በሮሜ.14:1 ላይ ‘’በእምነት የደከመውንም ተቀበሉት፥ በአሳቡም ላይ አትፍረዱ።’’ ባለው መሰረት በእምነት ድካም ሲመጣ በአማኝ ላይ ከሚመጣ የአስተሳሰብ መናጋት ለመታደግ ጥንቃቄ እንዲኖረን ቃሉ ይመክራል። በተለምዶ እንደምናየው ሰው በአሳብ መናጋት ውስጥ ሲገባ ሌሎች ሰዎች በርሱ ላይ እንዲፈርዱ መንገድ ይከፍታል፤ በተለየ ሁኔታ እንዲገምቱት፣ እንዲተቹትና እንዲፈርዱበትም ያደርጋል። ያ የሚያስተች አመለካከት ደግሞ አድሮ የስነ ልቦና መናወጥ ምንጭ መሆኑ አይቀርም፤ በዚህ …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(2…)
Category:የመጨረሻ ዘመን
መንፈሳዊ ድካም(1… )
መዝ.107:11-13 ‘’የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥ ልባቸው በድካም ተዋረደ፤ ታመሙ የሚረዳቸውም አጡ። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ በመከራቸውም አዳናቸው።’’ በእግዚአብሄር ላይ አመጽ የሚሆነው በእግዚአብሄር ምክር ሳንሄድ ስንቀር፣ ተግሳጹን ንቀን ችላ ስንል፣ ማስጠንቀቂያውን ምናምን ስናደርግ ነው። ይህን ባደረግንበት በፈንታው ግን በግልጽ ወይም በስውር የሚመጣ መከራ ያገኘናል፤ በግልጽ በስጋችን ላይ በሚሆን የተለያየ ህመም፣ ደዌ …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(1… )
የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (2…)
የአብረሃም አምላክ የሆነ እግዚአብሄር ብርቱ አምላክ ሲሆን ለሰው ደግሞ ያለው አሳብ በጎ ነው፣ የሰው አሳብ ወደ ጥፋት እየሆነ ባለበት በዚህ ዘመን እንኩዋን በመንገዱ ሁሉ በጎ ነው፣ በሚያደርግልን በስጦታው በጎ ነው፣ በራሳችን አውቀናል እያልን በምርጫዎች ብንሞላም ከኛ ይልቅ የተሻለውን የሚያውቅልን እርሱ ብቻ ነው። በእምነት ማጣት ምክኒያት እግዚአብሄር በገለጠልን እውነት ያለመርጋት ስለሚታይብን እንጂ ከርሱ የምንቀበለው እውነት ትልቅ …
Continue reading የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (2…)
የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)
እግዚአብሄር ያመለከተንን አይተን ባንወደውም፣ ከፊታችን ያኖረውን ትእዛዝ ሰምተን ባንመርጠውም፣ ሃሌሉያ አሰኝቶ ባናመሰግንበትም እርሱ ያዘዘውና የተናገረው ነገር በሙሉ በጎ ውጤት አለው። የእግዚአብሄር ንግግር የተሻለ መንገድ አመልካች ነው፣ የተሻለ ህይወት አለው፣ የተሻለ መጨረሻም አለው። እግዚአብሄር ነገሮች ከመምጣታቸው አስቀድሞ ይናገራልና፣ ሁኔታዎች ከመድረሳቸው አስቀድሞ ስለ እነርሱ ያመለክታልና፣ የድርጊቶቻችንን ውጤት እንድናውቅም ያመለክታልና፦ ስለዚህ እምቢታ ካሳየን ያለማስተዋላችንና ድምጹን ለመቀበል ያለመፍቀዳችን እጅግ …
Continue reading የእግዚአብሄር የተሻለው ነው (1…)
በመጨረሻ የሚሆነው(1..)
በመጨረሻ ዘመን ይሆናል የተባለው እየሆነ፣ ቀረ የሚባለው ጥቂት ሆኖ እያለ የአዳም ልጆች ዘመኑን በጥልቅ ብናየው፣ ብናተኩርበት ተጥቃሚ እንደምንሆን መገንዘብ መልካም ነው፤ ጊዜው ካለፉት ጊዜያቶች ጋር እየተነጻጸረ፣ ሰአቱ ካለፉት ሰአቶች ጋር እየተመዘነ፣ ወቅቱ ከሄዱት ጋር ተመዝኖ ሁኔታው የሚፈቅደውን ሳይሆን እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ መሆን የነበረበትን ብናስተውል መልካም ነው። ዋስትና ያለው ህይወት ያስፈልገናልና፣ አለም ወደ ጥፋት ስትንደረደር አብረን …
Continue reading በመጨረሻ የሚሆነው(1..)
የመመለስ ትርፍ {2…}
በመመለስ ውስጥ ከምናገኛቸው አስፈላጊ ነገሮች መሃል የሚከተሉትም ይገኛሉ፦ መመለስ ወደ ጽድቅ ይመለሳል፦ ‘’እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።’’ (ሃስ. 3:21) የመሸሽ ውጤቱ ብዙ ነው፣ አንዱ ደግሞ ከጽድቅ መውደቅ ነው፣ ጽድቃችን ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ ከእርሱ በሸሸን ሰአት ከሰጠን ጽድቅ እየሸሸንና እየራቅን ሄደን በጨለማ ውስጥ …
Continue reading የመመለስ ትርፍ {2…}
የመመለስ ትርፍ {1..}
መመለስ ከወጡበት፣ ከተዉት፣ ከተሰናበቱት፣ ከተጣሉት፣ ካኮረፉት እንዲሁም ከጣሉት ነገር ሊሆን ይችላል። መመለስ ከወጡበት ነገር ሲሆን ዳግም ወደ ቤት፣ ወደ አገር፣ ወደ ስራ፣ ወደ ልማድ፣ ወደ ካዱት፣ ወደ ረሱት፣ ወደ ጠሉትም ነገር ሁሉ ሊሆን ይችላል። በመመለስ አልፈልግም ብለው ከተዉት ነገር፣ ስራ ወይም ሰው ዳግም የመገናኘት እድል ይፈጥራል። የጠላነው ይሁን የወደድነው በሆነ አጋጣሚ ወይም ተጽእኖ ምክኒያት ትተነው …
Continue reading የመመለስ ትርፍ {1..}
የስሜት አግባብነት[3…]
ግራ በመጋባት ሰበብ ለዘመናት በላያችን የተሰራው በጎ መንፈሳዊ ስራ ይናዳል ግራ በመጋባት ውስጣዊ ስሜታችን ሲናወጥ መቆም ሊያቅተን በሚያደርስ መናወጥ ውስጥ ልንገባ እንችላለን። ግራ መጋባት፣ በተምታታ ሃሳብና ስሜት መያዝ፣ ያለመረጋጋትንም ጭምር ስለሚፈጥር በአንድ መንፈስ መጸለይ እንኩዋን አያስችለንም። በመንፈሳዊ ህይወት መዛባት ምክኒያት ግራ መጋባት ተፈጥሮ የነፍስ ደጋፊ አሳብ ከተምታታ መንፈሳዊ ሆኖ መቆም አይቻልም። በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም …
Continue reading የስሜት አግባብነት[3…]
የስሜት አግባብነት[2…]
መንፈሳዊ ድንዛዜ ስሜትንም ይገድላል/ያደነዝዛል ውስጣችንን የሚያነቃቃ ነገር በሌለበት ሁኔታ ውስጥ የጠለቅ ሲሆን ፍላጎታችን የመቀዝቀዝ ሁኔታ ውስጥ ይሆናል፤ የመንፈስ ብርታት ሁለንተናን እንደሚያንቀሳቅስ ሁሉ ቅዝቃዜም መተሳሰር ያመጣል። በመንፈሳዊ ብርታት ውስጥ ስንገኝ የቃሉ ጥማት ይመጣል፣ የጸሎት መንፈስ ይበረታል፣ ቅድስና ገዢ ይሆናል፣ ህይወትም ይጸናል። መንፈሳዊ ቅዝቃዜ የድንዛዜ መገለጫ ሲሆን የሁሉ ነገር ፍላጎትና ጥማት መዘጋትና የፍላጎት ጥማት መዘጋት በመሆኑ የህይወት …
Continue reading የስሜት አግባብነት[2…]
መልአክ የሚያሳርግ መሰውያ
እግዚአብሄርን የሚጸየፈው መስዋእት አለ፣ እግዚአብሄር የማያውቀው መስዋእትም አለ፣ ደግሞ እግዚአብሄር የሚቀበለው መስዋእት አለ (ይህን መስዋእት መልአክ ራሱ ይዞት ወደ ሰማይ ያርጋልና ታላቅ መስዋእት ነው) “ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ የእግዚአብሔርም መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ፤ ማኑሄና …
Continue reading መልአክ የሚያሳርግ መሰውያ
