እምነት በሃይማኖት ትምህርት ላይ መመስረት ይጠይቃል። ሃይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት እንጂ ቁሳዊ አይደለም፣ መደመርና መቀነስ ስሌት የሚመራውም አይደለም፣ ትምክህቱም ሳያይ መዘርጋት እንጂ ማስተማመኛ ሰብሳቢ አይሆንም፣ እምነትና ማስረጃ አብረው አይሄዱም፣ አማኝ የሰማውን መለኮታዊ ቃል ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል እንጂ ምረመራ አድርጎ ማረጋገጫን አያቀርብም። ‘’እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(3… )
ቃለ መለኮት(3…)
የህያው እግዚአብሄር ቅዱስ ቃል አመጸኛና ታዛዥ ላልሆኑ ሰዎች የትኩረት አቅጣጫ የተነፈገው፣ ቀዝቃዛ ስሜት በሚታይባቸው ቸልተኞች ተሸፍኖ ያለ፣ አሳቢነቱ ዝቅተኛና ትርጉሙ በማይሰማው ኢ-አማኝ አእምሮ ውስጥ ከንቱ የሚመስል ወይም ለፍጥረት ብዙም ፍላጎትና ጉጉት የማይፈጥርና የማይስብ ጉዳይ የሚመስል ነው። አለምም በማየት፣ በመዳሰስና በቀመር ስለምታምን በነዚህ ስጋዊ መታመኛ መሳሪያዎች የምትደገፍ ናት። እግዚአብሄር ግን ስለቃሉ በመናገር ያሳስባል፦ ‘’እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ …
Continue reading ቃለ መለኮት(3…)
የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (2..)
የመስቀሉ ቃል የመስቀሉ ቃል የወንጌል ማእከላዊ መልእክት ሆኖ ሳለ የበዙ አስተማሪዎች ያን ባለማስተዋል ትኩረታቸውን ወደ ሌላ አድርገው በደህንነት ትምህርት ላይ ብዙ ሰዋዊና አጋንንታዊ ትምህርቶች ጣልቃ እንዲገቡ ምክኒያት ሆነዋል። በሌላ በኩል በሃዋርያቱ በኩል ለአለም የደረሰው ወንጌል ያለመቀያየር እንዲቀጥል ከመስራት ይልቅ በተለያዩ ትምህርቶች እንዲበረዝ፣ በወግና በስርአት እንዲታሰር አድርገዋል። የመስቀሉ ቃል በትክክል በሚሰበክበት ስፍራ ሁሉ ነፍሳት ወደ ጌታ …
Continue reading የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (2..)
የመመለስ ትርፍ {1..}
መመለስ ከወጡበት፣ ከተዉት፣ ከተሰናበቱት፣ ከተጣሉት፣ ካኮረፉት እንዲሁም ከጣሉት ነገር ሊሆን ይችላል። መመለስ ከወጡበት ነገር ሲሆን ዳግም ወደ ቤት፣ ወደ አገር፣ ወደ ስራ፣ ወደ ልማድ፣ ወደ ካዱት፣ ወደ ረሱት፣ ወደ ጠሉትም ነገር ሁሉ ሊሆን ይችላል። በመመለስ አልፈልግም ብለው ከተዉት ነገር፣ ስራ ወይም ሰው ዳግም የመገናኘት እድል ይፈጥራል። የጠላነው ይሁን የወደድነው በሆነ አጋጣሚ ወይም ተጽእኖ ምክኒያት ትተነው …
Continue reading የመመለስ ትርፍ {1..}
ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(1… )
ሰው በእምነት ወይም በሃይማኖት በኩል የሚያመልከውን አምላክ ይጠጋል፣ ይከተላልም። ማንም ያለ ሃይማኖት መኖር አይችልም፣ ምክኒያቱም ለአምልኮ የተፈጠረ ማነንት በውስጡ ስለያዘ። ያ ማንነት መንፈሳዊ በመሆኑ ሁልጊዜ በመንፈስ ያስሳል፣ የሚያረካውንም ነገር ይፈልጋል። የሰው ተፈጥሮ ስጋ፣ ነፍስና መንፈስ እንደያዘ ቃሉ ያስተምራል፤ በስጋው በኩል ከግኡዙ አለም ጋር ይገናኛል፣ በመንፈሱ በኩል ደግሞ መንፈሳዊ አለምን ይገናኛል። በሰው ስጋዊ ተፈጥሮ ውስጥ ያለው …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(1… )
የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (1..)
የመስቀሉ ቃል ክርስቶስ የመሰቀሉ አዋጅ ቃል ነው፤ ወደ ቃሉ ውስጥ በጥልቀት ስንመለከት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ የምስራቹን የሚናገረው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል በሙሉ ነው፤ የመስቀሉ ቃል የእግዚአብሄርን የማዳን ስራ የሚያውጅ ቃል እው፤ በመስቀሉ ቃል ሃጢያተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ አለም መምጣቱ ተበስሮአል። የመስቀሉ ቃል የገዛ ወገኖቹን ሊያድን ወደነርሱ በስጋ መምጣቱን ያስረዳል። የመስቀሉ ቃል ክርስቶስ ባፈሰሰው …
Continue reading የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (1..)
ቃለ መለኮት(2…)
የህያው አምላክን ቃል የሚያስተውሉ አጥብቀው በቃሉ ይደገፋሉ፤ በቃሉ ላይ መዛነፍ እንደሌለ ማመናቸው ህያውነቱን አምነው እንዲቀበሉም ይረዳቸዋል። ‘’እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።’’ (ኢሳ. 45:22-23) ቃሉን ለኛ በምናስተውለው መንገድ እንደንሰማው …
Continue reading ቃለ መለኮት(2…)
የስሜት አግባብነት[3…]
ግራ በመጋባት ሰበብ ለዘመናት በላያችን የተሰራው በጎ መንፈሳዊ ስራ ይናዳል ግራ በመጋባት ውስጣዊ ስሜታችን ሲናወጥ መቆም ሊያቅተን በሚያደርስ መናወጥ ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ግራ መጋባት፣ በተምታታ ሃሳብና ስሜት መያዝ፣ ያለመረጋጋትንም ጭምር ስለሚፈጥር በአንድ መንፈስ መጸለይ እንኩዋን አያስችለንም። በመንፈሳዊ ህይወት መዛባት ምክኒያት ግራ መጋባት ተፈጥሮ የነፍስ ደጋፊ አሳብ ከተምታታ መንፈሳዊ ሆኖ መቆም አይቻልም። በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም …
Continue reading የስሜት አግባብነት[3…]
ቃለ መለኮት(1…)
ቃለ-መለኮት ወይም የመለኮት ቃል የእግዚአብሄር ድምጽ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ድምጹን ከራሱ አውጥቶ የሚናገር አምላክ ሲሆን ማስተላለፊያ መንገዱ ግን የተለያየ ነው፦ እግዚአብሄር በቀጥታ ድምጹን ለሰዎች ያሰማል፣ አሰምቶአልም፤ ድምጹን በመላእክት አንደበት ያስተላልፋል፣ አስተላልፎአልም፤ እንዲሁም የነቢያትን አንደበት ተጠቅሞ ወደ ህዝቡ ድምጹን ሲያሰማ ኖሮአል፣ አሁንም ያን ያደርጋል። ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ቃል ቀጥሎ እንመለከታለን፦ ‘’ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ …
Continue reading ቃለ መለኮት(1…)
የስሜት አግባብነት[2…]
መንፈሳዊ ድንዛዜ ስሜትንም ይገድላል/ያደነዝዛል ውስጣችንን የሚያነቃቃ ነገር በሌለበት ሁኔታ ውስጥ የጠለቅ ሲሆን ፍላጎታችን የመቀዝቀዝ ሁኔታ ውስጥ ይሆናል፤ የመንፈስ ብርታት ሁለንተናን እንደሚያንቀሳቅስ ሁሉ ቅዝቃዜም መተሳሰር ያመጣል። በመንፈሳዊ ብርታት ውስጥ ስንገኝ የቃሉ ጥማት ይመጣል፣ የጸሎት መንፈስ ይበረታል፣ ቅድስና ገዢ ይሆናል፣ ህይወትም ይጸናል። መንፈሳዊ ቅዝቃዜ የድንዛዜ መገለጫ ሲሆን የሁሉ ነገር ፍላጎትና ጥማት መዘጋትና የፍላጎት ጥማት መዘጋት በመሆኑ የህይወት …
Continue reading የስሜት አግባብነት[2…]
