የእውነተኛው ሃይማኖት ብቸኛ መሳርያ ወንጌል ነው፤ የወንጌል ምስጢርም ክርስቶስ። ወንጌል የጌታን ድል ስለሚያውጅ ነፍሳትን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ይሰበስባል፣ ሃይል ያለው የትንሳኤ መንፈስ ስለሚሰራም ሃሰተኛ ትምህርቶችን ይዋጋል፣ በቃሉ አስተማማኝ ቃል-ኪዳን የገባ አምላክ ለሰው ልጆች አይዋሽምና በሙሉ የጸና የእምነት መሰረት ሆኖ ይኖራል። ወንጌል የሚታመን ዘላለማዊው የእግዚአብሄር አሰራር የተገለጠበትም አዋጅ ነው። ወንጌል በተለያዩ ዘመናት ከተነሱ የሃሰት ሃይማኖቶች በኩል …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(6… )
የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)
እግዚአብሄር ያመለከተንን አይተን ባንወደውም፣ ከፊታችን ያኖረውን ትእዛዝ ሰምተን ባንመርጠውም፣ ሃሌሉያ አሰኝቶ ባናመሰግንበትም እርሱ ያዘዘውና የተናገረው ነገር በሙሉ በጎ ውጤት አለው። የእግዚአብሄር ንግግር የተሻለ መንገድ አመልካች ነው፣ የተሻለ ህይወት አለው፣ የተሻለ መጨረሻም አለው። እግዚአብሄር ነገሮች ከመምጣታቸው አስቀድሞ ይናገራልና፣ ሁኔታዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ስለ እነርሱ ያመለክታልና፣ የድርጊቶቻችንን ውጤት እንድናውቅም ያመለክታልና፦ ስለዚህ እምቢታ ካሳየን ያለማስተዋላችንና ድምጹን ለመቀበል ያለመፍቀዳችን እጅግ …
Continue reading የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)
ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(5… )
ሃይማኖት በውጫዊና ውስጣዊ መገለጫዎች ይታወቃል አንድ ሃይማኖት በእምነት ደረጃ ሲገለጥ መሰረቱ መንፈሳዊነት ሲሆን ከዚያ በመነሳት የውስጣዊ ህይወትን ከእግዚአብሄር ጋር በማገናኘትና በስጋችንም እግዚአብሄርን እያከበርን በቅድስና እንድንኖር የተፈጠረልን መንገድ ነው። ሆኖም በምድር ላይ የምናገኛቸው ሃይማኖቶች ከእውነተኛነታቸው ሌላ መንፈሳዊነት የሚገዛቸው ብቻ ሆነው አናይም፤ እጅግ ብዙ ሃይማኖቶች በዘመናችን ተፈጥረዋል፣ ስጋን የሚያገለግሉና መመሪያዎቻቸው በአእምሮ ውጤቶች ላይ መሰረት ያደረጉ ሆነው …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(5… )
መንገዱን እየተነጋገርን እየተረዳንም
መንገድ መንገድ ስንል ምክኒያቱ ምድር ላይ የተዘረጋ አንድ በአቅጣጫ የሚመራ የጉዞ መስመር ላይ ለማተኮር አይደለም። ምድር ላይ በተዘረጋው መንገድ ላይ እለት እለት እንመላለሳለን፣ ይህ አዲስ ነገር አይደለም፣ ምስጢርም የለውም። በመንፈሳዊ ቋንቋ ውስጥ መንገድ ተብሎ ስለሚጠራው በምድራዊው መንገድ ስለተመሰለው ነው እዚህ ላይ የምናነሳው። በዚህ ርእስ ደጋግመን ብንነጋገር ጠቃሚ ነው፣ በየጊዜው መለስ ብለን ብናተኩርበት ተገቢም ነው፣ ምክኒያቱ …
Continue reading መንገዱን እየተነጋገርን እየተረዳንም
አለማዊነት(1..)
እግዚአብሄር ሲመለከት አለማዊነትን ከሃጢያት አለያይቶ አይደለም፤ ያም ሆኖ ቤተክርስቲያን አለማውያንን ለማዳን ስትል በርዋን አስፍታ ከፍታ በርህራሄ እንድትቀበላቸው እግዚአብሄር ፈቅዶአል። ነገር ግን ቤተክርስቲያን ነፍስን ለማዳን ባቀደችው አካሄድ ውስጥ ልትጠነቀቅና አለማዊነት እንዳያጠምዳትና እንዳይረባባትም በመጠባበቅ ተልእኮዋን ልትፈጽም ተገቢ ነው፤ ሰይጣን ሾልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ አለማዊነትን ይዞ ስለሚገባ መንፈሳዊ ህይወትን በመበረዝ ቤተክርስቲያንን ያዳክማል። አለማዊነት የተቆጣጠራቸው አማኞች ሲበዙ ጽድቅ ጥያቄ …
Continue reading አለማዊነት(1..)
በመጨረሻ የሚሆነው(1..)
በመጨረሻ ዘመን ይሆናል የተባለው እየሆነ፣ ቀረ የሚባለው ጥቂት ሆኖ እያለ የአዳም ልጆች ዘመኑን በጥልቅ ብናየው፣ ብናተኩርበት ተጥቃሚ እንደምንሆን መገንዘብ መልካም ነው፤ ጊዜው ካለፉት ጊዜያቶች ጋር እየተነጻጸረ፣ ሰአቱ ካለፉት ሰአቶች ጋር እየተመዘነ፣ ወቅቱ ከሄዱት ጋር ተመዝኖ ሁኔታው የሚፈቅደውን ሳይሆን እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ መሆን የነበረበትን ብናስተውል መልካም ነው። ዋስትና ያለው ህይወት ያስፈልገናልና፣ አለም ወደ ጥፋት ስትንደረደር አብረን …
Continue reading በመጨረሻ የሚሆነው(1..)
ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(4…)
Faith (ሃይማኖት) – stand fast in the faith- በሃይማኖት ቁሙ – obedient to the faith- ለሃይማኖት የታዘዙ – he had opened the door of faith unto the Gentiles- ለአሕዛብ የሃይማኖትን ደጅ ከፈተላቸው – Examine yourselves, whether ye be in the faith- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ – the household of faith- የሃይማኖት ቤተ ሰዎች – One …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(4…)
ቃለ መለኮት(4…)
ህያው የእግዚአብሄር ቃል ህይወትን ይሰጣል፣ ያም ብቻ አይደለም መንፈስን ያነቃል፣ ሃይልን ያጎናጽፋል። ‘’ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።’’ (ዘዳ. 8:3) የእግዚአብሄርን ቃል ድምጽ የሚያከብሩ ቅዱሳን አትኩሮታቸው ዘመናትን የሚሻገረው ግን የማይሻረው ህያው ቃሉ ላይ ነው። ሆኖም ብዙ ትውልድ …
Continue reading ቃለ መለኮት(4…)
የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (3..)
2.የመስቀሉ ቃል ተስፋ አለበት ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቶ እንደሚያድነን በብሉይ ኪዳን መጽሃፍት ላይ ተስፋ ተሰጥቶ ነበር፣ ይህንንም በተለያየ መንገድ አመልክቶአል። መጥቶ ያድናችሁዋል የተባለውም በመስቀሉ ላይ ዋጋ የሚከፍል በመሆኑ ነው። በኢሳ.25:6-12 ላይ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አንድ ቀን ለእስራኤል ሕዝብ ክርስቶስ በሚሰቀልበት ተራራ ላይ አለም ሳይፈጠር ያቀደውን አስደናቂ የማዳን ስራውን እንደሚገልጥ ተስፋ ይሰጣል፤ ያም የደህንነት መስዋእት …
Continue reading የመስቀሉ ቃል አጽንኦት (3..)
የመመለስ ትርፍ {2…}
በመመለስ ውስጥ ከምናገኛቸው አስፈላጊ ነገሮች መሃል የሚከተሉትም ይገኛሉ፦ መመለስ ወደ ጽድቅ ይመለሳል፦ ‘’እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።’’ (ሃስ. 3:21) የመሸሽ ውጤቱ ብዙ ነው፣ አንዱ ደግሞ ከጽድቅ መውደቅ ነው፣ ጽድቃችን ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ ከእርሱ በሸሸን ሰአት ከሰጠን ጽድቅ እየሸሸንና እየራቅን ሄደን በጨለማ ውስጥ …
Continue reading የመመለስ ትርፍ {2…}
