የጠፋሁት ልጅ ነኝ፤ የኮበለልኩና የተራቆትኩ፣ ርቄ ተጉዤም በዚያው የተሰወርኩ ነኝ፣ራሴን በእርያዎች መሀል ደብቄ ከመልካሙ አባቴ የተገለልኩ አመጸኛ፡፡ዛሬ በዚያ ባለሁበት ሆኜ አባቴ ሊያየቸው እንኩዋን ከሚጸየፋቸው ጋር ተወዳጅቻለሁ፡፡ማድረግ የሌለብኝን እያደረግኩ በመኖር ላይም እገኛለሁ፡፡ ለዛሬ ኑሮዬ የዳረገኝ እምቢተኝነቴ ሲሆን ያ ያለመታዘዜ ምክኒያት ሆኖ ከአባቴ ለይቶ አርቆኛል፡፡ የመጣሁበት አገር ኑሮ ገና ከሀገሬ ሳልነሳ በፊት እንደገመትኩት አልሆነልኝም፡፡ ከባእድ አገር አመል …
Continue reading የጠፋው ልጅ ሰቆቃ
Category:የእግዚአብሄር ፈቃድ
መመለሰ – ለእውነት ንሰሀ
መታረቅ፣ መስማማት፣ ሰላም ማውረድ፣ መቀራረብና የመሳሰሉት የሰላም ማስቀጠያ መንገዶች በማህበረሰብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡ የሰው ልጅ የአብሮነት እሴትን በልቡ አትሞ ስለያዘ በተለይ እርቅ በሚባል የአንድነት ማሰሪያ ላይ ትልቅ አትኩሮት አለው ሊባል ይቻላል፡፡ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ መታረቅን ይሻና መታረቂያውን የማይስማማበት አጋጣሚ ይገጥመዋል፡፡ሁላችን ብንሆን እርቅ ሰላም እንደሆነ ይገባናል ስለዚህ እንስማማበታለን፡፡የእርቁን ሂደት ወይም አላማ ግን ልንወድደው ካልቻልን አንቀበለውም፡፡ለምሳሌ …
Continue reading መመለሰ – ለእውነት ንሰሀ
አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[2/2]
ሰው ህያው የሆነ ነፍስና የሚረግፍ ስጋ ውህደት ነው።ህያው ነፍስ ከእግዚአብሄር እፍ ከተባለ የህይወት እስትንፋስ ስለተገኘች የምትጠፋ አይደለችም፣ ረቂቅና መንፈሳዊ ስለሆነች የመታየትም የመዳሰስም ችሎታ የላትም።ስጋ ግን የአፈር(ምድራዊ) ነው፣ ግኡዝ፣ የሚታይና የሚዳሰስ ጭምር። ዘፍ.2:7 ይህን ያረጋግጥልናል፦ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።“ እውነታው እንደሚያሳየን የምድር አፈር ደቃቅ፣ …
Continue reading አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[2/2]
ዲያቢሎስን መቃወም
ክርስቲያኖች ጠላትን ስንቃወም በቃልም በስራም እንቃወመዋለን።የመቃወሚያ መሳሪያችን ደግሞ በመንፈስ የምንጠራው የኢየሱስ ስም ነው። ጠላትን ለመቃወም ስንነሳ ለምን እርሱን እንደምንቃወመውና ተቃውሞአችን ምን እንደሚሰራ/ውጤቱ ምን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።በቅድሚያ ለመቃወም ምክኒያታችን ዲያቢሎስ የሚያቅዳቸውና የሚሰራቸው የክፋት ስራዎቹ ናቸው። በተጨማሪ በክፉ ባህሪው ምክኒያትም እንቃወመዋለን። የህይወታችን ጥፋት መሰረቱ እሱ ነው፣የምንኖርበትን ማህበረሰብና የኑሮ ሲስተምም የተቆጣጠረው እሱ ነው። ለመቃወም መቃወሚያ መንገዱን መረዳት ይጠይቃል። …
Continue reading ዲያቢሎስን መቃወም
ያከበረ ጠሪ
አንድ ትሁት ንጉስ በግዛቱ ያለውን ህዝብ በማክበር የእራት ግብዣ ጠራ።የተጠራው ህዝብ የንጉሱን ክብር ባይመጠንም ንጉሱ ያንን ሳይቆጥር ወደ እርሱ የክብር ስፍራ ሁሉን ጋበዘ።ንጉስ ፈራጅ ነው፣ነገር ግን ያን ስልጣኑንና ፍርድን አስቀምጦ በርሱ ግዛት በየትኛውም የህይወት ይዘት ያሉትን በርህራሄ ተመልክቶ ጋብዞአቸዋል።ንጉሱ ባለ ሞገስና የተፈራ ነው።ነገር ግን የጠራቸውን ምስኪኖች ውርደታቸውን ገለል አድርጎና በክብር አይቶ በዙርያው ካሉ ባለማእረጎች ጋር …
Continue reading ያከበረ ጠሪ
አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[1/2]
ሮሜ.8:5-12 ስለ እኛ ስለ ሰዎች ሲናገር፦ “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ …
Continue reading አሮጌው ወይስ አዲሱ ሰው?[1/2]
ከእግዚአብሄር ፊት መሸሽ
ሀጢያት ስንሰራ ከጻድቁ አምላክ ፊት እንሸሻለን፡፡ ሀጢያት ያሳድዳል፣ ሂድ ሂድ ጥፋ ተሰወር ይላል፡፡ የምህረት በር እንዳናይ አድርጎ የሽሽት ቁለቁለት ላይ ያኖረናል፡፡ ከእግዚአብሄር ፊት የሚሸሹ ሁሉ ስብራት ላይ ይወድቃሉ፡፡ መሸሽ ከእግዚአብሄር ክልል ያስወጣል፡፡ አዳም ከእግዚአብር ፊት በሸሸበት ቀን ከኤደን ገነት እስከወዲያኛው ተባረረ፡፡ከመልካም ነገር በራቅን ቁጥር እየለቀቀን የሚሄድ የእግዚአብሄር መልካም ነገር ብዙ ነው፡፡ ዘፍ.4:9-16 ”እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፡- …
Continue reading ከእግዚአብሄር ፊት መሸሽ
ከራስ ሽሽት
አንዳንዴ ከራስ በሚመነጭ ፍላጎትና አስጨናቂ ስሜት፣ እረፍት ከማይሰጥ አሳብ፣ ከሰው ከሚመጣ ግፊት ያልያም የሁኔታዎች መወሳሰብ በሚፈጥረው አለመመቸት ጥብብ ጭንቅ ሲለን መሬት ላይ ያሉ እውነታዎችን ለመዝለል በሚል የምንሄደው አደገኛ አካሄድ አለ፡፡ ነገሩ ጎልቶ ሳለ እርሱን ላለማየትና ላለመስማት እንሞክራለን። እስጨንቆ የሚገፋ ሀይል እስከማናቆመው ድረስ ወጥሮናል፣ እናም አሳሳቢነቱ ስለሚሰማን መፍትሄ በምንለው መንገድ እንሄዳለን። የሆነው ያ የማንፈልገው ውጤት ህሊናችንን …
Continue reading ከራስ ሽሽት
የቀጠነው መንገድ ለዚህ ዘመን
ማቴ.13-14 “በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።” የእግዚአብሄር ቃል ከሚገልጠው መንፈሳዊ መንገድ መሃል ቀድሞ የምናገኘው ትልቅ መንገድ ተብሎ የተጠራውን ነው። የመንገዱ መጠን በትልቅነቱና በሚያስተናግደው መንገደኛ ብዛት ተገልጦአል። ይህ መንገድ ትልቅ ይሁን እንጂ ለሰው ልጆች ጥንቃቄ …
Continue reading የቀጠነው መንገድ ለዚህ ዘመን
ባለ ስልጣን አምላክ
ስልጣንና ባለስልጣን በምድር ስርአት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ የአስተዳደር፣ የስነ-ስርአትና የሰላም አብይ መሰረቶች ናቸው።ቃሉም በሮሜ.13:1-4 ላይ ሲናገር፦ “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን …
Continue reading ባለ ስልጣን አምላክ
