እንደተከፈለልህ ተመላለስ (1..)

አይሁድ ሳለህ ተከፈለልህ፣ ወይስ አህዛብ ሳለህ? 1ቆሮ.7:17 ”ብቻ ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር እንደ ከፈለለት እያንዳንዱም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይመላለስ። እንዲሁም በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እደነግጋለሁ።” የተጠራንበት ወቅት ላይ ተማሪ፣ ወታደር፣ ቢሮ ሰራተኛ፣ የቤት እመቤት እንሆን ይሆናል፡፡ ትዳር ውስጥ ልንሆን እንችላለን፣ ያላገባን ልንሆን እንችላለን፣ የተፈታ ትዳር ውስጥም ልንሆን እንችላለን፣ መበለት ልንሆን እንችላለን፣ ጡረተኛ ወይም ሌላም ሌላም፡፡ በየትኛውም ህይወት …
Continue reading እንደተከፈለልህ ተመላለስ (1..)

ሰላም ለናንተ ይሁን[3ኛ…]

ምክረ ሰላም ”እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው።”(1ቆሮ.14:33) ግን አንዳንዴ ሁከት ሲያስጨንቀን፣ ሰላም አጥተን ስንባዝንና እፎይ ያልንበት ጊዜ እስካይታወሰን በፈተና ስንቅበዘበዝ ወደ እኛ ተመልሶ የመምጣቱ ነገር ያጠራጥረናል፤ በእውነተኛ ትርጉሙም ላይ ጥያቄ በማንሳት ሰላምን እንነቅፋለን፤ እርሱ ማን ነው? እስከማለት እንደርሳለን፡፡ በእርግጥስ ሰላም ለእኛ ምንድነው? አንጻራዊውን ሰላም ለማለት አይደለም፤ …
Continue reading ሰላም ለናንተ ይሁን[3ኛ…]

ሰላም ለናንተ ይሁን[2ኛ…]

የአለም ህዝቦችና መንግስቶቻቸው ምድርን ለሚንጠው ሁከት ሰላምን በማፈላለግ ብዙውን ዘመናቸውን ፈጅተዋል፡፡ ሰላምን ለማምጣት ብዙ መክረዋል፣ በህብረት ለፍተዋል፣ አጥፊው ላይ ወስነዋል፣ የተጣሉትን ሊያስታርቁ ደክመዋል፤ ነገር ግን እንደልፋታቸው መጠን የተሻለ ነገር በአለም ላይ አልመጣም፡፡ ይህንም ይሁን ያን እርምጃ ይውሰዱ፣ በዚህኛውም ይሁን በዚያኛው ብልሀት ይሂዱ ያልደረሱበት ጥበብ እንዳለ እናያለን፤ የሰላም ጎዳና ወዴት መሆኑን እንዳላስተዋሉትም እንረዳለን፤ የምንጩን ማንነት አልደረሱበትማ፡፡ …
Continue reading ሰላም ለናንተ ይሁን[2ኛ…]

ሰላም ለናንተ ይሁን[1ኛ…]

የሰላማ አላማ እግዚአብሄር ወደ እኛ ዘንድ የሚመጣው እረፍትን ሊሰጥ ሲሆን ቀርቦ በምህረት ሲጎበኘንም በሚሰጠን እረፍት በኩል ህይወታችንን ማጽናት እንዲሁም የከበበንን ውስጣዊ ሆነ ውጫዊ ጫናና ሁከት ማራቅና በሰላም ማሳረፍ ነው፡፡ የሰላም መሰረት በሰዎች ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ እንዳለው የሚያውቅ አምላክ ወደ አለምና ወደ ሰው ልጆች ሲመለከት ቅድሚያ ትኩረት የሚያደርገው የጠፋብን ሰላም ላይ ነው፡፡ በዘኊ.6:25-27 ያለው ቃል …
Continue reading ሰላም ለናንተ ይሁን[1ኛ…]

የጠላትን መንገድ እወቅ[2…]

ከጠላት ጋር ፊት ለፊት መተያየት ለሰላም ጉዳይ እንደተገናኙ ያህል በተከፈተ ልብ የሚቀባበሉት አጋጣሚ አይደለም ወይም ለመልካም ጉዳይ እንደተነፋፈቁ ወዳጆች ለመተያየት የሚጉዋጉለት አይደለም፣ የሚያስጨንቅ፣ የማያስደስት፣ ሰላማዊ ያልሆነም ነው፡፡ ጠላትነት ከጥላቻና ከበቀል ጋር ከሆነም ጥፋትን የቁዋጠረ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የተገናኘነው ያ የሚጠላን ቂም ቁዋጥሮ፣ በቀል አውጠንጥኖስ ቢሆን? ወይ አዘናግቶ ሊያጠቃ ቢሆንስ? ካልቻለ ሊያሰናክል ከቻለ ሊያጠፋ እንደሚያስብ ማለም …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[2…]

የጠላትን መንገድ እወቅ[1…]

ጠላትን ፊት ለፊት ተጋፍጦ በሰራው መንፈሳዊ ስራ ድልን ያገኘው ነህምያ እግዚአብሄር ረድቶት ያሸነፈበትን ጥበብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡- ነህ.4:1-9 ”ሰንባላጥም ቅጥሩን እንደ ሠራን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድም አላገጠ። በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊትም ፊት፡- እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሠሩት ምንድር ነው? ይተዉላቸዋልን? ይሠዋሉን? በአንድ ቀንስ ይጨርሳሉን? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ያድኑታልን? ብሎ ተናገረ።አሞናዊውም ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ። በድንጋይ …
Continue reading የጠላትን መንገድ እወቅ[1…]

እንደሚጠበቀው መመላለስ

ወደ ከበረው ዘላለማዊ መንግስትና ወደ ቅዱሳን ማህበር ሊገባ የወሰነ አንድ ትውልድ ቅድሚያ የነፍሱን ደህንነት ሊያረጋግጥና አስተማማኙን መንፈሳዊ ማህተም ሊታተም ይገባዋል (ዮሀ3፡5)፡፡ ያን ማረጋገጫ በቅዱሱ አምላክ ስም በሚሆን የሀጢያት ስርየትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚቀበል መሆኑን የቃሉ አጠራር ያረጋግጣል፡፡ ይሄ እርግጠኛና እጅግ አስፈላጊ የሆነ የእግዚአብሄር አሰራር ወደ መንግስቱ የሚያስገባ ቢሆንም ታላቁ ድል ሙሉ የሚሆነው እግዚአብሄር በሚሰጠው ቀሪ …
Continue reading እንደሚጠበቀው መመላለስ

ቸል ባይ ተዋጊ[2…]

ቸል ባይ ተዋጊ አስቀድሞ ራሱን ያስጠቃል፤ ትጥቁን ስለማይጠብቅ፣ ራሱን በአግባቡ ስለማያሰማራ፣ በንቃትና በጥንቃቄ ስለማይመላለስ እንዲሁም ቸልተኝነት ስለሚያበዛ ድንገት ጠላት ይጎዳዋል፡፡ ከራሱ አልፎም የተደገፈው ወገኑን የሚያስጠቃ ስህተት ይፈጽማል፤ ሀላፊነቱን ባለመጠበቅ፣ የተጣለበትን አደራ ባለማቆየትና ለባልንጀራው መከታ ባለመሆን ለጠላት ያጋልጣል፡፡ የምድራዊ ሀይል ከላይ እንዳለው አይነት ሽንፈት ላለማስተናገድ ሲል ቢያንስ ወደ ውጊያ የሚልከውን ወታደር ሃላፊነት/ሸክም ይሰጠዋል፤ ወታደሩ ደግሞ በተመደበበት …
Continue reading ቸል ባይ ተዋጊ[2…]

እስራኤልም ወደ ያእቆብ

እስራኤል ወደ ያእቆብ ወይስ ያእቆብ ወደ እስራኤል ነበር ለውጡ ? ወንድሙን ያታለለው ያእቆብ የእግዚአብሄርን አላማ ያስፈጽም ዘንድ ማንነቱ በእግዚአብሄር ተቀይሮ ስሙ እስራኤል ተብሎ ነበር፡፡ አባቱን ሳይቀር በመመሳሰል ያሳተው ይህ ያእቆብ በፈቃዱ ብኩርናውን ካቃለለው ከወንድሙ ከኤሳው የፈለገውን ብኩርና በወጥ ገዝቶ ይቀበል እንጂ የፈጸመው አመጽ ችግር ላይ የሚጥለው ነበር፤ በወቅቱ አባቱና እናቱ ስለራሩለት ብቻ ከተግሳጽ አምልጦአል፡፡ እግዚአብሄር …
Continue reading እስራኤልም ወደ ያእቆብ

ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]

ባላንጣዎች ሁሌም በቅራኔ ውስጥ ያሉ ወገኖች ናቸው፡፡በውጊያ ሜዳ ይገናኙ እንጂ ከመፋለም ወደሁዋላ አይሉም፡፡አሸናፊ ለይቶ አንዱ ለሌላው እጅ ሳይሰጥም ፍልሚያው አያቁዋርጥም፡፡ በሁለቱም ተዋጊዎች በኩል በየጊዜው ለውጊያ ዝግጅት አለ፤ ላለመሸነፍ እጅ ላለመስጠትና ላለመገዛት ትግል አለ፡፡የተያዘም እንዲሁ ያመልጥ ዘንድ እስከሞት በሚደርስ ትግል ሳያቁዋርጥ ለነጻነት ይታገላል፤ ይህ የውጊያ ተፈጥሮ ነው፡፡ ውጊያ መንፈሳዊም ስጋዊም ነው፡፡ ስጋዊ ውጊያ በማይግባቡ፣ በተጣሉና ጦርነትን …
Continue reading ያልተሰናዳ ተዋጊ[1…]