ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )

ብቸኛውና ፍጹሙ ሃይማኖት መለኮታዊ ምንጭ ስላለው ከአህዛብ እምነት የተለየ ስራ ይሰራል፣ የተለየ ባህሪም ያለው ነው፤ ይህ ሃይማኖት በጌታ መገለጥ ፍጹ ሆኖ ልስ ልጆች ተሰጥቶአል ስለዚህ ይህ ሃይማኖት ወደ እኛ ሲመጣ፦ 1.አዲስ ስርአትን ያበስራል በብሉይ ኪዳን የነበሩት እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሄር ፊት የሚቀርቡበትን መንገድ ለውጦ በአዲስ መንገድ በመተካት የአብረሃምን እምነት ፍጹም የሚያደርግ ስርአት በጌታ ተገልጦአል። አስቀድሞም ቢሆን …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(6… )

የእውነተኛው ሃይማኖት ብቸኛ መሳርያ ወንጌል ነው፤ የወንጌል ምስጢርም ክርስቶስ። ወንጌል የጌታን ድል ስለሚያውጅ ነፍሳትን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ይሰበስባል፣ ሃይል ያለው የትንሳኤ መንፈስ ስለሚሰራም ሃሰተኛ ትምህርቶችን ይዋጋል፣ በቃሉ አስተማማኝ ቃል-ኪዳን የገባ አምላክ ለሰው ልጆች አይዋሽምና በሙሉ የጸና የእምነት መሰረት ሆኖ ይኖራል። ወንጌል የሚታመን ዘላለማዊው የእግዚአብሄር አሰራር የተገለጠበትም አዋጅ ነው። ወንጌል በተለያዩ ዘመናት ከተነሱ የሃሰት ሃይማኖቶች በኩል …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(6… )

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(5… )

 ሃይማኖት በውጫዊና ውስጣዊ መገለጫዎች ይታወቃል አንድ ሃይማኖት በእምነት ደረጃ ሲገለጥ መሰረቱ መንፈሳዊነት ሲሆን ከዚያ በመነሳት የውስጣዊ ህይወትን ከእግዚአብሄር ጋር በማገናኘትና በስጋችንም እግዚአብሄርን እያከበርን በቅድስና እንድንኖር የተፈጠረልን መንገድ ነው። ሆኖም በምድር ላይ የምናገኛቸው ሃይማኖቶች ከእውነተኛነታቸው ሌላ መንፈሳዊነት የሚገዛቸው ብቻ ሆነው አናይም፤ እጅግ ብዙ ሃይማኖቶች በዘመናችን ተፈጥረዋል፣ ስጋን የሚያገለግሉና መመሪያዎቻቸው በአእምሮ ውጤቶች ላይ መሰረት ያደረጉ ሆነው …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(5… )

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(4…)

Faith (ሃይማኖት) – stand fast in the faith- በሃይማኖት ቁሙ – obedient to the faith- ለሃይማኖት የታዘዙ – he had opened the door of faith unto the Gentiles- ለአሕዛብ የሃይማኖትን ደጅ ከፈተላቸው – Examine yourselves, whether ye be in the faith- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ – the household of faith- የሃይማኖት ቤተ ሰዎች – One …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(4…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(3… )

እምነት በሃይማኖት ትምህርት ላይ መመስረት ይጠይቃል። ሃይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት እንጂ ቁሳዊ አይደለም፣ መደመርና መቀነስ ስሌት የሚመራውም አይደለም፣ ትምክህቱም ሳያይ መዘርጋት እንጂ ማስተማመኛ ሰብሳቢ አይሆንም፣ እምነትና ማስረጃ አብረው አይሄዱም፣ አማኝ የሰማውን መለኮታዊ ቃል ተቀብሎ ተግባራዊ ያደርጋል እንጂ ምረመራ አድርጎ ማረጋገጫን አያቀርብም። ‘’እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(3… )

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(1… )

ሰው በእምነት ወይም በሃይማኖት በኩል የሚያመልከውን አምላክ ይጠጋል፣ ይከተላልም። ማንም ያለ ሃይማኖት መኖር አይችልም፣ ምክኒያቱም ለአምልኮ የተፈጠረ ማነንት በውስጡ ስለያዘ። ያ ማንነት መንፈሳዊ በመሆኑ ሁልጊዜ በመንፈስ ያስሳል፣ የሚያረካውንም ነገር ይፈልጋል። የሰው ተፈጥሮ ስጋ፣ ነፍስና መንፈስ እንደያዘ ቃሉ ያስተምራል፤ በስጋው በኩል ከግኡዙ አለም ጋር ይገናኛል፣ በመንፈሱ በኩል ደግሞ መንፈሳዊ አለምን ይገናኛል። በሰው ስጋዊ ተፈጥሮ ውስጥ ያለው …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(1… )

ጥሪና አገልግሎት (2…)

የእግዚአብሄር አሳብ ሲፈጸም፣ ‘’ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ ይህ ስለ ብርሃን ይመሰክር ዘንድ ለምስክር መጣ። ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም።’’(ዮሃ.1፡5-8) እግዚአብሔር ለተለየ አገልግሎት የላከው መጥምቁ ዮሐንስ አይሁድ ሁሉ በእርሱ በኩል የተገለጠውን አሰራር ተቀብለው እንዲያምኑ እርሱ ብርሃን ስለሆነው ስለ ክርስቶስ ተልእኮና ማንነት ይመሰክር ዘንድ በትንቢት ስለእርሱ …
Continue reading ጥሪና አገልግሎት (2…)

ጥሪና አገልግሎት(1…)

ጥሪ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ለመንግስቱ ወራሽ የመሆን ግብዣን ቢያጠቃልልም በተለይ ለእግዚአብሄር ስራ ለመለየት ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚመጣ ግብዣ ግን የወንጌሉ አገልጋይ ከመሆን ጋር ይያያዛል። እግዚአብሄር በብሉይ ኪዳን ውስጥ ለመንግስቱ የተጠሩ የእስራኤል ህዝብን ከግብጽ ምድር አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር አፍልሶአቸዋል። ይህም በአዲስ ኪዳን ከአለም ወጥተው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለሚፈልሱ የእግዚአብሄር ልጆች ምሳሌ ነበረ። እግዚአብሄር እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ …
Continue reading ጥሪና አገልግሎት(1…)

ነጻ የወጣ ህዝብ[3…]

የማሰር ስልጣኖች በማይታዘዙ ዜጎች ላይ የሚያርፍ ቅጣት አለ፣ ይህ የማንኛውም ሃገረ- መንግስት ድንጋጌ ነው። የምድር መንግስታት ህግ አውጥተው ዜጎችን በዚያ ካላስተዳደሩ ምድር ሰላም አታገኝም፤ በዚህ ምክኒያት የትኞቹም ዜጎች ለሚገዙለት መንግስት ሊታዘዙ የግድ ሆኖአል። የእግዚአብሄር ወገኖችን ካየን እነርሱ በምድር ሳሉ የሰማይ መንግስት ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ የምድር መንግስትም ጭምር እንደሆኑ ማስተዋል ይገባቸዋል። ስለዚህ እነርሱንም የምድር መንግስት ህግ …
Continue reading ነጻ የወጣ ህዝብ[3…]

ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]

የነጻነት ትርጉም የነጻነት ህይወት ትክክለኛ ትርጉም በኢየሱስ የሚገኝ ነው፤ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጆች በነጻነት ከአምላካቸው ጋር እንዲኖሩ የነጻነት መንገድ ሆነ። ሰዎች በህሊና እየተመሩ ከሚኖሩበት ነጻ ህይወት ተገፍተው ወጥተው በዲያቢሎስ ጫና የእርሱን ፈቃድ ይከተሉና ይፈጽሙበት የነበረው ብዙ ሺ ዘመን ያበቃው በነጻነት የሚኖሩበትን መንገድ ጌታ ኢየሱስ ስለገለጠው ነበር፤ ያን የነጻነት ህይወት ሰዎች ሁላችን ልንኖር ክርስቶስ ሃጢያት ከሚባል …
Continue reading ነጻ የወጣ ህዝብ[2…]