እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜ ይፈጽማል‹1..›

እግዚአብሄር ሲናገር፡-”ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም” ይላል (ኢሳ.45:23)፡፡ እግዚአብሄር ይናገር እንጂ የተናገረው መሆኑ/መፈጸሙ አይቀርም፡፡ ስልጣን ያለው ቃል አሳቡን ማከናወን እንደማይሳነው እንኩዋን ህያው አምላክ ከሰው የሆነ ባለስልጣንም በችሎታው አይጠረጠርም፡፡ የእግዚአብሄር ንግግር ለመከናወኑ እርግጠኛ/እውነት በመሆኑ ሲናገር የሰሙት ሰዎች የተናገረውን ቃል በደስታና በተስፋ ይዘው ይጠባበቁታል፡፡ መጠበቅ እንዲህ እንደምንለው ቀላል አይደለም፡- ትግስት ይጠይቃል፣ እምነት ይጠይቃል፣ ጊዜም ይጠይቃል፡፡ ቢሆንም የታመኑት …
Continue reading እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜ ይፈጽማል‹1..›

አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)

እግዚአብሄርን በማወቅና ባለማወቅ መሀል ያለው ልዩነት የሞትና የህይወት ያህል ዋጋ እንዳለው ጌታ ኢየሱስ በአጽንኦት ተናግሮአል፡፡ ጌታ በዮሐ.17:3 የተናገረው እንዲህ ይላል፡- ”እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” በትንሹ ልባችን ስለርሱ ባወቅነው እውቀት ምክኒያት ያገኘነውን ታናሽ እምነት ይዘንና ወደ እርሱ ቀርበን አላፈርንም፤ እንዲያውም ከርሱ ጋር በምንኖርበት ዘመን ሁሉ ሳይነቅፈን …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (2…)

አንተ ግን ያው አንተ ነህ (1…)

ንጉስ ዳዊት የህይወት ዘመኑ ወደ ማለቅ ቢፈጥንም የፈጠረው አምላክ ግን ያለመለወጥና ያለመናወጥ ጸንቶ እንደሚኖር እጅግ ያስተዋለ ሰው ነበረ፤ ስለዚህ እንዲህ ሲል በመዝ.102:11፣23-28 ውስጥ ተናገረ፡- ”ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘላለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው።… የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ። በዘመኔ እኵሌታ አትውሰደኝ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው። አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (1…)

ፊትህን አሳየን{3..}

ከፊቴ ያለ ጠላት ከፊት የሚወጣ ጠላት እስካልተቐቐምኩት ድረስ ከእርምጃዬ የሚፈጥን፣ ከጅማሬዬ ቀድሞ ያሻውን የሚፈጽም፣ ከጉዞዬ ፊትም ወጥቶ መሰናክል የሚሆን ነው፣ በእቅዴና በስራዬ እንዳይቀድመኝና እንዳያሰናክለኝ ምኞቴ ቢሆንም እኔ ያን ማሳካት እንደምችል በራሴ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ የሚያደባ ጠላት መንገዴ ላይ የሚያተኩረው ከእውነት ሊያስተኝ እግሬንም ሊያሰናክለው ካልሆነ ለሌላ ለምንም አይሆንም፡፡ በዚያ ተልእኮው ስንቴ ወጥመድ አጠመደብኝ? ስንቴ ማሰናከያ ድንጋይ አኖረብኝ? …
Continue reading ፊትህን አሳየን{3..}

ፊትህን አሳየን{2..}

የእግዚአብሄርን ታላቅነትና አስፈሪ ክብር ማወቅ ለሚፈልግና ሀይሉን ሊረዳ የሚፈቅድ ካለ እግዚአብሄር ለህዝቡ የተገለጠበትን ሁኔታ እንዲያይ እንዲያስፈልግ ለመታሰቢያነት በቃሉ ላይ ሰፍሮአል፡- ዘጸ.19:10-11 “እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፡- ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገም ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤ በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ይዘጋጁ።” የእስራኤል ህዝብ በግብጽ ሳለ በሙሴ በኩል ስለ እግዚአብሄር አዳኝነት ሰምቶ …
Continue reading ፊትህን አሳየን{2..}

ፊትህን አሳየን{1..}

የእግዚአብሄር ፊት ከቅርበቱ፣ ከክብሩ፣ ከእይታው፣ ከሞገሱ፣ ከጉብኝቱ፣ ከመገኛው፣ ከገጽታውና ከማንነቱ ጋር ይያያዛል፡፡ የእግዚአብሄር ፊት ሲታይ ክብሩ ይታያል፣ ሀይሉ ከሞገስና ከማስፈራቱ ጋር ይገለጣል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ፊት ሲሆን ለምህረት ይቆማል፣ በረከት ሊቀበል ይቆማል፣ ትእዛዝ ሊቀበል፣ ፍርድ ሊቀበል፣ ደግሞም ሀይል ይሞላ ዘንድ ሀያሉ አምላክ ፊት ይቆማል፡፡ የሰው ልጅ የመጨረሻው አቁዋቁዋሙ ግን ዘላለማዊውን ኑሮ መወሰኛ ሰአት ይሆናል፡- ራእ.20:12 “ሙታንንም …
Continue reading ፊትህን አሳየን{1..}

የማይፈሩ ልቦች

መንፈሳውያን በእምነት ተመርኩዘው በጽድቅ የሚደፍሩት ድፍረት አለ፡፡ በአምላካቸው ፊት ትሁትና የተገዙ ሆነው ይኖራሉ፤ በእርሱ ላይ ጠንካራ እምነት አላቸው፤ ልባቸው በቃሉ ላይ ሙሉ በመሆኑ ስለቃሉ ድፍረት አላቸው፣ነገር ግን አምላካቸውን የሚፈሩ ናቸው፡፡ በእግዚአብሄር የሚተማመኑ ሰዎች አያፍሩም፤ ”አልፈራም እግዚአብሄር ይረዳኛል” ይላሉ፡፡የታመኑት አምላክ ፈጽሞ ፊት እንደማይነሳቸው እጅግ ስለሚተማመኑ ሞት ፊት እንኩዋን ቢቆሙ በልበ-ሙሉነት አምላካቸውን ይጠራሉ፣ ለዚህ እነ ዳንኤልን ምስክር …
Continue reading የማይፈሩ ልቦች

ምን እንስራ?[3…]

• እግዚአብሄር ምን እንድንሰራ ነው የሚፈልገው? ሮሜ.12:11-12 ”ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ…” የእግዚአብሄር ልጆች ቀዳሚ ስራ እግዚአብሄርን ማመንና መከተል እንዲሁም ሲሰራ መንገድ እንጂ እንቅፋት ያለመሆን ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄርን በአባትነቱና በአምላክነቱ ካልወደደው ትክክለኛው የህይወት ይዘት ውስጥ ሆኖ ሊመላለስ አይችልም፡፡ አይሁድን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል፡- ዮሐ.8:39-42 ”መልሰው ፡- አባታችንስ …
Continue reading ምን እንስራ?[3…]

ምን እንስራ?[2…]

• እግዚአብሄር የሰራውን የሚያስቡና የሚያመሰግኑ የሚያስተውሉት ናቸው፡፡ ቃሉም በኢዮ.36:24-25 ውስጥ ሲናገር ”ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ። ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ ሰውም ከሩቅ ያየዋል።” ይላል፡፡ ሰዎች በራሳቸው ስራ እንዳይመኩ፣ ነገረ ግን መመካት ካለባቸው በእርሱ ስራ ብቻ እንዲሆን እርሱ በምድር ላይ ተገልጦአል፡፡ በማቴ.1:23 ”እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ….” ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ምን ሊሰራ እንደተገለጠም ሲናገር፡- ”…ልጅም ትወልዳለች፤ …
Continue reading ምን እንስራ?[2…]

ስራውን አስብ[1…]

ስራውን አስብ! • እግዚአብሄር በግልህ ህይወት የሰራውን፣ • እግዚአብሄር ለመላው የሰው ልጅ/ለአለሙ ሁሉ የሰራውን፣ • እግዚአብሄር በየዘመናቱ የሰራውንና የገለጠውን፣ • እግዚአብሄር ከዘላለም አቅዶ በአዲስ ኪዳን የፈጸመውን፣ • እግዚአብሄር በአለም ፍጻሜ በዘላለማዊ መንግስቱ ሊገልጠው ያለውን፡፡ ስራው በትክክል ገብቶን ከሆነ ለልባችን የዝማሬና የቅኔ ምንጭ ይሆናል፡- በእያንዳንዳችን ህይወት የሰራው ስራ አስገርሞን፣ አለምን የተመለከተበት ርህራሄ ደንቆን፣ ከብዙ ዘመናት አስቀድሞ …
Continue reading ስራውን አስብ[1…]