የፍቅርን ጉልበት ሊረታ ማን ይችላል? በሀይል ያልተደፈረ ጀግና ስለፍቅር እጅ ሲሰጥ በሶምሶም ታሪክ ውስጥ የምናየው ነው፤ የህዝብ ታላላቆችም ቢሆኑ በክፉ ቀን ስለሚመሩት ህዝብ ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡ በእስራኤል ነገስታቶች ታሪክ ውስጥ እናያለን፤ ወዳጆችም ስለባልንጀራቸው ፍቅር ሲሉ አክብረው የያዙትን አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ዮናታን ለዳዊት እንዳደረገው፡፡ይህ ሁሉ የሚሆነው በፍቅር የማስገደድ ጉልበት ምክኒያት ነው፡፡ ፍቅር ስጋዊ አይንን ከራስ ወዳድነት …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [1…]
Category:የእውነት እውቀት
የአዲስ ኪዳን ህያው አገልግሎት [2/2]
ከጌታ ሞት፣ ትንሳኤና እርገት አስቀድሞና ደቀምዛሙርት ለአገልግሎት ሳይወጡ በፊት አስፈሪ ስብራት በይሁዳ ላይ ወድቆአል፡፡ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ላይ እግዚአብሄር ይበልጥ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገና ወንጌል መሰበክ ሳይጀምር ታየ፤ ይሄ ክስተት በደቀመዛሙርቱ ዘንድ ይበልጥ ፍርሀትን፣ ጥንቃቄንና የእግዚአብሄርን ፊት ወደ መፈለግ አምጥቶአል፡፡የሁለቱን ኪዳኖች አገልግሎት በተመለከተ ግን ሀዋርያው ጳውሎስ እያነጻጸረ የሚገልጠው ምስጢር አለው፣ እንዲህ ይላል፡- 2ቆሮ.3:5-17 ”ብቃታችን ከእግዚአብሔር …
Continue reading የአዲስ ኪዳን ህያው አገልግሎት [2/2]
የአገልጋይ ስብራት[1/2]
በእግዚአብሄር ፊት በአገልግሎት በቆሙ ሰዎች ላይ ከተፈጠሩት ስብራቶች አንደኛው አስደንጋጭ ክስተት ኦዛ ላይ የደረሰው ስብራት ነበር፡፡ኦዛ በእግዚአብሄር ታቦት ፊት እየሄደ ባለበትና በደስታ እግዚአብሄርን በሚያገለገልበት በዚያች ወቅት ድንገት በስህተት የፈጸመው ድርጊት በመላው እስራኤል መሀል እስከወዲያኛው የሚታወስ መቅሰፍት አምጥቶበታል፡፡ይህን ክስተት ያስተዋለ ሁሉ እግዚአብሄርን እንዴት ማገልገል እንዲገባው ቆም ብሎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄርን ማገልገል እንዴትና እስከምን ድረስ የሚለውን ጥያቄ የሙሴና …
Continue reading የአገልጋይ ስብራት[1/2]
መንፈሳዊ ሪቫይቫል- ከሴኬም ወደ ቤቴል ተመለስ!
እግዚአብሄር ያእቆብን ስለወደደው ወደ በረከቱ ስፍራ እንዲመለስ አስታወሰው፡- ዘፍ.35:1-10 እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፡- ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ።ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ። እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፤ ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር …
Continue reading መንፈሳዊ ሪቫይቫል- ከሴኬም ወደ ቤቴል ተመለስ!
የታላቁ ጠላት ጥቂቱ
ብዙ ጊዜ ጥቂት ያልነው አነስተኛ ወይም አይን የማይገባና ጉልበቱን ቸል ያልነው ኢምንት ነገር ብዙሀኑን ሰርስሮ በመግባት በክሎና ተሰራጭቶ በራሱ ባህሪ ሲውጠው እናያለን፡፡የእግዚአብሄር ቃል ጥቂት እርሾ ሙሉውን ሊጥ እንደሚያቦካ ያስረዳል፡፡ጥቂት እርሾ ውስጥ ያለ ኮምጣጣ ነገር የመሰራጨት ጉልበቱ ከፍተኛ በመሆኑ ንጹሁንና ትኩሱን (ያልከረመውን) ሊጥ በፍጥነት ያቦካዋል/ያኮመጥጠዋል፡፡ነገሩ በእኛም ህይወት ውስጥ ሲመጣ እንዲሁ ነው፡፡እንደ እርሾው የኮመጠጠና የማይመች ነገር ከእኛ …
Continue reading የታላቁ ጠላት ጥቂቱ
የፈራሽ ቤት መሃንዲሶች
ህያው ነፍስ ያለን የሰው ልጆች የሚናድ፣ የሚፈርስና የሚከስም ጊዜያዊ መኖርያ ውስጥ እንደምንኖር መቼም ልንዘነጋው የማይገባ ነው። የእግዚአብሄር ፈቃድ የፈጠረውን አካል ከምድር እንዳወጣው መልሶ በምድር ወስጥ እንዲከስም ወስኖአል።ነቢዩ በኢሳ.38:12-16 ላይ፦ “ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፥ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከማለዳም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ …
Continue reading የፈራሽ ቤት መሃንዲሶች
ከእምነት መንሸራተት
በማቴ.8:237 ውስጥ ያሉ ደቀመዛሙርት በሁኔታዎች አስቸጋሪነት ምክኒያት ልባቸው በፍርሀት ተያዘና አብሮአቸው ያለውን ጌታ እስከመርሳት ደረሱ፡-”ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀመዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም፥ ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፡- ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉአስነሡት። እርሱም፡- እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም …
Continue reading ከእምነት መንሸራተት
ጊዜያዊ ዘላለማዊነት
ባለን ልዩ ልዩ አስተሳሰብ ምክኒያት ሰዎች ጊዜያዊውን ምድራዊ ኑሮ ዘላለም እንደሆነ በመቁጠር እንኖረዋለን። እንዲያ በመሆኑም እቅዳችን ከልክ ያለፈና የተለጠጠ ነው።መዘናጋትም ይታይበታል፡፡ በጊዜያዊው አለም ዘላለማዊ የሚመስል እቅድ ውስጥ መዘፈቅ ትክክለኛ ምርጫን መዘንጋት ይፈጥራል፡፡ ቁዋሚና ዘላለማዊ ነገር ምድር ላይ ሳይኖር እኛ ግን በራሳችን ዙሪያ እንደዚያ የመሳሰሉ እቅዶችን ስናስቀምጥ በጊዜያዊ የምድር ኑሮ ዘላለማዊንትን ልንገነባ እየሞከርን ነው ማለት ነው፡፡ …
Continue reading ጊዜያዊ ዘላለማዊነት
የለጋስ ስጦታ
1.በጎ ሥጦታ ስጦታ ከለጋስ አካል የሚወጣ ጥቅም ሆኖ በሰጪው ቸርነት ላይ የተመሰረተ የመስጠት እንቅስቃሴ ነው። ስጦታ ለሰጪውም ለተቀባዩም የሚያስደስት እንድምታ አለው። ማንም የሚሰጥ አካል አምኖበት የሚሰጥ ሲሆን ተቀባዩ ክብደት ሰጥቶ ሰጪውን የሚያከብርበት አጋጣሚ ነው። አንድ ሰጪ ለሌላው ተቀባይ እንደዚህ ባለ መንገድ ስጦታ ሊሰጠው ይችላል። እግዚአብሄር ሊባርክ ይሰጣል ዘፍ.17:15-16 ”እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ …
Continue reading የለጋስ ስጦታ
ህይወት የሚገኝበት ትምህርት
ዕብ.10:19-20 “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥…“ እግዚአብሄር በአዲስ ኪዳን የከፈተው አንድ ብቸኛ መንገድ ህይወት ያለበት መንገድ ነው።ህያው መንገድ ህያው አምላክ የሚገለጥበት አዲስ የህይወት ስርአት ነው።ህያዋን የሆኑ በመንፈስ የተወለዱ ነፍሳትም ይመላለሱበታል።ህያዋን የሆኑ እነዚህ መንፈሳውያን ከመንገዱ ሳይለቁ ጸንተው እንዲኖሩ እግዚአብሄር የህይወት ትምህርትን ይገልጥላቸዋል።ህይወት የሚገኝበትን …
Continue reading ህይወት የሚገኝበት ትምህርት
