ስለእግዚአብሄር ማንነት በሚወራበት ስፍራ ሁሉ ከእርሱ ጋር ስለፍቅር ሳይነሳ መታለፍ አይችልም፤ ፍቅር የእግዚአብሄር ታላቅ ባህሪ በመሆኑ በተለይ ለእኛ የእግዚአብሄር ፍቅር ማለት እጅግ ብዙ ትርጉም አለውና እርሱን አንስተን ብናወራ፣ ደጋግመን እግዚአብሄር ስለእኛ የገለጠውን የፍቅር ብርታት ብናስታውስ ሲያንስ እንጂ አይበዛም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ፍቅር እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ፍቅር እንደመሆኑ ሁሉ ይመኩበታል፣ ሁሉ ይጠጉታል፣ ሁሉም ያምኑበታል፡፡ ፍቅሩ ረቂቅና ጥልቅ …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [6..]
ለመመለስ መንቃት
የአምነት ጉዞንና የባህር ጉዞን የሚያመሳስሉ ሰዎች አሉ፤ ምክኒያታቸውን ሲያስረዱ አንድ ሰው የእምነት ጉዞን ሲጉዋዝ አገኛለሁ ብሎ የሚጠብቀውን መንፈሳዊ ነገር ተስፋ አድርጎ እንጂ በእጁ ጨብጦ የሚጉዋዝ አለመሆኑ፣ በባህር ላይ የሚደረግ ጉዞም የሚታይ ነገር ከፊት ሳይኖር በእምነት ብቻ መዳረሻን አልሞ ወደተገመተ አቅጣጫ የሚቀዝፍበት መሆኑ ነው፤ ባህርተኛው በእምነት ከሆነ ጊዜ በሁዋላ እደርሳለሁ ወዳለው ሩቅ ስፍራ እንደሚደርስ በማሰብ የሚጉዋዝም …
Continue reading ለመመለስ መንቃት
አዲስ ኪዳን ምልክት (2..)
የአዲስ ኪዳን ምልክት ሰው በብሉይ ኪዳን የነበረ አንድ ነቢይ በህይወቱ የተከናወነ አዲስ ልምምድ ማስተናገዱ ከግርምት ባለፈ ለትውልዱ የሚያበስረው ትልቅ ምልእክት ነበረው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ይባላል፣ ይህ ነቢይ በአንድ ወቅት ከእግዚአብሄር ፊት የሚኮበልልበት ሰበብና ጥሪውን ወደ ሁዋላ የሚያደርግ ድካም ገጥሞት ነበር፤ እግዚአብሄር ግን መኮብለሉን አይቶ ሳይተወው በመከታተል እስከተደበቀበት ስፍራ እስከ ጥልቅ ድረስ ወርዶ የሚያስተምረውን እርምጃ ሲወስድበት ይታያል፡፡ …
Continue reading አዲስ ኪዳን ምልክት (2..)
የአይን ነገር(2…)
አይን፣ ጆሮና ልብ ተቀናጅተውና በበጎ ልቦና ቁጥጥር ስር ሆነው በህይወታችን ቢሰሩ ህሊና ውጤታማ ስለሚሆን የጽድቅ ፍሬ ያሳያል፤ ለምሳሌ አይን በተገቢው መንገድና በተገቢው ስፍራ ተገቢ ነገር እንዲያይ ቢቃኝ ከፈተና ይጋረዳል፤ ጆሮም ከሚፈትን ድምጽ ቢጠነቀቅ ልብን ከክፉ ውሳኔ ይመልሳል፣ ዛሬም ቀድሞም ከሚሰማው ያልተገባ ነገር የተነሳ ልባችን በተሳሳተ ውሳኔ ሲመራ ስለኖረ ብዙ የህይወት ውጣ ውረድ፣ ፈተናና ስብራት በሰው …
Continue reading የአይን ነገር(2…)
የአይን ነገር(1…)
የአይን ነገር የብዙ ነገር ጉዳይ ነው፡- አይንን አስበን ወደ ምንነቱ፣ ወደ አፈጣጠሩ፣ ወደ ግልጋሎቱ እያነጣጠርን ስናጠና የእርሱን አስፈላጊነት የምናጎላበት ምክንያት ተገቢ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ባለአይን/ አይናማ ሰው ይህችን አለም በማየት እውቀት ስለሚኖራት የማየት ችግር ካለባቸው አይነስውራን ይልቅ የእርስዋን ግፊት የመቁዋቁዋም አቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ እንቅፋቶችን አይናማው ሰው መሻገር የሚችላቸው ቢሆንም የእይታ ግርዶሽ ለገጠመው ግን ፈተና …
Continue reading የአይን ነገር(1…)
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር
የአምላክ ምስጋና ሊያውም በሰንበት ቀን (በእግዚአብሄር እረፍት ውስጥ) የሚቀርብ እጅግ የላቀ ደስታና ምህረት የሚያመጣ በመሆኑ ዘማሪው ንጉስ ያን አስተውሎ በመዝሙሩ ጅማሬ በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር ይላል፡፡ ሲቀጥልም፡- ”እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብርንም ለበሰ፤ እግዚአብሔር ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም ከዘላለም ነህ። አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ …
Continue reading በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር
የመለያችን ምልክት (1..)
እግዚአብሄር ምልክት የሚያኖርባቸው ሰዎች በእግዚአብሄር የታዩ ሰዎች ናቸው፤ በእርሱ ከለላ ውስጥ ያሉ በአላማው ውስጥ የተቀመጡም ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር እቅድ ላይ በክፋት የተነሳው ቃየን እንኩዋን ከሚያገኘው ክፋት ይጠበቅ ዘንድ በሰዎች ዘንድ የመጀመሪያ የሆነውን ምልክት ከእግዚአብሄር ተቀብሎአል፡፡ ይህ ምልክት እርሱን በሰራው ሀጢያት ከመጥፋት የሚታደገው የእግዚአብሄር ምልክት ነበር፡፡ እግዚአብሄር ለራሱ ለለየው ህዝብ ደግሞ የተለየ ጥበቃ በማድረግ ምልክት በላዩ ላይ …
Continue reading የመለያችን ምልክት (1..)
የማንበቃበትን እክል መሻር
የማንበቃበት ነገር፡- በእግዚአብሄር መገኛ አካባቢ ይዘን የምንመላለሰው ነገርና አካሄዳችን በማንነታችን የሚደነቃቀፍ ሲሆን፣ የምንመራበት የህይወት መርህ ደካማ ሆኖ ያለን የህይወት ይዘት የማይበቃ ሆኖ ሲቆጠር፣ የእግዚአብሄር ቃል የሚቃወመው የህይወት ይዘት ሲኖረን፣ መርሀችን የተተወ/መታሰቢያ የማይገኝለት መርህ ከሆነ ያም ከአለም ልማድ እንዳንወጣ ካነቀን፣ ከመንፈሳዊ የህይወት ደረጃ የተጣለ/በአለም ብቻ ተቀባይነት ያለው ቃሉ ግን የሚኮንነው ልማድ ካለን፣ የተወገደ/በእኛ ቁጥጥር ስር የሌለ …
Continue reading የማንበቃበትን እክል መሻር
የህይወት ህያውነት
አዲሱ ህይወታችን በጌታ ኢየሱስ አሰራር የተፈጠረ ለዘላለም የሚኖር ዳግም የተወለደና መንፈሳዊ ነው፡፡: ይህ ህይወታችን በምድር ላይ እንደሚሆነው ሁሉ በመንፈሰዊውም አለም ህያው ሆኖ እንዲቀጥል ያስፈልጋል፡፡ህይወታችን አሁንም ቀጥሎም፣ ዛሬም ነገም ህያው እንዲሆን ከጌታ ከኢያሱስ ጋር ህያው መስመር ሊኖረው ይገባል፡፡ ጌታ በመንፈሱ እለት እለት ሊያጠጣው፣ ሊያለመልመውና ህያው ሊያደርገው ከእርሱ ጋር መጣበቅ የግድ ነው፡፡ ዳግም የተወለደው ሰው በጌታ ህያው …
Continue reading የህይወት ህያውነት
የውሳኔና ስምምነት አግባብ ‹2…›
ከእግዚአብሄር ጋር መስማማት ቃሉ ተስማምተን ከእግዚአብሄር ጋር ስንኖር የሚሆነውን ሁኔታ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፡- ”የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትጠብቅ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለልህ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል። የምድር አሕዛብም ሁሉ የእግዚአብሔር ስም በአንተ ላይ እንደ ተጠራ አይተው ይፈሩሃል። እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ …
Continue reading የውሳኔና ስምምነት አግባብ ‹2…›
