ምድራዊ መንግስታት እውቀትን እንደ ስልጣኔ በር ቆጥረው ህዝባቸው ያውቅ ዘንድ ይለፋሉ። በሁሉን አቀፍነት አንጻር ይህ እውቀትን የማግኘት፣ የመረዳትና የመቀበል ዝንባሌ የትውልድ ማስቀጠያም ተደርጎ የሚቆጠር ነው፤ ምክኒያቱም ያላወቀ የማያስተውልና ወገንን ጠቃሚ ስለማይሆን ነው። በመንፈሳዊ ጉዳይም ከዚህ የላቀ አስፈላጊነት ባለው ሁኔታ እውቀት አትኩሮት ይሰጠዋል። በምድራዊ እውቀትና በሰማያዊው መሃል ግን ከፍተኛ ልዩነት ያለበት ነጥብ አለ፣ እርሱም የእውቀት መገኛው/ምንጩ …
Continue reading እውቀተ መለኮት(1…)
ለኛ የታሰበልን
በእግዚአብሄር ፈቃድ አካባቢ ያለውን የፍጥረት ስፍራ ሰው ማስተዋል ቢችል የምድር ፊት ዛሬ ላይ ምን ሊመስል ይችል ነበር? ሌላው ቀርቶ ሰው የታሰበለትን ቢረዳ፣ እግዚአብሄር ሲጣራ ቢሰማ፣ ለራሱ አሳብ ሳይሆን ለሰሪው ድምጽ ጆሮውን ቢያዘነብል የሰው ልጅ እንዴት ባለ ሰላምና ደስታ ይኖር ነበር? አለም መልኩዋም አሳቡዋም ምንም ቢያባብል በመጎተቻዋ ተጠልፈው እጅ ያልሰጡ ያተረፉት ነገር ብዙ ነው፤ በዚህ ሳያበቃ …
Continue reading ለኛ የታሰበልን
ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]
የነጻነት ትርጉም የነጻነት ህይወት ትክክለኛ ትርጉም በኢየሱስ የሚገኝ ነው፤ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጆች በነጻነት ከአምላካቸው ጋር እንዲኖሩ የነጻነት መንገድ ሆነ። ሰዎች በህሊና እየተመሩ ከሚኖሩበት ነጻ ህይወት ተገፍተው ወጥተው በዲያቢሎስ ጫና የእርሱን ፈቃድ ይከተሉና ይፈጽሙበት የነበረው ብዙ ሺ ዘመን ያበቃው በነጻነት የሚኖሩበትን መንገድ ጌታ ኢየሱስ ስለገለጠው ነበር፤ ያን የነጻነት ህይወት ሰዎች ሁላችን ልንኖር ክርስቶስ ሃጢያት ከሚባል …
Continue reading ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]
የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(2…)
ካለፈው የቀጠለ… – እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ… ይላል (1ቆሮ.14:9) በፍቅሩ ምክኒያት የተቀበልነውን ደህንነት በፍቅርና በሸክም ድህንነት ለተገባችው የሰው ልጆች ሁሉ ማሳለፍ ምህረት ካገኘ ወገን ይጠበቃል። ስለመዳን እያወሩ አዳኙን ያለመንገር አይቻልም፣ የተሰጣቸውን እያስተዋወቁና በሰፊው እየተናገሩ ሰጪውን ያለማስተዋወቅ ንፉግነት ነው። አይሁድ የአለም ሁሉ አዳኝ ጌታን ሊቀበሉ እጅግ አንገራግረዋል፤ ምህረትና ፈውሱን ከተቀበሉም በሁዋላ የተሸሸጉ አልጠፉም፤ …
Continue reading የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(2…)
ነጻ የወጣ ህዝብ[1…]
የባርነት ሸክሞች ነበሩ… እነዚህ ሰውን የሚያጎብጡ፣ የሚያስሩ፣ የሚያስጭንቁ፣ የሚያውኩ ነበሩ። የተሸከማቸውን አያነቃንቁ፣ አያራምዱ፣ አያዘረጉ እረፍትም አይሰጡ። ጌታ ኢየሱስ ግን ከእኛ ላይ አወረዳቸው። ከሸክም በሁዋላ ጎብጦ መቅረትም አለ፣ የእስራት ጠባሳ ፈሪ አድርጎም ያስቀራል፣ የሚያስጨንቁም ለቀው ቢሄዱም በሩቅ ቢያስፈራሩ ዋስትናችን ጌታ ኢየሱስ ካለን ብቻ መፍትሄ ይሰጣል፤ እምነት በእርሱ ላይ ባለን መደገፍ፣ እርሱን በህይወታችን በማንገስ፣ ይሄ ልምምድ ብቻ …
Continue reading ነጻ የወጣ ህዝብ[1…]
የምስራች ለሁሉ
ማር.1:1-4 “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፦ እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።” መጽሃፍ እንደሚል ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ በሰጠው የእግዚአብሔር ወንጌል አስቀድሞ ከጠራቸው ሐዋርያ አልፎ …
Continue reading የምስራች ለሁሉ
የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(1…)
አምላካዊ ምክኒያት አለ? እግዚአብሄር አምላክ በየዘመኑ ላለ ህዝብ እንደ የትውልዱ ቀርቦ ይመጣና የሰውን ልጅ ወደ ራሱ ይጣራል፤ ለጠራው ሰው የጠራበትን ምክኒያት ከማመልከቱ በፊትም የራሱን ማንነት በፊቱ ያውጃል፤ ይህንም በዋናነት አብረሃምና ዘሩ እስራኤልን በጠራው ጊዜ አድርጎአል፡፡ ለእስራኤል አስርቱን ትእዛዝ በሰጠበት ወቅት ራሱን ከማስተዋወቁ ባሻገር ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አይሁንላችሁ ሲል አስጠንቅቆ ነበር፡፡ ይህ የጸና አዋጅ በህዝቡ …
Continue reading የእግዚአብሄር መገለጥ፦ምንና ለምን(1…)
የስሜት አግባብነት[1…]
ስሜት ምን? ማንኛውም ከሰውነታችን ውጪ የሆነ ነገር ተጽእኖው ወደ እኛ ሲመጣ የሆነ የሰውነታችን ክፍል መልስ ይሰጣል፤ ይህ የሚሆነው ያየነው፣ የዳሰስነውና የሰማነው ነገር ትኩረታችንን ስለሳበ ሊሆን ይችላል፤ ሁሌም የነካነው፣ የቀመስነው፣ ያየነውና የሰማነው ነገር እንድንንቀሳቀስ ያስወስነናል፦ አንድ ነገር ቢሸተን እንደሽታው ምንነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንገባለን፤ ሰውነታችንንም የነካን ነገር እንዲሁ ለመልስ እንድንንቀሳቀስ ሊያደርገን ይችላል። የማየት፣ የማሽተት፣ የመስማትና የመቅመስ …
Continue reading የስሜት አግባብነት[1…]
ጊዜ ጌታ? [3..]
– ጊዜ ፈራጁ? ጊዜ ፈራጅ ነው አንበል፣ ፈራጅስ ጌታ ነው፦ መዝ.50:5-6 ”ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።” የወቅትን ፈራጅነት ለማሳየት ጊዜ በሰው ላይ እንደሚሰለጥንም ለማመልከት ሰዎች በልማድ ያን ይሉታል፡፡ ግን እግዚአብሄር በጊዜያቱ ለሚሆኑት ነገሮች ባለቤት ከሆነ ጊዜ በነገሮቹ ላይ ስልጣን ሊኖረው አይችልም፤ ጊዜ ራሱ ጌታ ካለው የገዢነት ቦታ …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [3..]
የመሰረቱ ማጠንጠኛ (2…)
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ በመንፈሳዊ ህይወታችን መቆምያ፣ መጽኛችንና እምነታችንን በድል ማጠናቅቅ የሚያስችል የስኬታችን መሰረት ነው። እርሱ ሲናገር ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም ብሎአል። ጌታ ኢየሱስ ለእኛ የሁሉ ነገራችን መሰረት ነው፦ ”እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ …
Continue reading የመሰረቱ ማጠንጠኛ (2…)
