ተግዳሮት ተሸንፎአል(2..)

ተግዳሮት ተሸንፎአል የሚለውን ትልቅ ርእስ ከማየት በፊት ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች ለምሳሌ ተግዳሮት ምንድነው? ተግዳሮትስ ከማንና ለማን(ማን ላይ) የሚሆን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በአጭር ትርጉዋሜ ለማየት መሞከር ተገቢ ነው። ተግዳሮት በህይወት መንገድ ላይ የምናገኘው ፈታኝና አሰናካይ ነገር ሁሉ ነው፤ እርሱ፦ የሚገዳደር ነገር፣ የሚከለክል ነገር፣ ወደ ሁዋላ የሚስብ ነገር፣ የሚያደናቅፍ ነገር፣ የሚይዝ ነገር፣ የሚያፍን ነገር፣ ከመንገድ የሚያስቀር ነገር፣ …
Continue reading ተግዳሮት ተሸንፎአል(2..)

ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ(1…)

የእግዚአብሄር ቃል በዮሃንስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ ለሰው ልጆች በሚገልጠው የምስራች ላይ እንዲህ ብሎአል፦ ‘’… ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።’’ (ዮሐ.1:9-11) ከአዳም የተገኘ ትውልድ ሁሉ በአንድ ስም ሰው ተብሎ ከርሱም ለእያንዳንዱ ትውልድ እውነትን ያሳውቅ ዘንድ እግዚአብሄር በተለያየ መንገድ …
Continue reading ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ(1…)

ያለና የሚኖር (3…)

እግዚአብሄርን የተጠጉ ስለርሱ እንዲህ ይላሉ፡- ‘’እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው? መንገዱን ማን አዘዘለት? ወይስ፦ ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው? ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ። ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ ሰውም ከሩቅ ያየዋል። እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም። የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።’’ (ኢዮ.36:22) እርግጥ ነው፣ ያለና የሚኖረው ህያው አምላክ …
Continue reading ያለና የሚኖር (3…)

ያለና የሚኖር (1…)

‘’እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።’’ (ዘጸ.3:14) ያለና የሚኖር አምላክ የተባለው በራሱ የሚኖር፣ በሌላ የሚያኖር ሃይል የማይኖር፣ ለመኖር ጅማሬ የሌለው፣ ህያውነቱን የሚለካ የሌለ፣ ለህልውናው ድጋፍም መስፈርትም መመኪያም የሌለው፣ ለሌሎች መኖር መሰረት የሆነ፣ ፍጥረታት በርሱ በመፈጠራቸው ጅማሬያቸው ከርሱ የሆነ መሆኑን ያመለክታል። ይህን ታላቅ መልእክት እስራኤላውያን …
Continue reading ያለና የሚኖር (1…)

ተግዳሮት ተሸንፎአል(1…)

በእግዚአብሄር የታመንን ክርስቲያኖች ድሮ በአለም ሳለን (ወደ እምነት ሳንመጣ አስቀድሞ በአለማዊነት ህይወት ሳለን) ከነበረን ተግዳሮት ይልቅ አሁን የተለየ ምን አይነት ፈተና ገጠመን? በአለም ተጽእኖ ስር ሳለን ሲያስቸግሩን የነበሩ የስጋችን፣ የአለምና የሰይጣን ፍልሚያዎች አሁንም እንዳሉ ስላሉ በእኛ ህይወት ምን አዲስ ነገር ይኖራል? የሚል ጥያቄ ሊያመራምር ይችል ይሆናል። ምርመራውም ጥያቄውም ቢመጣ ትክክል ነው፣ ግን ተጠግተን ስንመለከት ውጊያውና …
Continue reading ተግዳሮት ተሸንፎአል(1…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(12…)

ያለጥርጥር ሁሉ ሊቀበሉት የተገባ የነጠረ እምነት አለ፣ ያለክርክር ሁሉ ሊከተሉት የተገባ ጌታ አለ፣ ያለማወላወል እጃቸውን ሊሰጡና በምስጋና ወደርሱ ሊገሰግሱ የተገባ አምላክ አለ፤ ይሄ አምላክ እናደርገው ዘንድ የተገባውን ትእዛዝ በፊታችን ሲያኖርም እንድንና ዋስትና ባለው መንገድ ውስጥ እንድንመላለስ ነው። በመጨረሻው ዘመን ግን ጨካኝ መንፈስ በግልጥም ተሰውሮም እየሰራ ስላለ ሃሰተኞች ሃይማኖቶች በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ እንዲነሱ አድርጎአል፣ ብዙዎች ስተው …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(12…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(11…)

የጌታ ኢየሱስ ክብር በብርሃን የተገጠለት አገልጋይ፣ ማዳኑንና ምህረቱን ከእርሱ የቀመሰ በአንድ ወቅት ግን የአማኞች አሳዳጅና ጠላት የነበረ ከተለወጠና የጌታ ጸጋ ካገኘው በሁዋላ ደግሞ ከሁሉም ሃዋርያት አብልጦ የሮጠ፣ አብዝቶ የደከመም የእግዚአብሄር ሰው የኖረበትንና የሰበከውን ሃይማኖት ለተተኪው ልጁ በጽናት አስይዞ ይሰድደው ዘንድ በምክሩ ሲያበረታው በብዙ የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል እንመለከታለን፤ በዚህ ስፍራ የምንመለከተው ቃል ደግሞ እንዲህ ሲል ይንገራል፦ …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(11…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(10…)

ሰው ያለፈጣሪው መኖር እንደማይችል የሚያውቅ ሰይጣን ሰዎች እርሱ አምላክ እንደሆነና መመለክ እንደሚገባው አድርጎ በተለያየ መንገድ ያሳምናቸዋል፣ በአገልጋዮቹ አድርጎ ይናገራል፣ ብዙዎችን አሳምኖም በሚታዩ ጣኦታት በኩል እንዲያመልኩት ያደርጋል፤ ይህን በተመለከተ ንጉስ ዳዊት እንዲህ ብሎአል፦ መዝ.96:4-5 ‘’እግዚአብሔር ታላቅ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነውና። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸውና፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።’’ ዋናው ነገር ሰዎች …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(10…)

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(9… )

​​​​​​​​ዕብ.3:1 ‘’ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ’’ እውነተኛ ሃይማኖት ከአይሁድ እምነት ይጀምር እንጂ ፍጻሜውን ያገኘው በኢየሱስ የመስቀል ስራ አማካይነት በተሰጠን እምነት ነው፤ የዚህ ሃይማኖት ሊቀካህናትና የሃይማኖቱ ሃዋርያ ራሱ ጌታ ነው፤ አይሁድ የተቀበሉት ህግ ሊመጣ ለነበረው በእምነት ለሚገኘው ለክርስቶስ ጽድቅ እንደ ጥላ ነበረ። ይህም እምነት አብረሃም እግዚአብሄርን …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(9… )

ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )

ብቸኛውና ፍጹሙ ሃይማኖት መለኮታዊ ምንጭ ስላለው ከአህዛብ እምነት የተለየ ስራ ይሰራል፣ የተለየ ባህሪም ያለው ነው፤ ይህ ሃይማኖት በጌታ መገለጥ ፍጹ ሆኖ ልስ ልጆች ተሰጥቶአል ስለዚህ ይህ ሃይማኖት ወደ እኛ ሲመጣ፦ 1.አዲስ ስርአትን ያበስራል በብሉይ ኪዳን የነበሩት እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሄር ፊት የሚቀርቡበትን መንገድ ለውጦ በአዲስ መንገድ በመተካት የአብረሃምን እምነት ፍጹም የሚያደርግ ስርአት በጌታ ተገልጦአል። አስቀድሞም ቢሆን …
Continue reading ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(7… )