ጥርጥር ጠላት(2…)

ጥርጥር የተስፋ ጠላት ነው ተስፋ ነገን መመልከቻ መነጽር ነው፤ ተስፋ የሌለውን ነገር እንዳለና ሩቅ ያለንም አቅርቦ መመልከቻ መነጽር ነው፤ ተስፋ በእግዚአብሄር በመታመን ምክኒያት ያደርገዋል ብለን የምንጠባበቅበት መያዣችን ነው። ተስፋ ይመለከታል፣ ተስፋ በልቦና እጅ በመታገዝ ከሩቅ ያለውን ነገር አቅርቦ ይጨብጣል፣ በዚህ ምክኒያት የእግዚአብሄር ህዝብ በመንፈስ እጁን እየዘረጋ የእግዚአብሄር የሆነውን ሁሉ በእምነት ይጨብጣል፣ በእውን እስከሚያገኝ ከእግዚአብሄር ጋር …
Continue reading ጥርጥር ጠላት(2…)

ከሰማይ እውቀት መጉደል[3…]

የሰማይ እውቀት የሰማይ የሆነው፣ የመለኮት የሆነው፣ መንፈሳዊ የሆነው ሲሆን ከምድራዊ እውቀት፣ ምጥቀት፣ ፍልስፍናም ይባል ጥልቅ የአጋንንት እውቀት፣ ከነዚህ በላይ የሚልቅ፣ የተለየ፣ የተቀደሰ፣ ሃይል ያለውና አሸናፊ እውቀት የሆነ እርሱ የሰማይ እውቀት ስለሆነ ለእግዚአብሄር መንግስት ማብቃት የሚችልና ከእግዚአብሄር ምንጭ የሚቀዳ መሆኑ የታመነ ነው። የሰማይ እውቀት በመሰረታዊነት በቃሉ ይገለጻል፦ ዳን.10:9-11 ”የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ …
Continue reading ከሰማይ እውቀት መጉደል[3…]

የመሰረቱ ማጠንጠኛ (1…)

መሰረት ማለት? መሰረት መነሻ ነው፣ መሰረት መቆሚያ ነው፣ መሰረት የእድገት መጀመሪያ ነው፣ መሰረት ስር ነው፣ መሰረት መስፋፊያ ነው፣ መሰረት መታመኛ ነው፣ መሰረት አቁዋም ነው፣ መሰረት መታወቂያ ነው፣ መሰረት ምንጭም ነው። እያንዳንዱ ነገር መሰረት ያለውና በዚያ ላይ የቆመ፣ የታነጸና ያደገ ነው። ለምሳሌ የምድር መሰረት በእግዚአብሄር ስለተመሰረተ የማይናወጥ ሆኖ ይኖራል። እንዲያውም መሰረቷ ቢናወጥ የሚያናውጣት ሌላ ሃይል ሳይሆን …
Continue reading የመሰረቱ ማጠንጠኛ (1…)

ጥርጥር ጠላት(1…)

• ጥርጥር የእምነት ጠላት ነው። • ጥርጥር የተስፋ ጠላት ነው። • ጥርጥር የመዳን ጠላት ነው። • ጥርጥር የመጎብኘት ጠላት ነው። • ጥርጥር የሞገስ ጠላት ነው። • ጥርጥር የምህረት ጠላት ነው። • ጥርጥር የጽናት ጠላት ነው። • ጥርጥር የፍቅር ጠላት ነው። • ጥረጥር የሰላም ጠላት ነው። • የሚጠራጠር አያምንም፣ ስለማያምን አይጸናም። • የሚጠራጠር ተስፋ አያደርግም፣ ተስፋ …
Continue reading ጥርጥር ጠላት(1…)

ከሰማይ እውቀት መጉደል[2…]

በእግዚአብሄር ከፍ ላለ ህይወት ተጠርተው ያሉ ወገኖች የእግዚአብሄርን ፈቃድ ባለማስተዋልና ባለመከተላቸው ምክኒያት የሰማይ እውቀት ጎደሎ ሲሆንባቸው ኖሮአል። ወደ እግዚአብሄር የተጠጋ የእግዚአብሄርን መንገድ ግን ልብ የማይል ሁሉ ከእውቀት በመጉደሉ በብዙ ይጎዳል። አንድ የእስራኤል መምህር የሆነ ቆርኖሌዎስ የተባለ ሰው በጌታ ፊት ቀርቦ ሲነጋገር ያን ችግር አጉልቶ ሲያሳይ ነበር፡፡ ይህ ሰው በአዋቂዎች ቦታ የተቀመጠ ሌሎችንም በእግዚአብሄር ቃል የሚመራ …
Continue reading ከሰማይ እውቀት መጉደል[2…]

ጊዜ ጌታ? [2..]

– ጊዜ ጌታ? የቀን ምንነት ለሚያሳስበውና ለሚመረምረው አንድ የሚታየው ጉልህ እውነት የነገው እለት ከዛሬው ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው፤ ቀን ቀለም የለው የትኛውም እለት አይወዳደርበትም፣ አንዱ ከሌላው ከፍና ዝቅ አይል እግዚአብሄር እኩል አድርጎና ወስኖ ፈጥሮታል፣ ሰው በእርሱ ላይ ተጽእኖ የለውም ስለዚህ እንደተፈለገው ሊዘወር አይቻልም… ሰለዚህ የትላንትናው ቀን የነበረው ሰአት ዛሬም አለው፣ ነገም ከነገ ወዲያም እንዲሁ፤ ዋናው …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [2..]

አንተ ግን ያው አንተ ነህ (3…)

ዕብ13:8 ስለ ጌታ ኢየሱስ ማንነት እንዲህ ይላል፡- ”ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።” ጌታ ኢየሱስ ሞቶ አልነበረም ወይ? የሚሉ አሉ፡፡ አዎ ሞቶ ነበር፣ ሞቱ ግን ዘላለማዊነቱ ላይ ምን ተጽእኖ ነበረው? እርሱ ራሱ ስለራሱ ተናግሮአል፡- ”ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (3…)

የውሳኔና ስምምነት አግባብ (3…)

ወስኖና ተስማምቶ መኖር ንጉስ ዳዊት ስለ እግዚአብሄር ማንነት ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ስነለነበር ከእርሱ ጋር ተስማምቶ ለመኖር (ሲሳሳት እንኩዋን ፈጥኖ በይቅርታ ለመስማማት) የማያቅማማ ሰው ነበር፡፡ ይህ ፍላጎቱም የተሳካለት ሰው ነበር፡፡ በመዝ.130:3-8 ውስጥ ሲናገር፡- ”አቤቱ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና። አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች። ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት …
Continue reading የውሳኔና ስምምነት አግባብ (3…)

የፍቅር ግዛቶች [7..]

ፍቅር ጥልቅና ሰፊ መለኮታዊ ባህሪ ያለው ነገር ነው። ሰው ስለፍቅር ያለው ግንዛቤና ትርጉዋሜ በእርግጥ ወደ ስጋዊነት የሚያጋድልና ይበልጥ ሰዋዊ ነው። ወደ ስጋዊነት የሚያደላ እንደመሆኑ በአብዛኛው መገለጫው የሚሆነው ስሜት ሲሆን ሰዋዊ እንደመሆኑ የፍቅር ግንኙነቱ የሚያጋድለው በሰውና በሰው መሀከል ነው ማለት ነው። እርግጥ ነው ፍቅር በሰው መሃል ይኖር ዘንድ የፈቀደው የፈጠረን አምላክ ነው። ነገር ግን በሰው መሃል …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [7..]

ጊዜ ጌታ? [1..]

  የሁሉ አምላክ እግዚአብሄር ስለእኛ ሲል ጊዜን ፈጥሮአል (ዘፍ.1.14-17)፡- ”እግዚአብሔርም አለ፡- ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [1..]