የፍቅር ግዛቶች [1…]

የፍቅርን ጉልበት ሊረታ ማን ይችላል? በሀይል ያልተደፈረ ጀግና ስለፍቅር እጅ ሲሰጥ በሶምሶም ታሪክ ውስጥ የምናየው ነው፤ የህዝብ ታላላቆችም ቢሆኑ በክፉ ቀን ስለሚመሩት ህዝብ ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡ በእስራኤል ነገስታቶች ታሪክ ውስጥ እናያለን፤ ወዳጆችም ስለባልንጀራቸው ፍቅር ሲሉ አክብረው የያዙትን አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ዮናታን ለዳዊት እንዳደረገው፡፡ይህ ሁሉ የሚሆነው በፍቅር የማስገደድ ጉልበት ምክኒያት ነው፡፡ ፍቅር ስጋዊ አይንን ከራስ ወዳድነት …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [1…]

እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]

የተሳሳተ ሀይማኖት ለምን ከመሰለኝ ይነሳል? መሰለኝ የስህተት መፈልፈያ ዋሻ በመሆኑ ነው፤ የጥርጥር መሰረት በመሆኑም የተሳሳተ ሀይማኖት ያስፋፋል፡፡ ሀይማኖቱ በሚመስል እውቀት ላይ በመመርኮዙና ግምታዊ ድምዳሜን በመቀበሉ ምክኒያት መንገዱን ይስታል፡፡ ቀጥ ብሎ ማደግ በሚገባው ወቅት ተንጋድዶ ከፍ ይላል፣ ከነአመሉ እንደተወላገደ ሽቅብ ይሄዳል፣ ያለእርምት ይጎለምሳል፣ ስርም ይሰዳል፣ በመጨረሻ ግን ማምለጥ በማይችለው የስህተት ወጥመድ ላይ ይቆማል፣ ይነከሳል፡፡ በተለይ ግምታዊ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]

ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]

ባላንጣዎች ሁሌም በቅራኔ ውስጥ ያሉ ወገኖች ናቸው፡፡በውጊያ ሜዳ ይገናኙ እንጂ ከመፋለም ወደሁዋላ አይሉም፡፡አሸናፊ ለይቶ አንዱ ለሌላው እጅ ሳይሰጥም ፍልሚያው አያቁዋርጥም፡፡ በሁለቱም ተዋጊዎች በኩል በየጊዜው ለውጊያ ዝግጅት አለ፤ ላለመሸነፍ እጅ ላለመስጠትና ላለመገዛት ትግል አለ፡፡የተያዘም እንዲሁ ያመልጥ ዘንድ እስከሞት በሚደርስ ትግል ሳያቁዋርጥ ለነጻነት ይታገላል፤ ይህ የውጊያ ተፈጥሮ ነው፡፡ ውጊያ መንፈሳዊም ስጋዊም ነው፡፡ ስጋዊ ውጊያ በማይግባቡ፣ በተጣሉና ጦርነትን …
Continue reading ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]

ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ በተባለበት አለም ውስጥ ስኖር ምን መስማት እንዳለብኝና እንደሌለብኝ ማስተዋል የለብኝምን? ለመንፈሳዊ ህይወቴ እንድጠነቀቅ የሚያሳስበኝ አምላክ የድምጾችን ምንጭና አቅጣጫ እንዲሁም ይዘትና ተጽእኖ ስለሚያውቅ ለእኔ ደካማ ሰው ጥንቃቄ ሲል ይህን ማሳሰቢያ አስተላልፎአልና፡፡ አለማችን ውስጥ የተለያየ መንፈስ ያላቸው ድምጾች ቢያንስ ቢያንስ በየሰከንዱ ይፈጠራሉ፤ ሰው ጆሮ የሚደርሱ፣ ተጽእኖ ያላቸውና የሰውን አስተሳሰብ ሊጫኑ የሚችሉ ድምጾችን እንደሰማሁ በግርድፉ …
Continue reading የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]

የአዲስ ኪዳን ህያው አገልግሎት [2/2]

ከጌታ ሞት፣ ትንሳኤና እርገት አስቀድሞና ደቀምዛሙርት ለአገልግሎት ሳይወጡ በፊት አስፈሪ ስብራት በይሁዳ ላይ ወድቆአል፡፡ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ላይ እግዚአብሄር ይበልጥ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገና ወንጌል መሰበክ ሳይጀምር ታየ፤ ይሄ ክስተት በደቀመዛሙርቱ ዘንድ ይበልጥ ፍርሀትን፣ ጥንቃቄንና የእግዚአብሄርን ፊት ወደ መፈለግ አምጥቶአል፡፡የሁለቱን ኪዳኖች አገልግሎት በተመለከተ ግን ሀዋርያው ጳውሎስ እያነጻጸረ የሚገልጠው ምስጢር አለው፣ እንዲህ ይላል፡- 2ቆሮ.3:5-17 ”ብቃታችን ከእግዚአብሔር …
Continue reading የአዲስ ኪዳን ህያው አገልግሎት [2/2]

እንደመሰለኝ ቢሆን[2…]

የመሰለንን ማድረግ በኑሮአችን ውስጥ የተለያየ ውጤት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ስለአንድ ነገር ገምቼ እንደመሰለኝ ቢሆንና የገመትኩት ቢፈጠር ቢያንስ አስቀድሜ የጠበቅኩት ሆኖአልና በግምቴ ትክክለኝነት እመካለሁ፤ ደግሞም ነገሮች ከመሆናቸው አስቀድሜ መገመቴ ከቻልኩ ከአስቸጋሪ ሁኔታ ማምለጫ አገኝበት ይሆናል፣ ግምቴ ቢሳሳት ግን ተቃራኒ ውጤት ይፈጠራል፡፡ እርግጥ ነው ጥሩ ገማች አለም ትፈልጋለች፡፡ ይሄም በቦታው ተገቢ ነው፡፡ እንደ አየር ሁኔታ ትንበያ የመሳሰሉ ተግባሮች …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[2…]

የጠፋው ልጅ ሰቆቃ

የጠፋሁት ልጅ ነኝ፤ የኮበለልኩና የተራቆትኩ፣ ርቄ ተጉዤም በዚያው የተሰወርኩ ነኝ፣ራሴን በእርያዎች መሀል ደብቄ ከመልካሙ አባቴ የተገለልኩ አመጸኛ፡፡ዛሬ በዚያ ባለሁበት ሆኜ አባቴ ሊያየቸው እንኩዋን ከሚጸየፋቸው ጋር ተወዳጅቻለሁ፡፡ማድረግ የሌለብኝን እያደረግኩ በመኖር ላይም እገኛለሁ፡፡ ለዛሬ ኑሮዬ የዳረገኝ እምቢተኝነቴ ሲሆን ያ ያለመታዘዜ ምክኒያት ሆኖ ከአባቴ ለይቶ አርቆኛል፡፡ የመጣሁበት አገር ኑሮ ገና ከሀገሬ ሳልነሳ በፊት እንደገመትኩት አልሆነልኝም፡፡ ከባእድ አገር አመል …
Continue reading የጠፋው ልጅ ሰቆቃ

በኮሬብ ተራራ ቁም (2/2)

•ኮሬብ ተራራ — የእግዚአብሄር ቅባት መቀበያ ተራራ ከቀርሜሎስ ተራራ የወረደው ኤልያስ ምን ገጠመው? በዚያ ተራራ እግዚአብሄርን አምልኮ ነበር፤ እሳት ከሰማይ ወርዳ ታምራት ሲሆንም ተመልክቶአል፤ የህዝቡ ልብ ወደ አምላኩ ሲመለስና የአጋንንት ሰራዊቶች (የበአልና የአጸድ ነቢያቶች) ከህዝቡ መሀል በእጁ ሲደመሰሱ እርሱ ራሱ አይቶአል፤ በጸሎቱም ምድሪቱ ላይ ከሶስት አመታት ድርቅ በሁዋላ ከባድ ዝናብ ያዘነበውን ታምራት ተቀብሎአል፡፡ ወዲያው ግን …
Continue reading በኮሬብ ተራራ ቁም (2/2)

የአገልጋይ ስብራት[1/2]

በእግዚአብሄር ፊት በአገልግሎት በቆሙ ሰዎች ላይ ከተፈጠሩት ስብራቶች አንደኛው አስደንጋጭ ክስተት ኦዛ ላይ የደረሰው ስብራት ነበር፡፡ኦዛ በእግዚአብሄር ታቦት ፊት እየሄደ ባለበትና በደስታ እግዚአብሄርን በሚያገለገልበት በዚያች ወቅት ድንገት በስህተት የፈጸመው ድርጊት በመላው እስራኤል መሀል እስከወዲያኛው የሚታወስ መቅሰፍት አምጥቶበታል፡፡ይህን ክስተት ያስተዋለ ሁሉ እግዚአብሄርን እንዴት ማገልገል እንዲገባው ቆም ብሎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄርን ማገልገል እንዴትና እስከምን ድረስ የሚለውን ጥያቄ የሙሴና …
Continue reading የአገልጋይ ስብራት[1/2]

እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]

ተፈጥሮአችን ስለሆነ ሰዎች እንደሚመስለን እንገምታለን፡፡እንደሚሰማንም እንናገራለን፣ሊሆን ይችላል ብለን፡፡መሰለኝን አምነን እንቀበላለን፡፡ብዙ ጊዜ መስሎን የነበረ አሳብ ውስጣችን ከርሞ ወደ ምስል ይለወጥና የአስተሳሰባችንን አቅጣጫ ይቀይረዋል፡፡መሰለኝ እያልን ፣ፈራ ተባም እያልን እንጀምራለን፣ ነገራችንን፡፡ከጊዜ ወደጊዜ እያሳደግነው ከሄደና በታናሽነቱ ካልገዛነው አድጎ ወደ እምነት በመቀየር በተራው ይገዛናል፣ደግሞም ይመራናል፡፡ የመሰለኝ ጉልበት የሚገለጠው በዝግታ ነው፡፡ እውነት በሚገኝበት ስፍራ ላይ ልብን በሙላት ማዘንበል ከግምት አስተሳሰብ ያወጣል፡፡”እከሌ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]