ፈጠራ ብዙ ተደክሞበት ለውጤት የሚበቃ ስራ ሲሆን ዋና አላማውም ኑሮን ማቅለልና ምቹ ማድረግ ነው። ነገር ግን እነርሱ ከተፈጠሩለት አላማ ውጪ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋሉ።ኑሮን ለማቀላጠፍና ለማቃለል ተፈጥረው ሳለ የሰው ልጅን መከራ ያብሳሉ።በጎ አእምሮ ያመነጨው መልካም ቴክኖሎጂ ክፉ አእምሮ ቀይሮት የክፋት መሳርያና የመርገም መሳቢያ …
Continue reading ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ መርገም ሲሆን)
የሀዋርያት ስራ መጽሀፍ – የሀይማኖቶች መከራከሪያ ሜዳ[misunderstanding the book]
በክርስትና እምነት ውስጥ የሚጠቃለሉ አብዛኛዎቹ እምነቶች የጋራ የሆኑ ወይም ብዙም የማያከራክሩ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይጋራሉ፡፡ስለዚህ ሁሎችም በሚባል ደረጃ በህግ በመዝሙራትና በነቢያት የተጻፉ መጻህፍትን (የብሉይ ኪዳን መጽሃፍትን)ያለብዙ ልዩነት ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡ከዚህ በተጨማሪ የወንጌል መጽሀፍቶችንና መልእክቶችን ጭምር ያለክርክር ያስተምሩዋቸዋል፣ያምኑአቸዋል፡፡ነገር ግን ሁሎችም በሚያስብል ደረጃ በሀዋርያት ስራ መጽሀፍ ላይ የተለያየ አመለካከትና እምነት ያንጸባርቃሉ፡፡መጽሀፍ ቅዱስ የመዘገበውን የቤተክርስቲያን አመሰራረት ያለማወላወል ከተቀበልን ዛሬ …
Continue reading የሀዋርያት ስራ መጽሀፍ – የሀይማኖቶች መከራከሪያ ሜዳ[misunderstanding the book]
ወንጌልን መቀበል
በወንጌል ጉዳይ ዋነኛ ናቸው ከሚባሉት ነገሮች መሀል በወንጌል መልዕክት ውስጥ የሚገኘውን የጌታ ደህንነት ሰው እንዴት አድርጎ እየተቀበለውና እየኖረው ነው? የሚለው ነው፡፡ታላቅና ዘላለማዊ የሆነ የአምላክ እቅድ ወደ ሰዎች ሲላክ ሰዎች አቀባበላችን እንዴት ነበር? መላእክት የጌታን መወለድ በአድናቆትና በሙገሳ ሊያጅቡ ከሰማያት ወርደዋል።ነብያት ስለዚህ መዳን በትልቁ አጉልተው ተናግረዋል።ቅዱሳን በመንፈስ ሆነው ስለእርሱ አመስግነዋል። ሉቃ1:67-75 “አባቱ ዘካርያስም(የመጥምቁ ዮሃንስ አባት) መንፈስ …
Continue reading ወንጌልን መቀበል
የቤተክርስቲያን ጥሪ[true call; true church]
ሀ.ቤተክርስቲያን የበጉ ሙሽራ እንድትሆን ዝግጁ መሆን አለባት፡፡በዚህ ዘመን ያለች ቤተክርስቲያን በተረጋገጠ የመዳን መንገድ ውስጥ መኖር ከፈለገች እውነተኞች ሀዋርያት የሄዱበትን የእምነት መንገድ መከተል እንጂ ሌላ ከንቱ ትምህርት ውስጥ መስጠም አስፈላጊ እንዳልሆነ ማስተዋልና ልብወለድ ትምህርቶችን (መናፍቃዊ ትምህርቶችን) በብርቱ መቁዋቁዋም አለባት፡፡2ቆሮ.11:2-3 ”በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን …
Continue reading የቤተክርስቲያን ጥሪ[true call; true church]
የመጨረሻ ዘመን[4/4]
3ኛው የመጨረሻ ቀን ምልክት:- ሰዎች በምኞት የተጠመዱ ይሆናሉ
ትውልዳችንን ከየትኛውም ትውልዶች በተለየ ሁኔታ ምኞት የሚያሩዋሩጠው ትውልድ ነው፡፡እንድንመኝ የሚገፋፉን ነገሮች በደጃችን ያንዣብባሉ፡፡የተለያዩ ማስታወቂያዎች አእምሮአችንን ያስጨንቃሉ፡፡የሚያጉዋጉ ነገሮች በቅርባችን አሉ፡፡የምናየውና የምንሰማው ሁሉ የሚያስጎመጅ ነው፣በቃኝን እንዳንማር ውስጣችንን ዘወትር በፍላጎት ረሃብ ይቦረቡራል፡፡በዚያ ተፅእኖ ምክኒያት ቀልባችን ከምኞቶቻችን መነሳት አይችልም፡፡እንዲያውም ሰው የሚመኘው ሀብት ለማካበትና ብር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ላይ ይሁን ከጋብቻ ውጪ ለመሴሰን ከፍተኛ ምኞት የሚንፀባረቅበት ጊዜ ነው፡፡አብዛኛው የአለም ህዝብ ትኩረት የሚያደርገው በመንፈሳዊ በረከት ላይ ሳይሆን በስጋዊ ባርኮት ላይ ነው፡፡ይህም ለመንፈሳዊ ዝቅጠት ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ጌታ ሆይ ምራኝ መባሉ ቀርቶ ህገወጥ ስራ እንኩዋን ቢሆን ያለ መሸማቀቅ ያን አድርግልኝ ተብሎ ይፀለያል፡፡”እግዚአብሄር ፀሎታችንን እንዳይሰማና ዝም እንዲል ያደረገው ምንድነው?” ብሎ ዛሬ መጠየቅ መልካም ነው፡፡ የጠላንና ያስጨነቀን ከፊታችን እንዲወገድ ብንፀልይ ምን አለበት? የቀሰፈን ቢቀሰፍ፣ ያሳፈረን ቢያፍር፣ የደበደበን ቢደበደብ እኮ ምን አለበት? ፡- እንዲያ እንመኛለን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ካላወቅን፡፡ እግዚአብሄርንም እናማዋለን ለዚህ ፀሎታችን ባለመመለሱ፡፡
በተለይ በክርስትና ስም በሚንቀሳቀሱ ሀይማኖቶች ውስጥ ሰዎች በምኞት እንዲቃጠሉ የሚገፋፉ ተግባሮችና ስብከቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም ፡-በዚህ ዘመን፡፡ “የብልፅግና ወንጌል” ከጌታ ወንጌል ተገንጥሎ በልዩ መንገድ አማኞችን በትምህርት ያናውዛል፡፡በዚህም እግዚአብሄርን የሚፈልጉ ትኩረታቸውን ወደ ምድራዊ ጥሪት መመኘትና ማለም ውስጥ እንዲሰጥሙ መንገድ ከፋች ሆኖአል፡፡
እስቲ በእውነት እንጠይቅ፡-እግዚአብሄር ለምን አትመኝ አለ? በአጭሩ ምኞት የመውደቂያችን ወጥመድ በመሆኑ!
መዝ.106:12-17 ”በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ።ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም።በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።የለመኑትንም ሰጣቸው፤ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።”
4ኛው የመጨረሻ ቀን ምልክት፡- ሰዎች ትምክህተኛና ኩራተኞች ይሆናሉ
ኩራት ሰይጣንን ከነበረበት የክብር ስፍራ ያስወገደ ምክኒያት ነበር፡፡በእግዚአብሄር ፊት መኩራት ውድቀትን እንደሚያስከትል ካስተዋልን በመጨረሻው ዘመን ሰዎች በእግዚአብሄር ፊት ኩራተኞች ናቸውና ይህ ውድቀታቸውን እያፋጠነ እንደሚገኝ መመልከት እንችላለን፡፡
በዚህ ዘመን ያለ ዝንባሌ እኔነት የሞላበት በመሆኑ በዚያ ውስጥ መመካትና መኩራት የሚንፀባርቅበትና የእኔ ይሁንልኝ በሚል ዙርያ ትኩረት ያደረገ ግለ-ሰባዊነት የሚታይበት ነው፡፡በሰውም በእግዚአብሄርም ፊት ኩራትን ማንፀባረቅ፣ በሚያስፈልግ ጊዜ ለሰው ከመድረስ መራቅ፣ ራስን ስለሰው ከመስጠት መቆጠብ ሁሉ የዚያ ስሜት ነፀብራቅ ነው፡፡የእኔነት ስሜት ”እኔን እዩ፣እኔን ብቻ ስሙ ወይም እኔን በማንኛውም ምክኒያት ከፍ አድርጉ፣ እኔን ተከተሉ…” ወዘተ አለበት፡፡ይሄን ስሜት ለማጀብም የሚገለጠው ባህሪ ትምክህት ወይም ኩራት ይሆናል፡፡
በኩራትና በትምክህት መንፈስ ሲጠመዱ በአለባበስና በኑሮ ዘይቤ ወጣና ጎላ ብሎ ለመታየት ጥረት ይደረጋል፣ የሰውነት ክፍልን የሚያስቆጥር የተወጣጠረ ልብስ መልበስ፣ በአካል ቅርፅ የተሻሉ እንደሆኑ ለማሳየት መድከምና ሰዎች በዚያ ታይታ በምኞት እንዲሳቡና ምንዝርን እንዲመኙ ለማድረግ መጣጣር አለበት፡፡ይህም በዚህ ዘመን ከህፃን እስከአሮጊት ያለ ሀፍረት የሚከናወን እሽቅድምድም ነው፡፡ምርጥና የተደነቀ መኪና መንዳት፣ እጅግ የተቀናጣ ቤት መገንባት፣ ሰዎች እነሱን ከሌሎች ከፍ አድርጎ ሊያሳይ የሚችልን ነገር ሁሉ መሸመት… የዚህ ዘመን አብይ መገለጫ ነው፡፡በዚህች አለም ላይ የአለምን ትልቅ ገፅታ ለአለም ነዋሪዎች በገዛ ማንነት ላይ እየሞከሩ ለማሳየት መድከም የተያዙበትን መንፈስ አመልካች ብቻ ሳይሆን ይህችን ምድር ብቻ ተስፋ በማድረግ በርሱዋ ላይ ሀሳብን እየጣሉ ስለመሆኑ አመልካች ነገር ነው፡፡
5ኛው የመጨረሻ ቀን ምልክት፡- ልጆች ለወላጆች አይታዘዙም
በዚህ ዘመን ልጆች ወላጆች እንዲሰሙዋቸውና ለስሜቶቻቸው ታዛዥ እንዲሆኑ የሚጫኑዋና አዛዦች ሆነዋል፡፡”ኸረ ልጄ እንዳያዝንብኝ፣ አይ እሷ እንዳታኮርፍ ፈራለሁ ወይም ተዉ ልጆቼ ቁጣን አይወዱም” የሚል ትህትና የሚመስል ነገር ግን የልጅን የወደፊት አቅጣጫ የሚያጣምም የቤተሰብ አስተሳሰብም አለ፡፡ልጆችን መቅጣት ወይም በተግሳፅ መመለስ የማይታሰብ እስኪመስል ድረስ የልጆች የበላይነት ከፍ ብሎ፣ ወላጆች ደግሞ ይህን መንፈስ ተቀብለነው ያልያም ተሸንፈንለት በዘመኑ ውስጥ አንድ የአመፅ መንገድ በራሳችን ፈቃድ ከፍተን እንገኛለን፡፡
ቤተሰቦች በራሳቸው ቸልተኝነት ምክኒያትና በልጆቻቸው መረንነት አንገት ደፍተው ብቻ የሚቆዝሙበት ጊዜ ነው፡፡ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ አንዳንድ ወላጆች የእግዚአብሄር ትእዛዝ የሚወጣው ልጆችን ብቻ የሚመለከት አድርገው ነው፡፡እውነቱ ግን ያ አይደለም፡፡እግዚአብሄር ልጅህን የምትወደው ከሆነ ቅጣው ሲል መውደድ የሚለው የፍቅር ግዴታ ወደ እነርሱ እንደሚጠቁም ማስተዋል አለባቸው፡፡ጥቅሱን ለራሴ ልውሰድና በዚያ እኔም ተጠያቂ እንደሆንኩ እያሰብኩ ቃሉ በህይወቴ ተሳክቶ እኔም ልጄም እስክንተርፍ በፀሎትም በተግሳፅም መትጋት አለብኝ ማለት ነው፡፡
በሌላ በኩል ልጆችን በተለያዩ ነገሮች እየሞሉ እዚህ ያደረሱ ወላጆች ብቻ ሳይሆኑ የሚዲያ ተፅእኖዎችም ናቸው፡፡ልጆቻችንን ከዚያ ተፅእኖ ለማውጣት እንዴት እናድናቸው ብለን በሚገባ ማሰብና መትጋት፣ ከልጆቻችን ጋር በግልፅነት መመካከርም ጭምር አለብን፡፡
የሌሎች ሀገሮች የባህል ወረርሽኝ በቲቪ፣ በፊልምና በመፅሄት ስለሚገባ ያንን የሚያዩና እርሱን ለመኖር የሚለማመዱ ወጣቶች በዘመናዊነት ስም የማንነት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል፡፡የእግዚአብሄር ልጆች በዚህ የትውልድ ጥቃት እንዳይጎዱ ወላጆች ልጆቻቸውን በእግዚአብሄር ቃል ማስተማር፣ መምራት፣ ሲያስፈልግ መገሰፅና ሁሉን ጠቃሚ መንገድ በመጠቀም የማዳን ስራ ላይ እንዲጠመዱ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቤተሰብ ግንኙነት አንፃርም ከእግዚአብሄር ፈቃድ ውጪ የሆነን የወላጅና የልጅ ግንኙነት የሚፈጥሩ አካሄዶችን ማቆም ያስፈልጋል፡፡ራስ መግዛትን እንዲማሩ የልጆች አእምሮ ውስጥ ተቀርፆ የሚቀር ትምህርት ያስፈልጋል፡፡ለማህበረሰቡ በተለይ ለአዛውንቶች ክብር እንዲሰጡ፣ በሁሉ ታዛዥ እንዲሆኑና ትሁትና እውነተኞች ሆነው እንዲያድጉ የቤተሰብ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡
በመጨረሻው ዘመን ልጆች ያልተገቡ ድርጊቶች ማሳየትና ክብር የሚባል ስሜት ያለመኖር ይታይባቸዋል፡፡ ይህም እግዚአብሄርን ያለመፍራትና ያለማወቅ ውጤት ነው፡፡እግዚአብሄርን የሚፈራ ቤተሰብ ሁሌም የእግዚአብሄርን ትእዛዝ ለልጁ ስለሚያሳውቅ ለመልካም ማህበረሰብ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ ቴክኖሎጂው፣ ሳይንስና እውቀቱም እግዚአብሄርን የሚከልል ቁሳዊ ግኝት እየሆነ በማስቸገሩ በዚያ ውስጥ ተጠምደው የሚውሉ ለእግዚአብሄር፣ ለቃሉና ለወላጅ መታዘዝን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዳያዳብሩ ከፍተኛ መሰናክል ይፈጥራል፡፡ ወላጆች ግን ይህን ፈተና በአሸናፊነት ይሻገሩ ዘንድ ልጆቻቸውን በትጋት በክትትልና በጥንቃቄ ሊያሳድጉዋቸው ያስፈልጋል፡፡
1ጴጥ.5:5 እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
የታመነው ዜና
ወንጌልን እጅግ አስተማማኝ፣ውብና አስደሳች ዜና ያደረገው በጌታ ኢየሱስ የሆነው ጸጋና እውነት በውስጡ በመገለጡ ነው፡፡የጌታ ኢየሱስ ወደ ምደር መምጣት ከመንፈስ አለም ሳይቀር የምስራች ነጋሪዎችን የጋበዘ ነበር፡፡ እነዚህ እንግዶች መናፍሰቶች ቢሆኑም ለሰው ልጅ ተስፋ የሆነ ዜና ስለያዙ ያን የታመነ ዜና ያበስሩ ዘንድ ወደ ምድር ወረዱ፡፡ ስለዚህ ያኔ እንዲህ ሆነ፡- ” በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ …
Continue reading የታመነው ዜና
እርሱ ጠባቂዬ መጋቢዬም ነው
ሰው የአምላኩን ቸርነት ያውቅና ስጦታውን ይቀበል ዘንድ የእግዚአብሄርን አሳብ ማስተዋል እንደፈቃዱም እርሱን መፈለግ ይገባዋል።ነገር ግን ሁላችን ያን ልናደርግ ባለመቻላችን ከዚያም በላይ ደግሞ እንድናገኘው ፍላጎት ባለማሳየታችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ሰጪው እንዳያመለክተን መቀበል የነበረብንንም የርሱን በጎ ስጦታ በአንድነት እንድናጣ አድርጎአል።በመጽህፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የእግዚአብሄርን ባህሪ ጠንቅቆ የተረዳው ንጉስ ዳዊት ግን እግዚአብሄርን በመፈለጉ የተቀበለውን መንፈሳዊ በረከት በመዝሙሩ ገልጦታል፦ …
Continue reading እርሱ ጠባቂዬ መጋቢዬም ነው
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
መዝ.23:3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። ነፍስ ከየት ወዴት ተጉዛ ወዴት ትመለሳለች? ወይስ ምን የሚያሳስባት ጉዳይ ቢገጥማት ከመንገድዋ ፊትዋን ትመልሳለች? በነፍስ ጉዳይስ የሚያሳስብ ጉዳይ ምን ኖሮ መመለስን ትመርጣለች? መቼም ቢሆን ከተቃናልን የህይወት እርምጃ መመለስ፣ከተሳካልን ድል ወደ ሁዋላ ማለት፣ከተጉዋዝንበት ርዝመት ያለው መንገድ ማፈግፈግ ወይም የማስጠንቀቂያ ደውል ሰምተን የእኛ የምንላቸውን ለመሸሸግ ሙከራ ማድረግ፣ እንዲህ ቀላል …
Continue reading እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
የእውነት እውቀት[3/3]
1.4 የወንጌል መጽሀፍት ስለኢየሱስ ሕይወት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ፣ ደቀመዛሙርት የእርሱን ወዲያው መመለስ ይጠባበቁ ነበር፣ በህይወት እያሉ እንደሚከሰት ገምተው ነበርና፡፡በዚህም ምክንያት ለወደፊት ትውልዶች የሚሆን የጽኁፍ መረጃ ለማስቀመጥ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው ቀረ፡፡ ነገር ግን የዐይን ምስክሮች እየሞቱ መሄድና የቤተክርስቲያን የሚስዮናውያን ተልእኮ ፍላጎት እያደገ ሲሄድ፣ የክርስትና መሰረት የሆነውን ጌታ ህይወት እና ትምህርቶች በፅሁፍ ማስፈር …
Continue reading የእውነት እውቀት[3/3]
