እውቀተ መለኮት(2…)

ካለፈው የቀጠለ… የእግዚአብሄር እውቀት የእግዚአብሄርን ህልውና ያበስራል፤ አሰራሩን ይናገራል፤ አምላክነቱን ያውጃል። በእግዚአብሄር እውቀት መሰረት ላይ ያልቆሙ የሰው ልጆች ከእግዚአብሄር ስራ ጋር ይጋጫሉ፤ ባለማወቃቸው ጠንቅ ስህተት ትይዛቸዋለች፤ ለእግዚአብሄርም ቅጣት አሳልፋ ትሰጣለች፦ “እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ። እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ።”(መዝ.73:11-12) ይህ በጎ ያልሆነ አሳብ የተፈጠረው ባለማወቅ ምክኒያት በመሆኑ ባልሆነ …
Continue reading እውቀተ መለኮት(2…)

እውቀተ መለኮት(1…)

ምድራዊ መንግስታት እውቀትን እንደ ስልጣኔ በር ቆጥረው ህዝባቸው ያውቅ ዘንድ ይለፋሉ። በሁሉን አቀፍነት አንጻር ይህ እውቀትን የማግኘት፣ የመረዳትና የመቀበል ዝንባሌ የትውልድ ማስቀጠያም ተደርጎ የሚቆጠር ነው፤ ምክኒያቱም ያላወቀ የማያስተውልና ወገንን ጠቃሚ ስለማይሆን ነው። በመንፈሳዊ ጉዳይም ከዚህ የላቀ አስፈላጊነት ባለው ሁኔታ እውቀት አትኩሮት ይሰጠዋል። በምድራዊ እውቀትና በሰማያዊው መሃል ግን ከፍተኛ ልዩነት ያለበት ነጥብ አለ፣ እርሱም የእውቀት መገኛው/ምንጩ …
Continue reading እውቀተ መለኮት(1…)

የስሜት አግባብነት[1…]

ስሜት ምን? ማንኛውም ከሰውነታችን ውጪ የሆነ ነገር ተጽእኖው ወደ እኛ ሲመጣ የሆነ የሰውነታችን ክፍል መልስ ይሰጣል፤ ይህ የሚሆነው ያየነው፣ የዳሰስነውና የሰማነው ነገር ትኩረታችንን ስለሳበ ሊሆን ይችላል፤ ሁሌም የነካነው፣ የቀመስነው፣ ያየነውና የሰማነው ነገር እንድንንቀሳቀስ ያስወስነናል፦ አንድ ነገር ቢሸተን እንደሽታው ምንነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንገባለን፤ ሰውነታችንንም የነካን ነገር እንዲሁ ለመልስ እንድንንቀሳቀስ ሊያደርገን ይችላል። የማየት፣ የማሽተት፣ የመስማትና የመቅመስ …
Continue reading የስሜት አግባብነት[1…]

ጥርጥር ጠላት(2…)

ጥርጥር የተስፋ ጠላት ነው ተስፋ ነገን መመልከቻ መነጽር ነው፤ ተስፋ የሌለውን ነገር እንዳለና ሩቅ ያለንም አቅርቦ መመልከቻ መነጽር ነው፤ ተስፋ በእግዚአብሄር በመታመን ምክኒያት ያደርገዋል ብለን የምንጠባበቅበት መያዣችን ነው። ተስፋ ይመለከታል፣ ተስፋ በልቦና እጅ በመታገዝ ከሩቅ ያለውን ነገር አቅርቦ ይጨብጣል፣ በዚህ ምክኒያት የእግዚአብሄር ህዝብ በመንፈስ እጁን እየዘረጋ የእግዚአብሄር የሆነውን ሁሉ በእምነት ይጨብጣል፣ በእውን እስከሚያገኝ ከእግዚአብሄር ጋር …
Continue reading ጥርጥር ጠላት(2…)

ጥርጥር ጠላት(1…)

• ጥርጥር የእምነት ጠላት ነው። • ጥርጥር የተስፋ ጠላት ነው። • ጥርጥር የመዳን ጠላት ነው። • ጥርጥር የመጎብኘት ጠላት ነው። • ጥርጥር የሞገስ ጠላት ነው። • ጥርጥር የምህረት ጠላት ነው። • ጥርጥር የጽናት ጠላት ነው። • ጥርጥር የፍቅር ጠላት ነው። • ጥረጥር የሰላም ጠላት ነው። • የሚጠራጠር አያምንም፣ ስለማያምን አይጸናም። • የሚጠራጠር ተስፋ አያደርግም፣ ተስፋ …
Continue reading ጥርጥር ጠላት(1…)

አንተ ግን ያው አንተ ነህ (3…)

ዕብ13:8 ስለ ጌታ ኢየሱስ ማንነት እንዲህ ይላል፡- ”ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።” ጌታ ኢየሱስ ሞቶ አልነበረም ወይ? የሚሉ አሉ፡፡ አዎ ሞቶ ነበር፣ ሞቱ ግን ዘላለማዊነቱ ላይ ምን ተጽእኖ ነበረው? እርሱ ራሱ ስለራሱ ተናግሮአል፡- ”ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ …
Continue reading አንተ ግን ያው አንተ ነህ (3…)

የአይን ነገር(2…)

 አይን፣ ጆሮና ልብ ተቀናጅተውና በበጎ ልቦና ቁጥጥር ስር ሆነው በህይወታችን ቢሰሩ ህሊና ውጤታማ ስለሚሆን የጽድቅ ፍሬ ያሳያል፤ ለምሳሌ አይን በተገቢው መንገድና በተገቢው ስፍራ ተገቢ ነገር እንዲያይ ቢቃኝ ከፈተና ይጋረዳል፤ ጆሮም ከሚፈትን ድምጽ ቢጠነቀቅ ልብን ከክፉ ውሳኔ ይመልሳል፣ ዛሬም ቀድሞም ከሚሰማው ያልተገባ ነገር የተነሳ ልባችን በተሳሳተ ውሳኔ ሲመራ ስለኖረ ብዙ የህይወት ውጣ ውረድ፣ ፈተናና ስብራት በሰው …
Continue reading የአይን ነገር(2…)

የአይን ነገር(1…)

የአይን ነገር የብዙ ነገር ጉዳይ ነው፡- አይንን አስበን ወደ ምንነቱ፣ ወደ አፈጣጠሩ፣ ወደ ግልጋሎቱ እያነጣጠርን ስናጠና የእርሱን አስፈላጊነት የምናጎላበት ምክንያት ተገቢ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ባለአይን/ አይናማ ሰው ይህችን አለም በማየት እውቀት ስለሚኖራት የማየት ችግር ካለባቸው አይነስውራን ይልቅ የእርስዋን ግፊት የመቁዋቁዋም አቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ እንቅፋቶችን አይናማው ሰው መሻገር የሚችላቸው ቢሆንም የእይታ ግርዶሽ ለገጠመው ግን ፈተና …
Continue reading የአይን ነገር(1…)

የህይወት ህያውነት

አዲሱ ህይወታችን በጌታ ኢየሱስ አሰራር የተፈጠረ ለዘላለም የሚኖር ዳግም የተወለደና መንፈሳዊ ነው፡፡: ይህ ህይወታችን በምድር ላይ እንደሚሆነው ሁሉ በመንፈሰዊውም አለም ህያው ሆኖ እንዲቀጥል ያስፈልጋል፡፡ህይወታችን አሁንም ቀጥሎም፣ ዛሬም ነገም ህያው እንዲሆን ከጌታ ከኢያሱስ ጋር ህያው መስመር ሊኖረው ይገባል፡፡ ጌታ በመንፈሱ እለት እለት ሊያጠጣው፣ ሊያለመልመውና ህያው ሊያደርገው ከእርሱ ጋር መጣበቅ የግድ ነው፡፡ ዳግም የተወለደው ሰው በጌታ ህያው …
Continue reading የህይወት ህያውነት

እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜው ይፈጽማል‹2..›

እግዚአብሄር የተናገረውን እንደተናገረው ልክ/ ፍጹም አድርጎ በትውልድ መሃል በጊዜው እንዲገልጠው የተመቻቸ ስፍራ/ማረፍያ ልብ ይፈልጋል፡፡ በአዲስ ኪዳን ሊሆን የተጠበቀው፣ የሆነውም ይህ ነበር፤ ስለዚህ የእግዚአብሄር መልአክ የእግዚአብሄርን ስራ ሊያውጅ ሲገለጥ ወደ ሁለት ቤተሰቦች ዘንድ ሄደ፡- ወደ ካህኑ ዘካርያስና ወደ ማርያም ቤት፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ እልሳቤጥ በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ። ማርያም ለዮሴፍ …
Continue reading እግዚአብሄር የተናገረውን በጊዜው ይፈጽማል‹2..›