ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

ሐ.የጌታን ምርጫ በተመለከተ፡-እነርሱን ብቻ እንድንሰማ ጌታ እንዳዘዘ ማስተዋል ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጅ በሙሉ ለእነርሱ የወንጌል ስብከት ክብር እንዲሰጥ አጥብቆ ወደ እኛ ትእዛዝ ስድዶአል፡፡ ሉቃ10:16 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።”ሲል ተናግሮአል፡፡ ይህን ጥቅስ ካስተዋልን ጌታ ኢየሱስ እኔን የሚሰማ እናንተን ይሰማል አላለም፣ለምን? የጌታ ፍቃዱ በመረጣቸው ሀዋርያት አድሮ መስራት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

የመጨረሻ ዘመን[3/4]

2ኛው የመጨረሻ ቀን ምልክት:- ሰዎች ከእግዚአብሄር ይልቅ ገንዘብና ተድላን ይወዳሉ በሰዎች  ዘንድ (በተለይ በዚህ ዘመን)የምንኖረው ህይወት ሙሉነትመለኪያ የተድላ ጣርያ ወይም ከፍታውናየስኬቱ መጠን  ማደግ ነው፡፡ለአለም ሰዎችገንዘብና ንብረት ካለ ህይወት ሙሉ ነው፡፡በዚህ አስተሳሰብ ምክኒያት ብዙዎችለተድላ ህይወት ከምንም በላይ ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ያንን ለማግኘትም ማንኛውንም መስዋእትነት ይከፍላሉ(ገላቸውን ይሸጣሉ፣ሰውን ለገንዘብ ይገድላሉ፣ባልሰሩት ስራ ጉቦ ይበላሉ፣የሰው አካል ሰርቀው እስከመሸጥ ይደርሳሉ…ሌላም ሌላም)፡፡ በሌላ …
Continue reading የመጨረሻ ዘመን[3/4]

ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]

ረ. የሀዋርያቱን የማይለወጥ ወንጌል በተመለከተ፡-ከእነርሱ ሌላ ወንጌልን አሻሽሎ የሚያቀርብ ቢኖር ሰማይ የሚቀበለው ሳይሆን እርግማን እንደሚያስረው ስለምታስተውል ነው፡፡ ሀዋርያቶች በመልእክቶቻቸው ውስጥ አጥብቀው ካነሱት ርእስ መሀል የሀሰት ትምህርት አንዱ ነበር፡፡ከሰውና ከአጋንንት የፈለቀ የሀሰት ትምህርት ከጌታ የተቀበሉትን ትምህርት እንደሚበርዝ አስቀድመው በመንፈስ ስላስተዋሉ አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ገላ.1:7-8 “እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።ነገር …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[2/3]

​​​​​​​​መዝ.23:2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። አምላካችን ማሰማርያ መስክ ያለው አምላክ ነው፡፡መስኩ ማረፍያ ያለው ፣ ምግብና መጠጥም  የተሞላ ስለሆነ የአቅርቦት አጥረት ከቶ አያጋጥመውም፡፡የመስኩ ባለቤት የመስኩን ልምላሜ ይቆጣጠራል፣ባእዳን ረግጠው እንዳያረክሱት ዘወትር ያጠራዋል፡፡በመስኩ ላይ የሚሰማሩ በጎች ባለቤታቸው አንድ ብቻ በመሆኑ የእርሱን ድምጽ ይለያሉ፣ምሪቱን ያስተውላሉ፡፡የእረፍት ውሀ በጎቹን በመስኩ ላይ በእረፍት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ያለ ፍርሃትና ጥርጣሬ ይጸኑ ዘንድ …
Continue reading እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[2/3]

የእውነት እውቀት[2/3]

1.2 ወንጌል ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ ስራና ትምህርት የተፃፈ ዘገባ: ​​​​​​በዮሐ.21:24-25 ውስጥ ቃሉ ሲናገር “ስለ እነዚህም የመሰከረ ይህንንም ጽፎ ያለ ይህ ደቀ መዝሙር ነው፥ ምስክሩም እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።​​​​​​​ ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።” ይላል፡፡በእርግጥ ወንጌል ብቸኛው የክርስቶስ ስራ የመረጃ ምንጭ ነው፡፡በየእለቱ፣በየሰአቱ፣በየደቂቃውና፣በየሽርፍራፊው ጊዜ ሳይቀር የሰራው …
Continue reading የእውነት እውቀት[2/3]

የመጨረሻ ዘመን[2/4]

በመጨረሻው ቀን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስቸጋሪ ባህሪያት እንደሚመጡ እንዲህ በግልጥ ተነግሮአል፡፡እነዚህ ባህሪዎች በእኛ ትውልድ ውስጥ እየታዩ ካሉት ጋርሲነፃፀሩ ምን ይመስላሉ? በእኛ በራሳችን ላይ አየነገሰ ያለ ነገር ምንድነው? እውነተኛ ሆነን ራሳችንን ስናይ ከእኛ መወገድ የሚገባው አላስፈላጊ ነገር እንዳለ ይታየናል?  ምልክቶቹ በስፍራና በፆታ ስለማይለያዩ እንደ ትውልድ በአንድነት እንደ ግለሰብም እያንዳንዳችን ነገሩን አስተውለን እንድንጉዋዝ እንዲሁም በእነዚህ አስጨናቂ ባህሪዎች አንዳችንም …
Continue reading የመጨረሻ ዘመን[2/4]

መዝ.23:1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[1/3]

እውነተኛ እረኛ ወደ በረቱ በበሩ የሚገባ ነው፡፡ሾልኮ የሚገባ ወንበዴን ይከላከላል፡፡ሌባው እንዳያገኘንና በመንገድ፣ እንዳንቀር አወጣጥና አገባቡን የሚያሳየን አርሱ ብቻ ነው፡፡እውነተኛ እረኛ ድምጹን ያሰማና በጎቹን ያነቃል፡፡የበጎች እረኛ በህይወት በር በመግባት ወደ መኖርያችን በደህንነት ያስገባናል፡፡በልባችን ያድራል፡፡ያኔ ልባችንን ወደ እረፍት ያቀናዋል፡፡ወደ ቀናው የህይወት ስርአት ሊያመለክተን በእርሱም እንድንኖር ያጸናናል፡፡   እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡እንዲያ በመሆኑ ከእርሱ ብዙ ይደረግልናል፡፡ለምሳሌ፡- ስጋችንና መንፈሳችን የሚያስፈልጋቸውን …
Continue reading መዝ.23:1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[1/3]

የእውነት እውቀት[1/3]

  1.1 ወንጌል የኢየሱስን መወለድ ያበሰረ የደስታ ዜና፡፡ የምስራች! አስደናቂና ታላቅ የሆነ ዜና፣ የሰው ልጆችን በደስታ የሚሞላ ብስራት  በጌታ መወለድ ምክኒያት በምድር ላይ ወጥቶአል፡፡የጌታ ኢያሱስ የመወለድ አዋጅ በመላእክት በኩል የተነገረ ነበር፡፡ይህም የእግዚአብሄር ፈቃድና ፍቅር ለፍጥረት ሁሉ የመገለጡ ምስራች ሲሆን አለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሄር አቅዶ በእርሱ ዘንድ የጠበቀው፣ ቀኑና ዘመኑ ሲደርስ ከእግዚአብሄር የወጣ የደህንነት አዋጅ ነው፡፡ያም …
Continue reading የእውነት እውቀት[1/3]

የመጨረሻ ዘመን[1/4]

በእኛ ትውልድ መሀል የሚታዩና በየወቅቱ እየተገለጡ በማስጨንቅ ላይ ያሉ የመጨረሻ ዘመን ምልክቶች ብዙ ናቸው፡፡እያስጨነቁን ያሉ እንደ ረሀብ፣ጦርነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የእውቅት በፈጣን ሁኔታ መጨመርና ክህደት መብዛት ከመቼውም ይልቅ ተፅእኖ እያደረጉብን ነው፡፡ የአየርና የውሀ ብክለት ከፍተኛ በመሆኑ ሰዎች በዚያ ይሞታሉ፣ በአየር የሚበሩ አእዋፋትና በውሀ ውስጥ የሚኖሩ አሳዎችም በከፍተኛ ቁጥር ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ጎርፍና ማእበል፣ድርቅና ረሀብም በየሀገሩ ስለሚያዘወትሩ ብዙ …
Continue reading የመጨረሻ ዘመን[1/4]