ያለመቻል አቅም ማጣት፣ መጉደል፣ ማንከስ፣ ወደ ሁዋላ ማለት፣ ፍጥነት መቀነስ፣ ጥንቃቄ ያለማድረግ፣ በመሳሰለው ነገር ይገለጣል፡፡ አቅም ያጣንባቸው ጊዜያቶች በውስጣችን ያለውን አሳብ ወይም ራእይ እንዳንፈጽም ወደ ሁዋላ ይጎትቱናል፣ ወይም እቅዳችንን እንዳናከናውን ያደርጉናል፡፡ አቅማችን በራእያችን ልክ ወይም ከዚያም በላይ ካልሆነ ልንደርስበት የምንፈልገው ግብ ይርቃል፡፡ አንዳንዴ አቅም ማጣት በጥበብ ቢያዝ ችግሩ ሊታለፍ ይችል ይሆናል፤ ሆኖም በውስጥ የማይኖር እምቅ …
Continue reading ባለመቻል ማንከስ/ማነስ
Category:የመጨረሻ ዘመን
እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]
የተሳሳተ ሀይማኖት ለምን ከመሰለኝ ይነሳል? መሰለኝ የስህተት መፈልፈያ ዋሻ በመሆኑ ነው፤ የጥርጥር መሰረት በመሆኑም የተሳሳተ ሀይማኖት ያስፋፋል፡፡ ሀይማኖቱ በሚመስል እውቀት ላይ በመመርኮዙና ግምታዊ ድምዳሜን በመቀበሉ ምክኒያት መንገዱን ይስታል፡፡ ቀጥ ብሎ ማደግ በሚገባው ወቅት ተንጋድዶ ከፍ ይላል፣ ከነአመሉ እንደተወላገደ ሽቅብ ይሄዳል፣ ያለእርምት ይጎለምሳል፣ ስርም ይሰዳል፣ በመጨረሻ ግን ማምለጥ በማይችለው የስህተት ወጥመድ ላይ ይቆማል፣ ይነከሳል፡፡ በተለይ ግምታዊ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[3…]
እንደመሰለኝ ቢሆን[2…]
የመሰለንን ማድረግ በኑሮአችን ውስጥ የተለያየ ውጤት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ስለአንድ ነገር ገምቼ እንደመሰለኝ ቢሆንና የገመትኩት ቢፈጠር ቢያንስ አስቀድሜ የጠበቅኩት ሆኖአልና በግምቴ ትክክለኝነት እመካለሁ፤ ደግሞም ነገሮች ከመሆናቸው አስቀድሜ መገመቴ ከቻልኩ ከአስቸጋሪ ሁኔታ ማምለጫ አገኝበት ይሆናል፣ ግምቴ ቢሳሳት ግን ተቃራኒ ውጤት ይፈጠራል፡፡ እርግጥ ነው ጥሩ ገማች አለም ትፈልጋለች፡፡ ይሄም በቦታው ተገቢ ነው፡፡ እንደ አየር ሁኔታ ትንበያ የመሳሰሉ ተግባሮች …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[2…]
እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]
ተፈጥሮአችን ስለሆነ ሰዎች እንደሚመስለን እንገምታለን፡፡እንደሚሰማንም እንናገራለን፣ሊሆን ይችላል ብለን፡፡መሰለኝን አምነን እንቀበላለን፡፡ብዙ ጊዜ መስሎን የነበረ አሳብ ውስጣችን ከርሞ ወደ ምስል ይለወጥና የአስተሳሰባችንን አቅጣጫ ይቀይረዋል፡፡መሰለኝ እያልን ፣ፈራ ተባም እያልን እንጀምራለን፣ ነገራችንን፡፡ከጊዜ ወደጊዜ እያሳደግነው ከሄደና በታናሽነቱ ካልገዛነው አድጎ ወደ እምነት በመቀየር በተራው ይገዛናል፣ደግሞም ይመራናል፡፡ የመሰለኝ ጉልበት የሚገለጠው በዝግታ ነው፡፡ እውነት በሚገኝበት ስፍራ ላይ ልብን በሙላት ማዘንበል ከግምት አስተሳሰብ ያወጣል፡፡”እከሌ …
Continue reading እንደመሰለኝ ቢሆን[1…]
በዘመን መሀከል እግዚአብሄር
የባቢሎን ምድር በገነነችበት ዘመን ምድሪቱን ያሳወቁትና ዝናዋን ከፍ ያደርጉት ነገስታቶችዋ ብቻ አልነበሩም፡፡ምድሪቱዋ የመናፍስት መናሀሪያ እንደመሆንዋ በአማልክቶቹዋ ብዛትም የታወቀች ነበረች፡፡የመንግስታቶችዋ ዝና፣ ስመጥር ስራዎችና ወረራዎች እንዲሁም ጠቢባኖችዋ በዘመኑ ከፍ ያሉ ነበሩ፡፡በነዚያ ዘመናት መካከል ግን የእስራኤል አምላክና የባቢሎን አማልክት የሚወዳደሩበት አውድና አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡በአጋጣሚው መሀል ህያው አምላክ የመረጣቸው ህዝቦች ከአህዛብ መሃል ተገኙ፤ የአይሁድ በባቢሎን መገኘት ግን የእንግድነት ሳይሆን ይምርኮና …
Continue reading በዘመን መሀከል እግዚአብሄር
የቸርነቱን ደውል አስተውል
የእግዚአብሄርን ባህሪ የሚገልጥ አዋጅ እንዲህ ይላል፡- ዘጸ.34:6-8 ”… እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥እስከ ሺህ ትውልድም ቸርነትን የሚጠብቅ፥ አበሳንና መተላለፍን ኃጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኃጢአት በልጆች እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው ሲል አወጀ።ሙሴም ፈጥኖ ወደ መሬት ተጐነበሰና ሰገደ።” የእግዚአብሄርን ምህረትና ቸርነት የሚያውቁ ቅዱሳን …
Continue reading የቸርነቱን ደውል አስተውል
ጥሪን የማይምጥን ህይወት
የጌታ ቅዱስ አጠራር ጠሪው አምላክ ቅዱስ መሆኑንና የሚጠራቸው ሰዎችም ቅዱስ እንዲሆኑ እንደሚሻ ያመለክታል።በቅዱስ አጠራር የተጠራ ሰው ለጠሪው ሊለይና እንደተጠራ አስተውሎ ሊዘጋጅ ያስፈልጋል። እንዲሁም ቅዱስ መሆን የማይችል ሰውና ቅዱስ የሆነ አምላክ ህብረት ያደረጉበት መንገድ ላይ ትኩረት ሊያደርግ ተገቢ ነው። ለዚህም ምሪት የሚሆን የእግዚአብሄር አሰራር በቃሉ ላይ ተቀምጦአል። አህዛብ የተጠራነው በኛ ውስጥ ባለ መልካም አሳብና ስራ ምክኒያት …
Continue reading ጥሪን የማይምጥን ህይወት
ያለ እውነተኛ አምላክ ኑሮ
እውነተኛ አምላክ ባልተገለጠበት ስፍራና ዘመን የሃሰት አማልክት ተገልጠው ይሰራሉ (2ዜና.15:3)።በዚያን ጊዜ አጋንንት በድፍረትና በግልጽ ስለሚንቀሳቀሱ ተጽኖአቸው ከፍተኛ ነው።የጣኦታት ወረራም ነፃነት አሳጥቶ ማስተዋል እስኪሳን ድረስ ክፋት ይነግሳል፡፡የፍጥረታት ሁሉ ጌታ ግን ፍጥረቶቹ በርሱ ጥላ ስር ተማምነው እንዲኖሩ እንጂ ባለቤት ወዳልሆኑ አማልክት ፊታቸውን እንዲመልሱ አይሻም። እውነተኛ አምላክ የሌለው ትውልድ በክፉ መናፍስት የተጠቃ እንደሆነ የንጉስ አሞጽ ታሪክ ያሳየናል፦ 2ነገ.21:19-22 …
Continue reading ያለ እውነተኛ አምላክ ኑሮ
ራስን የመጣል ስልጣኔ[2/2]
ራስን መጣል ከስልጣኔ ጋር? ራስን መጣል ከስልጣኔ ጋር በአፍሪካ ምድር መዋሃድ ይችላሉ ሲባል እዚህ አህጉር ላይ የስልጣኔ ትርጉዋሜና የራስ አተያይ (ለራስ የሚሰጥ ግምት) በተሳሳተ መንገድ ተጣምረው ይገኛሉ ማለት ነው፡፡ የገዛ ራስን በተሳሳተ መንገድ ማየት ባልሰለጠነ ስልጣኔ ላይ ተጨምሮ ይበልጥ ነገሮችን እንዳወሳሰበ ለማሳየትም ነው፡፡ራስን መጣል ሳያንስ የተሳሳተ ስልጣኔ ሲታከልበት በጣም ይጎዳል፡፡ ለምን ”ሰለጠንን” ብለን እንደሰለጠነ ሰው …
Continue reading ራስን የመጣል ስልጣኔ[2/2]
ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ በሃገር ላይ መርገም ሲሆን)
አንድ አገር እየሰለጠነች ስትሄድ በዚያው ልክ ለማህበራዊ እሴትዋ ካልተጠነቀቀች እጅግ ስር በሰደደ ማህበራዊ ቀውስ ትመታለች። ቴክኖሎጂና ስልጣኔ የእውቀት ሽግግር ብቻ ሳይሆን የመጥፎ ባህል ተስቦ መተላለፊያ መንገድም ነው። ባእድ አምልኮና ያልተለመደ ወግ አንድን ሃገር እንደ በረሃ አንበጣ በጥቂት ወቅት ሊያጥለቀልቅና ሃገራዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል። ዋጋ መሰጣጣት፣ መከባበርና መተሳሰብ የሚቀዘቅዘው ማህበረሰቡ ያካበተውን ማህበራዊና መንፈሳዊ ሀብቶች በስልጣኔ አመካኝቶ …
Continue reading ቴክኖ-መርገም (ቴክኖሎጂ በሃገር ላይ መርገም ሲሆን)
