የጠላትን መንገድ እወቅ[2…]

ከጠላት ጋር ፊት ለፊት መተያየት ለሰላም ጉዳይ እንደተገናኙ ያህል በተከፈተ ልብ የሚቀባበሉት አጋጣሚ አይደለም ወይም ለመልካም ጉዳይ እንደተነፋፈቁ ወዳጆች ለመተያየት የሚጉዋጉለት አይደለም፣ የሚያስጨንቅ፣ የማያስደስት፣ ሰላማዊ ያልሆነም ነው፡፡ ጠላትነት ከጥላቻና ከበቀል ጋር ከሆነም ጥፋትን የቁዋጠረ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የተገናኘነው ያ የሚጠላን ቂም ቁዋጥሮ፣ በቀል አውጠንጥኖስ ቢሆን? ወይ አዘናግቶ ሊያጠቃ ቢሆንስ? ካልቻለ ሊያሰናክል ከቻለ ሊያጠፋ እንደሚያስብ ማለም …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[2…]

የማይፈሩ ልቦች

መንፈሳውያን በእምነት ተመርኩዘው በጽድቅ የሚደፍሩት ድፍረት አለ፡፡ በአምላካቸው ፊት ትሁትና የተገዙ ሆነው ይኖራሉ፤ በእርሱ ላይ ጠንካራ እምነት አላቸው፤ ልባቸው በቃሉ ላይ ሙሉ በመሆኑ ስለቃሉ ድፍረት አላቸው፣ነገር ግን አምላካቸውን የሚፈሩ ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር የሚተማመኑ ሰዎች አያፍሩም፤ ”አልፈራም እግዚአብሄር ይረዳኛል” ይላሉ፡፡የታመኑት አምላክ ፈጽሞ ፊት እንደማይነሳቸው እጅግ ስለሚተማመኑ ሞት ፊት እንኩዋን ቢቆሙ በልበ-ሙሉነት አምላካቸውን ይጠራሉ፣ ለዚህ እነ ዳንኤልን ምስክር …
Continue reading የማይፈሩ ልቦች

ሁሉን ትተን ተከተልን [2…]

እግዚአብሄር በፍቅሩ የጠራቸው ሰዎች የጠራቸውን አምላክ ታዝዘው በመውጣት ፈቃዱን ሲከተሉና ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ ጥሪውን ሰምተው ለመውጣት የፈቀዱ እነዚህ ታማኝ ሰዎች ታሪካቸው ለትምህርታችን እንዲነገር በቃሉ ውስጥ ተጠቅሰዋል፡፡ የጥቂቶችን ታሪክ አስቀድመን ያየን ሲሆን ከዚህ በመቀጠል ተጨማሪ ሰዎችን እናያለን፡- • አብረሃም ወገንና ቤተሰቦቹን ትቶ ወጥቶ ነበር አብረሃም እግዚአብሄር ወደ ነገረው ስፍራ ሲወጣ ሁሉን ነገር ትቶ በመከተል ነበር፡፡ ያኔ አብረሃምን …
Continue reading ሁሉን ትተን ተከተልን [2…]

አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[2…]

ክርስቶስ ኢየሱስ በመልከጼዴቅ ምሳሌነት ብዙ ባህሪውንና ተልእኮውን ለአለም ገልጦአል፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች ይህንን እውነት የሚያሳዩ ናቸው፡- • የዘር ሀረግ አልነበረውም ክርስቶስ ባህሪም ሆነ የዘር ሀረግ ከሰብአዊ አባትና እናት አልወረሰም፣ ስለዚህ ምድራዊ ጅማሬም ማለቂያም የለውም፡፡ የክርስቶስን ምድዊ የዘር ሀረግ መቀጣጠል የተሳናቸው እስራኤላውያን የዮሴፍንና የማርያምን የዘር ሀረግ እየሳቡ ከርሱ ጋር ሊያስጠጉ ሞክረዋል፡፡ቃሉ ግን እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነው ይላል(ራእ.1:8)፤ …
Continue reading አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[2…]

የጠላትን መንገድ እወቅ[1…]

ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ በሰራው መንፈሳዊ ስራ ድልን ያገኘው ነህምያ እግዚአብሄር ረድቶት ያሸነፈበትን ጥበብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡- ነህ.4:1-9 ”ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ። በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፡- እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።አሞናዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ። በድንጋይ …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[1…]

ምን እንስራ?[3…]

• እግዚአብሄር ምን እንድንሰራ ነው የሚፈልገው? ሮሜ.12:11-12 ”ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ…” የእግዚአብሄር ልጆች ቀዳሚ ስራ እግዚአብሄርን ማመንና መከተል እንዲሁም ሲሰራ መንገድ እንጂ እንቅፋት ያለመሆን ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በአባትነቱና በአምላክነቱ ካልወደደው ትክክለኛው የህይወት ይዘት ውስጥ ሆኖ ሊመላለስ አይችልም፡፡ አይሁድን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡- ዮሐ.8:39-42 ”መልሰው ፡- አባታችንስ …
Continue reading ምን እንስራ?[3…]

ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]

በጎውን፣ መልካሙንና የተሸለውን የጌታ ምህረት ለማግኘት የአለምን ፍቅር፣ የስጋን ምኞትና ሰይጣናዊ ልምምድን መተው፣ መሸሽና መጸየፍ ግድ ይላል፡፡ አመጽን ማቆም፣ ከክፉዎች መለየት፣ ወደተውነው ክፉ ልማድ ዳግም ያለመመለስ ውሳኔን በራስ ላይ ማሳለፍ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከተከለን ስፍራ ያለመልቀቅ፣ ከክፋት መራቅ፣ የራስን ለርሱ አሳልፎ መስጠትና የጌታን ፈቃድ መከተል የፈለግነውን የጌታ ምህረት እንድንቀበል ያግዘናል፡፡ ጌታን መከተል፣ ቃሉን በፈቃደኝነት መቀበል፣ …
Continue reading ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]

አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ (በእብራይስጥ ሲጠራ መሲህ/የተቀባ) የተባለ፣ ሁለተኛው ሰው ሲል ቃሉ የጠራው፣ የሰው ልጅ ሲል እርሱ ራሱን ያስተዋወቀው ለእግዚአብሄር አላማና የዘላለም ፈቃድ አስፈጻሚነት የተቀባ ሰማያዊ ሰው ነው፡፡ ሰዎች እርሱን ማን ሲሉ እንደሚጠሩት ጠየቀ፡- ” ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፡- ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም መልሰው፡- መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፡- ኤልያስ፥ …
Continue reading አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]

የዝምታ ድምጽ

ዝምታ ምን አይነት ድምጽ ሊያሰማ ይችላል? ወይም ዝምታና ድምጽ እንደምን ይገናኛሉ? ዝምታ ያለ ድምጽ የሆነ ክስተት ሲሆን ድምጽ ከሚሰማ ቃል ጋር በመሆኑ ሁለቱ በተቃራኒ በኩል ሳሉ በአንድነት ትርጉም ያላቸው እንዲሆኑ ተደርገዋል፤ የቻሉት ግን የእግዚአብሄር አሰራር በመሆናቸው ነው፡፡ በዝምታ ውስጥ ምን ልንሰማ እንችላለን? ምን አይነት ድምጽስ በዝምታ ውስጥ ሊሰማ ይችላል ብለን መጠበቅ እንችላለን? እንደ ሰው ግን …
Continue reading የዝምታ ድምጽ

እንደሚጠበቀው መመላለስ

ወደ ከበረው ዘላለማዊ መንግስትና ወደ ቅዱሳን ማህበር ሊገባ የወሰነ አንድ ትውልድ ቅድሚያ የነፍሱን ደህንነት ሊያረጋግጥና አስተማማኙን መንፈሳዊ ማህተም ሊታተም ይገባዋል (ዮሀ3፡5)፡፡ ያን ማረጋገጫ በቅዱሱ አምላክ ስም በሚሆን የሀጢያት ስርየትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚቀበል መሆኑን የቃሉ አጠራር ያረጋግጣል፡፡ ይሄ እርግጠኛና እጅግ አስፈላጊ የሆነ የእግዚአብሄር አሰራር ወደ መንግስቱ የሚያስገባ ቢሆንም ታላቁ ድል ሙሉ የሚሆነው እግዚአብሄር በሚሰጠው ቀሪ …
Continue reading እንደሚጠበቀው መመላለስ