ባለን ልዩ ልዩ አስተሳሰብ ምክኒያት ሰዎች ጊዜያዊውን ምድራዊ ኑሮ ዘላለም እንደሆነ በመቁጠር እንኖረዋለን። እንዲያ በመሆኑም እቅዳችን ከልክ ያለፈና የተለጠጠ ነው።መዘናጋትም ይታይበታል፡፡ በጊዜያዊው አለም ዘላለማዊ የሚመስል እቅድ ውስጥ መዘፈቅ ትክክለኛ ምርጫን መዘንጋት ይፈጥራል፡፡ ቁዋሚና ዘላለማዊ ነገር ምድር ላይ ሳይኖር እኛ ግን በራሳችን ዙሪያ እንደዚያ የመሳሰሉ እቅዶችን ስናስቀምጥ በጊዜያዊ የምድር ኑሮ ዘላለማዊንትን ልንገነባ እየሞከርን ነው ማለት ነው፡፡ …
Continue reading ጊዜያዊ ዘላለማዊነት
ከእግዚአብሄር ፊት መሸሽ
ሀጢያት ስንሰራ ከጻድቁ አምላክ ፊት እንሸሻለን፡፡ ሀጢያት ያሳድዳል፣ ሂድ ሂድ ጥፋ ተሰወር ይላል፡፡ የምህረት በር እንዳናይ አድርጎ የሽሽት ቁለቁለት ላይ ያኖረናል፡፡ ከእግዚአብሄር ፊት የሚሸሹ ሁሉ ስብራት ላይ ይወድቃሉ፡፡ መሸሽ ከእግዚአብሄር ክልል ያስወጣል፡፡ አዳም ከእግዚአብር ፊት በሸሸበት ቀን ከኤደን ገነት እስከወዲያኛው ተባረረ፡፡ከመልካም ነገር በራቅን ቁጥር እየለቀቀን የሚሄድ የእግዚአብሄር መልካም ነገር ብዙ ነው፡፡ ዘፍ.4:9-16 ”እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፡- …
Continue reading ከእግዚአብሄር ፊት መሸሽ
ሹመኛ መንፈሳዊ አካል[The appointed body]
በእግዚአብሄር ዘላለማዊ እቅድ ላይ የሚመጣ ብዥታ ቤተክርስቲያን ማንነትና ተልእኮ ላይ ተጋብቶ ተመሳሳይ ብዥታ እንዲፈጠር ያደርጋል። የእግዚአብሄር እቅድ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተሻጋሪ ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ ያለው እቅድ ለሰው ልጅ ያለውን አሳብ የያዘ ነው፡፡ በሚመጣው እያንዳንዱ ትውልድ ያን ዘላለማዊ እቅድ በመግለጥ የሰው ልጆች በእቅዱ ውስጥ እንዲገቡ ይጋብዛል፣ ኑ ብሎ ወደ እርሱ ይጠራል፡፡ በሰማይ ያለው እቅዱን ሊገልጥ ሲመጣ …
Continue reading ሹመኛ መንፈሳዊ አካል[The appointed body]
ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ በሃገር ላይ መርገም ሲሆን)
አንድ አገር እየሰለጠነች ስትሄድ በዚያው ልክ ለማህበራዊ እሴትዋ ካልተጠነቀቀች እጅግ ስር በሰደደ ማህበራዊ ቀውስ ትመታለች። ቴክኖሎጂና ስልጣኔ የእውቀት ሽግግር ብቻ ሳይሆን የመጥፎ ባህል ተስቦ መተላለፊያ መንገድም ነው። ባእድ አምልኮና ያልተለመደ ወግ አንድን ሃገር እንደ በረሃ አንበጣ በጥቂት ወቅት ሊያጥለቀልቅና ሃገራዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል። ዋጋ መሰጣጣት፣ መከባበርና መተሳሰብ የሚቀዘቅዘው ማህበረሰቡ ያካበተውን ማህበራዊና መንፈሳዊ ሀብቶች በስልጣኔ አመካኝቶ …
Continue reading ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ በሃገር ላይ መርገም ሲሆን)
የለጋስ ስጦታ
1.በጎ ሥጦታ ስጦታ ከለጋስ አካል የሚወጣ ጥቅም ሆኖ በሰጪው ቸርነት ላይ የተመሰረተ የመስጠት እንቅስቃሴ ነው። ስጦታ ለሰጪውም ለተቀባዩም የሚያስደስት እንድምታ አለው። ማንም የሚሰጥ አካል አምኖበት የሚሰጥ ሲሆን ተቀባዩ ክብደት ሰጥቶ ሰጪውን የሚያከብርበት አጋጣሚ ነው። አንድ ሰጪ ለሌላው ተቀባይ እንደዚህ ባለ መንገድ ስጦታ ሊሰጠው ይችላል። እግዚአብሄር ሊባርክ ይሰጣል ዘፍ.17:15-16 ”እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ …
Continue reading የለጋስ ስጦታ
ከራስ ሽሽት
አንዳንዴ ከራስ በሚመነጭ ፍላጎትና አስጨናቂ ስሜት፣ እረፍት ከማይሰጥ አሳብ፣ ከሰው ከሚመጣ ግፊት ያልያም የሁኔታዎች መወሳሰብ በሚፈጥረው አለመመቸት ጥብብ ጭንቅ ሲለን መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ለመዝለል በሚል የምንሄደው አደገኛ አካሄድ አለ፡፡ ነገሩ ጎልቶ ሳለ እርሱን ላለማየትና ላለመስማት እንሞክራለን። እስጨንቆ የሚገፋ ሀይል እስከማናቆመው ድረስ ወጥሮናል፣ እናም አሳሳቢነቱ ስለሚሰማን መፍትሄ በምንለው መንገድ እንሄዳለን። የሆነው ያ የማንፈልገው ውጤት ህሊናችንን …
Continue reading ከራስ ሽሽት
የአምልኮ ንጥቂያ[Faith in the worldly way]
ብዙ ሰዎች መንፈሳዊነትን በሚጋፋ የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ራሳቸውን አስገብተው ሳለ ያሉበት ጭልጥ ያለ አለማዊነት ምንም ተጽእኖ እንዳላደረገባቸው ሆነው መንፈሳዊነትን ያለ ችግር ሊኖሩት እንደሚችሉ ለአለም ሊያሳዩ ይሞክራሉ፡፡ዝናቸውን የምንሰማው ዘፋኞች፣ቁማርተኞች፣ሞዴሊስቶች፣ በውጪው አለም ደግሞ እጅግ አስደንጋጭ በሆነ ክፉ ተግባር ውስጥ ያሉ ሰዎች ወደ ቤተ-አምልኮ ሲያዘወትሩ ወይም ፕሮግራሞችን ሲካፈሉ በሚዲያ መስኮት የምናየው ነው፡፡ታዲያ እኛም ያንን እንመለከትና በውኑ ዝነኞች በአምልኮ …
Continue reading የአምልኮ ንጥቂያ[Faith in the worldly way]
ራስን የመጣል ስልጣኔ[1/2]
የመጨረሻው ዘመን ስልጣኔ ፣ቴክኖሎጂ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ህይወት ወዘተ ከፍታ ላይ ሆኖ የሚታይበት ዘመን ነው፡፡ሰው ተራርቆ መኖር ያበቃበት፣አንዱ ጉዋዳ የሆነው ጊዜ ሳይፈጅ ሌላው ጆሮ ድረስ ፈጥኖ ተጉዞ የሚሰማበትና ድርጊቱ በማስረጃ የሚተላለፍበት፣ የኑሮ ውጣውረዶች እጅግ ተቃልለው በብዙ መልኩ ትውልዱ የተመቻቸ ኑሮ የቀረበለት ዘመን ነው፡፡ገንዘብ አይጠር እንጂ ቴክኖሎጂ በእጅ ነው፡፡የስልጣኔስ ነገር? ስልጣኔ እንደ ቴክኖሎጂ ውጤት ከፋብሪካ ተመርቶ አይወጣም፡፡ስልጣኔ …
Continue reading ራስን የመጣል ስልጣኔ[1/2]
ህይወት የሚገኝበት ትምህርት
ዕብ.10:19-20 “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥…“ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን የከፈተው አንድ ብቸኛ መንገድ ህይወት ያለበት መንገድ ነው።ህያው መንገድ ህያው አምላክ የሚገለጥበት አዲስ የህይወት ስርአት ነው።ህያዋን የሆኑ በመንፈስ የተወለዱ ነፍሳትም ይመላለሱበታል።ህያዋን የሆኑ እነዚህ መንፈሳውያን ከመንገዱ ሳይለቁ ጸንተው እንዲኖሩ እግዚአብሄር የህይወት ትምህርትን ይገልጥላቸዋል።ህይወት የሚገኝበትን …
Continue reading ህይወት የሚገኝበት ትምህርት
የቀጠነው መንገድ ለዚህ ዘመን
ማቴ.13-14 “በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።” የእግዚአብሄር ቃል ከሚገልጠው መንፈሳዊ መንገድ መሃል ቀድሞ የምናገኘው ትልቅ መንገድ ተብሎ የተጠራውን ነው። የመንገዱ መጠን በትልቅነቱና በሚያስተናግደው መንገደኛ ብዛት ተገልጦአል። ይህ መንገድ ትልቅ ይሁን እንጂ ለሰው ልጆች ጥንቃቄ …
Continue reading የቀጠነው መንገድ ለዚህ ዘመን
