እንደተከፈለልን ለመመላለስ ከወሰንን እግረመንገዳችንን ከእግዚአብሄር የተቀበልነውን ስጦታ እንደ ክብሩ መጠን መያዝ እንዲገባን ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ የተሰጠን መዳን የተከፈለውስ የዋጋው ተመን ምን ያህል ነው? ስንል መጠየቅም ተገቢ ነው፡፡ በእርግጥ መዳን ሰዋዊ የዋጋ ተመን ከቶ የለውም፣ ስለዚህ ልኬት አይወጣለትም፣ ተመንም አይተመንለትም፤ የሰው ክፍያ ሊመጥነው ሆነ ደረጃ ሊሰጠው አይችልም፡፡ ሰው ግን ያን ያገኘውን ታላቅ ነገር እጅግ ተጠንቅቆና አክብሮ በእውቀት …
Continue reading እንደተከፈለልህ ተመላለስ (2..)
ኢያሪኮን መስራት? (2..)
ኢያሪኮ ፈርሶ እንደቀረ የተደመደመ ጉደይ ሆኖ ሳለ በአእምሮ ውስጥ ትዝታው አልለቅ ካለ የቀደመው ሀጢያት ከልብ ሊርቅ አልቻለም እንደማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ኢያሪኮን ለምን ረገማት? ኢያሪኮ ማለት ከተማዋ፣ አካባቢዋ ወይም የኑሮዋ ስርአት ብቻ ሳይሆን የአምልኮ ልማድዋን ተከትሎ የተፈጠረው ያልተገባ የህይወት አኑዋኑዋር ሁሉ ማለት ነው፡፡ ኢያሪኮ የአህዛብ ከተማ በመሆንዋ የአህዛብ ልማዶችን የተሞላች ስለመሆንዋ አያጠራጥርም፡፡ ልማዶችዋ እግዚአብሄርን የሚያስደስቱ አልነበሩም፡፡ …
Continue reading ኢያሪኮን መስራት? (2..)
አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)
እግዚአብሄርን በማወቅና ባለማወቅ መሀል ያለው ልዩነት የሞትና የህይወት ያህል ዋጋ እንዳለው ጌታ ኢየሱስ በአጽንኦት ተናግሮአል፡፡ ጌታ በዮሐ.17:3 የተናገረው እንዲህ ይላል፡- ”እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” በትንሹ ልባችን ስለርሱ ባወቅነው እውቀት ምክኒያት ያገኘነውን ታናሽ እምነት ይዘንና ወደ እርሱ ቀርበን አላፈርንም፤ እንዲያውም ከርሱ ጋር በምንኖርበት ዘመን ሁሉ ሳይነቅፈን …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)
ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]
ህዝቡን የሚያድን አምላክ ለሰው ልጆች የሆነ የማዳኑን ብስራት ሲገልጥ በሰማይ የተገለጠው ትእይንት ልብ የሚሞላ ነው፡- ”እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም …
Continue reading ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]
እንደተከፈለልህ ተመላለስ (1..)
አይሁድ ሳለህ ተከፈለልህ፣ ወይስ አህዛብ ሳለህ? 1ቆሮ.7:17 ”ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ።” የተጠራንበት ወቅት ላይ ተማሪ፣ ወታደር፣ ቢሮ ሰራተኛ፣ የቤት እመቤት እንሆን ይሆናል፡፡ ትዳር ውስጥ ልንሆን እንችላለን፣ ያላገባን ልንሆን እንችላለን፣ የተፈታ ትዳር ውስጥም ልንሆን እንችላለን፣ መበለት ልንሆን እንችላለን፣ ጡረተኛ ወይም ሌላም ሌላም፡፡ በየትኛውም ህይወት …
Continue reading እንደተከፈለልህ ተመላለስ (1..)
ኢያሪኮን መስራት? (1..)
• ኢያሪኮ ይፍረስ በሙሴ ዘመን የኢያሪኮ ከተማ የእግዚአብሄር ፈቃድ የሌለባት ስፍራና የአመጸኛ ህዝብ ምልክት የነበረች ነች፡፡ የአመጽ ልማድ የነገሰባት፣ ጣኦት የሚገዛባት፣ ስርአት የሌለባትና እግዚአብሄር የማይፈራባት ስፍራ ስለነበረች በርሱዋ ውስጥ የእግዚአብሄር ፈቃድ መገለጥ አይችልም ነበር፤ የከተማዋ ህዝብ እግዚአብሄርን ሳይሆን ጣኦትን የሚከተልና የሚያመልክም ነበር፡፡ ስለዚህ በርስዋ ያለ ምድር ከጣኦት የተነሳ የረከሰ ፣ ህዝቦችዋ ከእግዚአብሄር ጋር ሳይሆን ከአጋንንት …
Continue reading ኢያሪኮን መስራት? (1..)
አንተ ግን ያው አንተ ነህ (1…)
ንጉስ ዳዊት የህይወት ዘመኑ ወደ ማለቅ ቢፈጥንም የፈጠረው አምላክ ግን ያለመለወጥና ያለመናወጥ ጸንቶ እንደሚኖር እጅግ ያስተዋለ ሰው ነበረ፤ ስለዚህ እንዲህ ሲል በመዝ.102:11፣23-28 ውስጥ ተናገረ፡- ”ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።… የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ። በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው። አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (1…)
ህዝቡን የሚያድን አምላክ[1..]
ሰውን ለማዳን በጎ ፈቃዱ የሆነና ሁሌም ሊገለጥ የሚፈቅድ አምላክ ሲናገር ተመልከቱና አስተውሉ እንጂ ለማዳን፣ ለመፈወስ፣ ለመምታትም ሆነ ለመግደል የምችለው እኔ እግዚአብሄር ብቸኛው አምላክ ነኝ፣ ይህን እወቁም ሲል አዋጅ ይናገራል፡፡ በተለይ በዘዳ.32:39 ላይ ብርቱ ቃል ሲናገር፡- ”አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ የሚያድን የለም።” እግዚአብሄር …
Continue reading ህዝቡን የሚያድን አምላክ[1..]
የፍቅር ግዛቶች [5..]
የፍቅር ክልል በስፋት፣ በርዝመትና በጥልቀት የማይለካ ግን ልብን አእምሮንና ነፍስን የሚቆጣጠር ብርቱ ሀይል፣ ሰውንም ያለጉልበት መግዛት የሚችል ታላቅ መለኮታዊ ስጦታ ነው፡፡ ክፉ የተባለውን የሰው ልብ ሌላ ምን አይነት ጉልበት ሊያቆመው ችሎአል? እርሱን ለመለወጥ የሚችል ፈቃድስ ምን ነበር? እግዚአብሄር ለብዙ ዘመናት ቃሉን፣ ህጉን፣ ስርአቱንና መንገዱን ቢሰጥም የሰው ልብ እሺ ብሎ የተገዛው መቼ ነበር? እግዚአብሄር ግን ያን …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [5..]
እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
የጌታ ደቀመዛሙርት ቅድሚያ ሊሰጡዋቸው ከሚገቡ ነገሮች ፊት የሚገኘው (አውራና መሰረት የሆነው) የመንፈሳዊ ህይወት ጤንነት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወት እንደ ስጋ ያለ ቁመና፣ ፍላጎት ወይም ስሜት ስለማይኖረው የጤንነቱ መለኪያ በስጋ ከሚደረገው ጋር አይመሳሰልምና የተለየ መፍትሄ የሚሻ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወታችንን የሚመረምርና የሚያክም የእግዚአብሄር መሳሪያ የሆነው ህያው ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ ስለሚሰራው ስራ መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ”የእግዚአብሔር …
Continue reading እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
