ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]

ህዝቡን የሚያድን አምላክ ለሰው ልጆች የሆነ የማዳኑን ብስራት ሲገልጥ በሰማይ የተገለጠው ትእይንት ልብ የሚሞላ ነው፡- ”እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም …
Continue reading ህዝቡን የሚያድን አምላክ[2..]

ህዝቡን የሚያድን አምላክ[1..]

ሰውን ለማዳን በጎ ፈቃዱ የሆነና ሁሌም ሊገለጥ የሚፈቅድ አምላክ ሲናገር ተመልከቱና አስተውሉ እንጂ ለማዳን፣ ለመፈወስ፣ ለመምታትም ሆነ ለመግደል የምችለው እኔ እግዚአብሄር ብቸኛው አምላክ ነኝ፣ ይህን እወቁም ሲል አዋጅ ይናገራል፡፡ በተለይ በዘዳ.32:39 ላይ ብርቱ ቃል ሲናገር፡- ”አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ የሚያድን የለም።” እግዚአብሄር …
Continue reading ህዝቡን የሚያድን አምላክ[1..]

የፍቅር ግዛቶች [5..]

የፍቅር ክልል በስፋት፣ በርዝመትና በጥልቀት የማይለካ ግን ልብን አእምሮንና ነፍስን የሚቆጣጠር ብርቱ ሀይል፣ ሰውንም ያለጉልበት መግዛት የሚችል ታላቅ መለኮታዊ ስጦታ ነው፡፡ ክፉ የተባለውን የሰው ልብ ሌላ ምን አይነት ጉልበት ሊያቆመው ችሎአል? እርሱን ለመለወጥ የሚችል ፈቃድስ ምን ነበር? እግዚአብሄር ለብዙ ዘመናት ቃሉን፣ ህጉን፣ ስርአቱንና መንገዱን ቢሰጥም የሰው ልብ እሺ ብሎ የተገዛው መቼ ነበር? እግዚአብሄር ግን ያን …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [5..]

ከሰማይ እውቀት መጉደል[1…]

ከሰማያዊ እውቀት መጉደል የሚያመጣውን መምታታት፣ የሚፈጥረውን የማስተዋል እጦት፣ የሚጥለውን የጉዳት ጠባሳ፣ የሚያስቀረውን መለኮታዊ ጸጋ፣ ተመትቶ ማንከስ ወይም ተቆርጦ መንገድ ላይ መቅረትን ለመገንዘብ በግልጽ ከአይሁድ የህይወት ተሞክሮ በማየት መማር እንችላለን፡፡ ሰማያዊ እውቀት ምንድነው? የእውቀቱ መታጣት እንዴት አስከፊ ቢሆን ነው የዚህን ያህል ጉድለትና ጥፋት ያሚያስከትለው? የምንል ልንኖር እንችላለን፡፡ ቅድሚያ በዘኊ.24:15-16 ላይ የሚገኘው በለአም የተባለ ሰው ስለ መለኮታዊ …
Continue reading ከሰማይ እውቀት መጉደል[1…]

የፍቅር ግዛቶች [4..]

እግዚአብሄርን ለምን እንወደዋለን? መውደዱ ዋስትናችን ስለሆነ አይደለምን? መዝ.145:20 “እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል” ስለሚል፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄር ውደዱ ያለን ነገር እንዳለ ሁሉ እንድንጠላው የሚፈልገው ነገርም አለ፡፡ ጥሉ ያለንን ነገር እግዚአብሄር በእኛ ዘንድ ሊያያቸው እንደማይሻ ከቃሉ መመልከት እንችላለን፡- 1ሳሙ.28:16-19 ”ሳሙኤልም አለ፡- እግዚአብሔር ከራቀህ ጠላትም ከሆነህ ለምን ትጠይቀኛለህ? እግዚአብሔርም በቃሌ እንደ ተናገረ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [4..]

አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[2…]

ክርስቶስ ኢየሱስ በመልከጼዴቅ ምሳሌነት ብዙ ባህሪውንና ተልእኮውን ለአለም ገልጦአል፡፡ የሚከተሉት ነጥቦች ይህንን እውነት የሚያሳዩ ናቸው፡- • የዘር ሀረግ አልነበረውም ክርስቶስ ባህሪም ሆነ የዘር ሀረግ ከሰብአዊ አባትና እናት አልወረሰም፣ ስለዚህ ምድራዊ ጅማሬም ማለቂያም የለውም፡፡ የክርስቶስን ምድዊ የዘር ሀረግ መቀጣጠል የተሳናቸው እስራኤላውያን የዮሴፍንና የማርያምን የዘር ሀረግ እየሳቡ ከርሱ ጋር ሊያስጠጉ ሞክረዋል፡፡ቃሉ ግን እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነው ይላል(ራእ.1:8)፤ …
Continue reading አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[2…]

አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ (በእብራይስጥ ሲጠራ መሲህ/የተቀባ) የተባለ፣ ሁለተኛው ሰው ሲል ቃሉ የጠራው፣ የሰው ልጅ ሲል እርሱ ራሱን ያስተዋወቀው ለእግዚአብሄር አላማና የዘላለም ፈቃድ አስፈጻሚነት የተቀባ ሰማያዊ ሰው ነው፡፡ ሰዎች እርሱን ማን ሲሉ እንደሚጠሩት ጠየቀ፡- ” ለብቻውም ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፡- ሕዝቡ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም መልሰው፡- መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም፡- ኤልያስ፥ …
Continue reading አልፋ ኦሜጋ ካህንና ንጉስ[1…]

የዝምታ ድምጽ

ዝምታ ምን አይነት ድምጽ ሊያሰማ ይችላል? ወይም ዝምታና ድምጽ እንደምን ይገናኛሉ? ዝምታ ያለ ድምጽ የሆነ ክስተት ሲሆን ድምጽ ከሚሰማ ቃል ጋር በመሆኑ ሁለቱ በተቃራኒ በኩል ሳሉ በአንድነት ትርጉም ያላቸው እንዲሆኑ ተደርገዋል፤ የቻሉት ግን የእግዚአብሄር አሰራር በመሆናቸው ነው፡፡ በዝምታ ውስጥ ምን ልንሰማ እንችላለን? ምን አይነት ድምጽስ በዝምታ ውስጥ ሊሰማ ይችላል ብለን መጠበቅ እንችላለን? እንደ ሰው ግን …
Continue reading የዝምታ ድምጽ

የፍቅር ግዛቶች[3..]

”ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።” (1ዮሐ.4:10-12) ፍቅርን ስናስብ የማንነቱ ነገር/ እርሱ ማን …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች[3..]

የፍቅር ግዛቶች [2…]

ስለ ፍቅር፡- ፍቅር የሚባል ስጦታ ከመለኮት የመነጨና ልዩ ባህሪ ያለው፣ ከነገሮቻችን መሀል ከፍ ያለ የተሰጠን የማንነታችን ገዢ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሰጠን ፍቅር ጥልቅ በመሆኑ አእምሮን ያልፋል፣ የልብ ፈቃድን ያልፋል፣ የነፍስ ምኞትን ያልፋል፣ ከመንፈስ ይዘትም ይልቃል፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር ሲገባ ሁሉ ነገራችንን ያሸንፋል፣ ይቆጣጠራልም፡፡ እውነተኛ ፍቅር ልብ፣ አእምሮና አሳብን በመግዛትና ወደ ፈለገው አቅጣጫ በመምራት የደስታ ስሜትን በሁለንተናችን ያፈልቃል፡፡ …
Continue reading የፍቅር ግዛቶች [2…]