ጠይቆ ያለመቀበል ፈልጎ ያለማግኘት የወለደው ውጤት ሲሆን የዚህም ምክኒያት ሰጪውን አምላክ ፊት ሽቶ ለማየት ያለመቻል የፈጠረው ውድቀትና ያለመረጋጋት ነው፡፡ በሌላ አባባል ሰጪውን አምላክ በትክክለኛ አካሄድ ተራምደን ልናገኘው ባለመቻላችን የጠየቅነውን ነገር ከሰጪው መቀበል አልቻልንም፣ ለማግኘት እንደተመኘነው አልተሳካልንምም ማለት ነው፤ ሞገስ አልባ አካሄድ ማለትም ይሄው ነው፡፡ ለመሆኑ ለምንድነው ሰው ከፈጣሪው አንዳች ነገር ፈልጎ ሳለ ቢጠይቅ ከርሱ የፈለገውን ያላገኘውና ፍላጎቱን ሊያሙዋላ ያልቻለው? ሰጪው ካለ፣ የተናገረው ቃል ካለ፣ ከጠየቃችሁኝ መልሳለሁም ካለ፣ ምንድነው የከለከለን ነገር? አንድ ትልቅ ክፍተት የአምላካችንን ፊት እንዳናይና ሞገሱን እንዳንቀበልም እያደረገ ነው ማለት ነው፡፡
አንድ ነገር ከመፈለግ በፊት ሊታወቅ የሚገባ ነገር
መጠየቅ ለመቀበል እስከሆነ ድረስ እንደሚያገኙ ሆኖ በእምነት መፈለግና ተማምኖ ፊቱን ለማየት፣ ሞገሱንም ለመቀበል መጠባበቅ በጠባቂው ዘንድ ሊኖሩ የሚገቡ ተግባሮች ናቸው፡፡ ሰው ግን ሙሉ መስሎ መታየት እንጂ ፈላጊ ወይ ለማኝ ሆኖ መታየትን አይፈልግም፤ እንዲያ ባይሆን ኖሮ ባለመታከት የአምላኩን ፊት በፈለገ፣ እስኪሰጠው በትግስት በጠበቀ፣ ባለመታከት በለመነና የለመነውን እስኪያስረክበው በምስጋና በቆየ ነበር፡፡
እንደ እግዚአብሄር ቃል የሆነ ፍለጋ ሁለት ደረጃዎችን ያልፋል፡-
የመጀመሪያው ሰጪውን መፈለግን ይመለከታል፡፡ ሰጪው ማን ነው? ባህሪው፣ ፈቃዱስ? ይሄን ስናውቅ እርሱን እንዴት እንደምንቀርብና አፈላለጋችን ምን እንደሚመስል ይገለጥልናል፡፡
1ዜና.16:10-14 “በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም የአፉንም ፍርድ። እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው። ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥”
እግዚአብሄርን ፈልጉት አለ፤ ስትፈልጉትም ሁልጊዜ ፊቱን በመሻት፣ እስክታገኙትም አዘውትራችሁና ደጋግማችሁ ፈልጉት አለ፡፡ ስትፈልጉት በልብ ደስታ ይሁን፣ ድንቁን በማሰብ ይሁን፣ በስሙ ሰርቶ እንደሚሰጥም በመታመንና በሙሉ ልብ በመናገር ይሁን አለ፡፡
ይህን የምናደርገው ማንነቱን በማወቅ ሲሆን ማን ብለን እንደምንፈልገው በመረዳትም ይሁን፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር ማን መሆኑን ለህዝቡ ሲያስተምር እንዲህ ብሎ ነበር፡-
”…አንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህ፥ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ በሕይወት ይኖራልን? አምላካችሁ እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ ነበርን? እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። ያስተምርህ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማህ፤ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳየህ፤ ከእሳትም ውስጥ ቃሉን ሰማህ።… እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቅ፥ በልብህም ያዝ።” (ዘዳ.4:32-40)
እንዲሁም ፈቃዱን ካወቅን እርሱን እንዴት እንደምንቀርብና አፈላለጋችን ምን እንደሚመስል ይገለጥልናል ካልን ከእኛ ምን ሊያይ ይፈቅዳል የሚለውን ማወቅ ይገባል፡-
ዘዳ.5:32-33 ”እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”
የሚሰጥ አምላክ የተናገረውን የሚያድረግ ነው እንጂ የሚዘነጋ አይደለም፤ ምክኒያቱም እግዚአብሄር ብዙ ትውልዶችን የሚያልፍ ቃልኪዳን ተናግሮ ቢሆንም እንኩዋን ያን የተናገረውን ጠብቆ ከመፈጸም ወደ ሁዋላ አይልም፣ አይታክትምም፡፡ ለዚህ ምሳሌ ለሄዋን የገባላት የዘፍ.3:15 ቃል ኪዳን ሲሆን ይህን ቃል ኪዳን ክርስቶስን በመውለድ ከብዙ ሺህ አመታት በሁዋላ ሲያደርግ መታየቱ የተናገረውን መፈጸሙን ያሳያል፡፡
እግዚአብሄርን ለመለመን ስንነሳ የለመንነውን የሚሰማ አምላክ መሆኑን በማመን መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሄር የቅርብ አምላክ፣ አይኖቹ ሁሉ በምድር ያሉትን እንደሚያዩ እንዲሁም እስትንፋሳችንን ሳይቀር ማድመጥ እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ሩህሩህ መሆኑን ስንረዳም ለጥያቄያችን ፈጣን መልስ እንዳለው እናስተውላለን፡፡ እንዲሁም የቸርነቱን ብዛት በማስተዋል መስጠት የማይችለው ነገር እንደሌለ ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን እግዚብሄር ካስቀመጠው መልካም መዝገቡ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ማወቅ ልመናችንንም በዚህ እውቀት መቃኘት እንዳለብን ያለመርሳት ነው፡፡ በጸሎት ወቅት ስሙን ከፍ ማድረግና አጥብቆ መጥራት ሲፈለግ በቅዱስ ስሙ ላይ ሙሉ እምነት አኑሮ መሆን አለበት፡፡ በቅዱስ ስሙ መጓደድ መመካታችንን ይጨምራል፣ የጠላታችንን ሀይልና አሳብ ያሳንሳል፣ ልባችንም በእምነት እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው ማለቱም ወደ እርሱ ስንቀርብ እርሱ እንደሚቀርበን በማመንና ሰምቶ እንደሚመልስልን አምነን ጸሎታችንን በመቻሉ ደስታ እናቅርብ ማለቱ ነው። እግዚአብሔርን በመፈለግ ምክኒያት የህይወት ጽናትና መመስረት እንደሚመጣ ቃሉ ያስተምረናል፤ ሁልጊዜ ፊቱን መፈለግም መልስን። የእግዚአብሄር ልጆች በእርሱ ምህረት፣ በጎነትና ቸርነት እንደሚኖሩ አስተውለው በውስጣቸው ሊረኩ የተገባ ነው፤ ይህም እምነትን ይጨምርላቸዋል፡፡
ህዝቡ እግዚአብሄር የሠራትን ድንቅ ሲያስብ፣ ተአምራቱንና የአፉንም ፍርድ በልቡ ሲያሰላስል የሚሸነፍ የጠላት አሰራር አለ፣ ለሰው የሚመጣ የእምነት መንፈስም እንዲሁ አለ፡፡ እግዚአብሄርን የሚያውቁ የለመኑትንም እንደሚሰጣቸው ያስተዋሉ አስረግጠው የሚናገሩት፡- “እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው” በማለት ነው፤ ይህን የሚሉትም ማንነቱን ስለተረዱ ብቻ ነው።
ሰጪውን መፈለግ በተመለከተ የሰጪውን ማንነት ማወቅ፣ ባህሪውንና ፈቃዱን መረዳት እንደሚያስፈልግ አይተናል፡፡ ቃሉ እንደሚያስረዳን ከሆነ እግዚአብሄርን ለማግኘት ከእርሱ ጋር በአብሮነት መጽናት አስፈላጊ ነው፡- ከራቅነው ይርቀናል፤ ከተውነው ይተወናል፤ ከቀረብነው ግን ይቀርበናል፣ ያለጥርጥር ያየናል ይሰማናልም፡፡ ሲፈጥን ከጉዳት ለመታደግ፣ ሲዘገይ እንድንሰራ ጊዜ ሊሰጥ፣ በፍሬያማ ወቅትም ሊያየን አስቦ እንደሆነ ይግባን፡፡
2ዜና.15:2-4 “አሳንም ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፡- አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል። እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር። በመከራቸውም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ አገኙት።”
እስራኤል እግዚአብሄርን ትቶ ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ኖረ። ህዝቡ በዚያ ህይወታቸው ውስጥ በነበሩበት ዘመን ሁሉ እውነተኛው አምላክ ርቆአቸው ነበር፣ ምህረቱ ሆነ ቸርነቱም እንደዚያው፡፡ ከእርሱ በራቁበት የያኔው ዘመን የነበራቸውን መልካም ነገር ጥለው ተገኙ፣ በስርአቱ ማደርንም ተዉ፣ በዚያ ሰበብም ከበጎነቱ ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡ ለምነው አልተቀበሉም፣ ጸልየውም አልተሰሙም፤ ለምን? ከሌላ አምላክ ጋር ቃልኪዳን ተጋብተው ነበርና! ህዝቡ ተጎሳቅለውና በመከራ ተኮርኩመው ከደቀቁ በሁዋላ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፣ በፈለጉት ጊዜም አገኙት፡፡
በእርግጥ እርሱን መፈለግ ማንነቱን ከማወቅ ጋር ሲሆን ታላቅ መልስ ያመጣል፣ ፍጹም ላቃተንና ለከበደን ነገር እንኩዋን መልስ ፈጥኖ ይመጣል፡፡ ይሄንን እውነት ለማስተዋል ንጉስ ኢዮሣፍጥ የተከተለውን መንገድ ማስተዋል ይጠቅማል (2ዜና.20:1-16)፡-
”እንዲህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞዓብና የአሞን ልጆች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መጡ። … ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ። ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ተከማቸ፤ ከይሁዳ ከተሞችም ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ። ኢዮሣፍጥም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባኤ መካከል በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በአዲሱ አደባባይ ፊት ቆመ፤ እንዲህም አለ፡- አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፥ በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ችሎታ በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም። አምላካችን ሆይ፥ በዚህ ምድር የነበሩትን አሕዛብ ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት ያሳደድህ፥ ለወዳጅህም ለአብርሃም ዘር ለዘላለም የሰጠሃት አንተ አይደለህምን? እነርሱም የተቀመጡባት፥ ለስምህም መቅደስን ሠርተውባት፡- ክፉ ነገር፥ የፍርድ ሰይፍ ወይም ቸነፈር ወይም ራብ፥ ቢመጣብን ስምህ ባለበት በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ ቆመን በመከራችን ወደ አንተ እንጮኻለን፥ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ አሉ። አሁንም፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ያልፉባቸው ዘንድ ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ፈቀቅ ብለው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥ እነሆ፥ ለወሮታችን ክፋት ይመልሱልናል፤ ከሰጠኸንም ርስት ያወጡን ዘንድ መጥተዋል። አምላካችን ሆይ፥ አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን እንቃወም ዘንድ አንችልም፤ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን ወደ አንተ ናቸው። የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ከሕፃናቶቻቸውና ከሚስቶቻቸው ከልጆቻቸውም ጋር በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካሪያስ ልጅ በየሕዚኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤ እንዲህም አለ፡- ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል። ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። ነገ በእነርሱ ላይ ውረዱ፤ እነሆ፥ በጺጽ ዓቀበት ይወጣሉ፤ በሸለቆውም መጨረሻ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት ታገኙአቸዋላችሁ።”
ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ብዙ ነገር ያስተምረናል፡- ስለ እግዚአብሄር ማንነትና እርሱን አፈላለግ፣ ፈቃዱን ስለመጠየቅና እንደ ፈቃዱ መጸለይ የሚያመጣውን ፈጣን መልስ፣ በፊቱ መቅረብ እንዴት እንደሚቻልና በርሱ ላይ መታመን ማለት እንዴት እንደሆነ… የመሳሰሉትንም ያሳውቃል፡፡ መፈለግ፣ መጠየቅ፣ መጠበቅም ሆነ መጽናት እንደ ኢዮሳፍጥ ቢሆን እንዴት ያለ የእግዚአብሄር ማዳንና በረከት እንደሚሆን ይህ ቃል በግልጥ ያሳያል፡፡
እንደ እግዚአብሄር አሳብ የሆነ አፈላለግ ለማድረግ፣ ቸርነቱን ለመቅመስና በርሱ መልካምነት ለመጥገብም እርሱን መፍራት እንዲገባ በ መዝ.34:8-10 ውስጥ ተገልጦአል፡-
”እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት። ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉትን ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም” ይላል፡፡
እንዲህ ሰጪውን አምላክ እንደሚገባ ካወቅን ዘንድ በሁለተኛ ደረጃ ሊሰጠን ፈቃዱ የሆነውን ነገር ማወቅ፣ አውቆም መፈለግ እንዲገባ ማስተዋልም ተገቢ ነው፡፡ ብዙ ልብ የማንላቸው በራሳቸው የሚሆኑ የሚመስሉን ክስተቶች በሙሉ እግዚአብሄር ለጥቅማችን አዘጋጅቶ የሰጠን ስጦታዎች ናቸው፡፡ ሰው ግን ወደ ማስተዋል ካልደረሰ በእነዚህ የእግዚአብሄር ስራዎች ምስጋና አያቀርብም፡፡
ቃሉ በመዝ.147:7-11 ሲናገር፡-
”ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤ ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም። ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል። የፈረስን ኃይል አይወድድም፥ በሰውም ጭን አይደሰትም። እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል።” ይላል፡፡
”አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ” (ኢሳ.40:28-30)
እግዚአብሄር እንደ አንድ ወዳጅና ሩህሩህ አባት የለመንነውን የሚሰጥ አምላክ ቢሆንም እንደ ፈቃዱ ያልሆነ ነገር ሊሰጠን ግን ፍላጎቱ አይደለም፡፡ ስለዚህ የምንፈልገው እንደ ፈቃዱ የሆነውን ብቻ ሊሆን ይገባል ማለት ነው፡፡
1ዮሐ.5:14-16 ”በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።”
እንደፈቃዱ የሆኑ ነገሮች በሙሉ ለእኛ መልካም ነገሮች ናቸው፡፡ በጎው አምላክ የሚያድኑንን፣ የሚያተርፉንንና መንግስቱን የሚያወርሱንን ነገሮች ሁሉ ከመልካም መዝገቡ ውስጥ ስላኖራቸው እነርሱን ሊሰጠን ፈቃዱ ነው፡፡
የሚያሰዝን አስፈሪም የሆነ ሁኔታ ግን አለ፡-እግዚአብሄር መስጠትን አስቀርቶ ተላልፎ መሰጠትን የሚፈጥርበት ያ ሁኔታ አደገኛው ሁኔታ ነው፤ ይህ የምንለው ነገር ሲፈጠር ከእግዚአብሄር አንዳችም የምንቀበለው ነገር አናገኝም፣ ይልቅ ለጠላት ተላልፈን የምንሰጥበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው ፡፡
ኤር.32:4-5 ”የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፥ አፍ ለአፍም ይናገረዋል፥ ዓይኑም ዓይኑን ያያል እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤ እርሱም ሴዴቅያስን ወደ ባቢሎን ያፈልሰዋል፥ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከላዳውያን ጋር ብትዋጉ ምንም አትረቡም።”
ከእግዚአብሄር የጥበቃ ክልል ስንወድቅና እጁ ስትለቀን ከወዴት እንደወደቅን አስተውለን መመለስ እንጂ የሰመጥንበት ውስጥ እንዳለን የምንወራጭበት አካሄድ ከንቱ ሙከራ እንጂ ጠላትን እንድናሸንፍ የሚያስችል አይሆንም፡፡ እስራኤላውያን በአካሄዳቸው ከእግዚአብሄር ተለይተው ሳለና ለጠላት ተላልፈው በተሰጡበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚገዛቸውን የጠላት ብርቱ ክንድ ሊጋፉ ሲሞክሩ ይታያል፡፡ ጠላትን ተዋግቶ ለማሸነፍ የሚበጀው መንገድ ግን ቅድሚያ ከርሱ ጋር መታረቅና በእምነት እንዲዋጋለት መንገድ መልቀቅ ነው፡፡
መሳ.3:7-9 ”የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በኣሊምንና አስታሮትን አመለኩ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኵሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኵሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት። የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ወንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው።”
እግዚአብሄር ህዝቡን ለምን እንዲያ ያደርጋል? በማይታዘዝ ህዝብ ላይ ስለሚቆጣ፣ ከሚጣላው ጠላቱ ጋር በግብሩ ሲተባበርና በአሳቡ ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር ሲጋጭ ነው፤ በዚያ አካሄድ ውስጥ ባለበት ዘመንም ሁሉ በጠላቱ እጅ ላይ ይጥለዋል፤ አዎ፣ የሚያስፈልገንን እየሰጠ ከሚንከባከበን፣ ከክፉም ከሚጋርደን አምላክ ፈቃድ ጋር መጋጨት ስናመጣ እንዲህ ለጠላት ተላልፈን እንሰጣለን ማለት ነው፡፡
በሮሜ.1:22-26 ውስጥ የተገለጠው ቃል እግዚአብሄር አእምሮና ማስተዋል ሰጥቶ ሳለ የተቀበሉትን እንዳልተቀበሉ ሆነው ወደ አመጽ ሊያመሩ በሚንደረደሩ ሁሉ ላይ ጥፋት ሊሆንባቸው እንደሚችል የሚያስጠነቅቅ ነው፡-
”ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን። ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው”