ሰው የአምላኩን ቸርነት ያውቅና ስጦታውን ይቀበል ዘንድ የእግዚአብሄርን አሳብ ማስተዋል እንደፈቃዱም እርሱን መፈለግ ይገባዋል።ነገር ግን ሁላችን ያን ልናደርግ ባለመቻላችን ከዚያም በላይ ደግሞ እንድናገኘው ፍላጎት ባለማሳየታችን ማድረግ ያለብንን ሁሉ ሰጪው እንዳያመለክተን መቀበል የነበረብንንም የርሱን በጎ ስጦታ በአንድነት እንድናጣ አድርጎአል።በመጽህፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የእግዚአብሄርን ባህሪ ጠንቅቆ የተረዳው ንጉስ ዳዊት ግን እግዚአብሄርን በመፈለጉ የተቀበለውን መንፈሳዊ በረከት በመዝሙሩ ገልጦታል፦ …
Continue reading እርሱ ጠባቂዬ መጋቢዬም ነው
Category:የእግዚአብሄር ፈቃድ
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
መዝ.23:3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። ነፍስ ከየት ወዴት ተጉዛ ወዴት ትመለሳለች? ወይስ ምን የሚያሳስባት ጉዳይ ቢገጥማት ከመንገድዋ ፊትዋን ትመልሳለች? በነፍስ ጉዳይስ የሚያሳስብ ጉዳይ ምን ኖሮ መመለስን ትመርጣለች? መቼም ቢሆን ከተቃናልን የህይወት እርምጃ መመለስ፣ከተሳካልን ድል ወደ ሁዋላ ማለት፣ከተጉዋዝንበት ርዝመት ያለው መንገድ ማፈግፈግ ወይም የማስጠንቀቂያ ደውል ሰምተን የእኛ የምንላቸውን ለመሸሸግ ሙከራ ማድረግ፣ እንዲህ ቀላል …
Continue reading እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[3/3]
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[2/3]
መዝ.23:2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። አምላካችን ማሰማርያ መስክ ያለው አምላክ ነው፡፡መስኩ ማረፍያ ያለው ፣ ምግብና መጠጥም የተሞላ ስለሆነ የአቅርቦት አጥረት ከቶ አያጋጥመውም፡፡የመስኩ ባለቤት የመስኩን ልምላሜ ይቆጣጠራል፣ባእዳን ረግጠው እንዳያረክሱት ዘወትር ያጠራዋል፡፡በመስኩ ላይ የሚሰማሩ በጎች ባለቤታቸው አንድ ብቻ በመሆኑ የእርሱን ድምጽ ይለያሉ፣ምሪቱን ያስተውላሉ፡፡የእረፍት ውሀ በጎቹን በመስኩ ላይ በእረፍት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ያለ ፍርሃትና ጥርጣሬ ይጸኑ ዘንድ …
Continue reading እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[2/3]
መዝ.23:1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[1/3]
እውነተኛ እረኛ ወደ በረቱ በበሩ የሚገባ ነው፡፡ሾልኮ የሚገባ ወንበዴን ይከላከላል፡፡ሌባው እንዳያገኘንና በመንገድ፣ እንዳንቀር አወጣጥና አገባቡን የሚያሳየን አርሱ ብቻ ነው፡፡እውነተኛ እረኛ ድምጹን ያሰማና በጎቹን ያነቃል፡፡የበጎች እረኛ በህይወት በር በመግባት ወደ መኖርያችን በደህንነት ያስገባናል፡፡በልባችን ያድራል፡፡ያኔ ልባችንን ወደ እረፍት ያቀናዋል፡፡ወደ ቀናው የህይወት ስርአት ሊያመለክተን በእርሱም እንድንኖር ያጸናናል፡፡ እግዚአብሄር እረኛችን ነው፡፡እንዲያ በመሆኑ ከእርሱ ብዙ ይደረግልናል፡፡ለምሳሌ፡- ስጋችንና መንፈሳችን የሚያስፈልጋቸውን …
Continue reading መዝ.23:1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው[1/3]
