ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

ሐ.የጌታን ምርጫ በተመለከተ፡-እነርሱን ብቻ እንድንሰማ ጌታ እንዳዘዘ ማስተዋል ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጅ በሙሉ ለእነርሱ የወንጌል ስብከት ክብር እንዲሰጥ አጥብቆ ወደ እኛ ትእዛዝ ስድዶአል፡፡ ሉቃ10:16 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።”ሲል ተናግሮአል፡፡ ይህን ጥቅስ ካስተዋልን ጌታ ኢየሱስ እኔን የሚሰማ እናንተን ይሰማል አላለም፣ለምን? የጌታ ፍቃዱ በመረጣቸው ሀዋርያት አድሮ መስራት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

የቤተክርስቲያን ጥሪ[true call; true church]

ሀ.ቤተክርስቲያን የበጉ ሙሽራ እንድትሆን ዝግጁ መሆን አለባት፡፡በዚህ ዘመን ያለች ቤተክርስቲያን በተረጋገጠ  የመዳን መንገድ  ውስጥ  መኖር ከፈለገች  እውነተኞች ሀዋርያት የሄዱበትን የእምነት መንገድ መከተል እንጂ ሌላ ከንቱ ትምህርት ውስጥ መስጠም አስፈላጊ እንዳልሆነ ማስተዋልና ልብወለድ ትምህርቶችን (መናፍቃዊ ትምህርቶችን) በብርቱ መቁዋቁዋም አለባት፡፡2ቆሮ.11:2-3 ”በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ  ንጽሕት ድንግል እናንተን  ለክርስቶስ  ላቀርብ  ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን …
Continue reading የቤተክርስቲያን ጥሪ[true call; true church]

ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]

ረ. የሀዋርያቱን የማይለወጥ ወንጌል በተመለከተ፡-ከእነርሱ ሌላ ወንጌልን አሻሽሎ የሚያቀርብ ቢኖር ሰማይ የሚቀበለው ሳይሆን እርግማን እንደሚያስረው ስለምታስተውል ነው፡፡ ሀዋርያቶች በመልእክቶቻቸው ውስጥ አጥብቀው ካነሱት ርእስ መሀል የሀሰት ትምህርት አንዱ ነበር፡፡ከሰውና ከአጋንንት የፈለቀ የሀሰት ትምህርት ከጌታ የተቀበሉትን ትምህርት እንደሚበርዝ አስቀድመው በመንፈስ ስላስተዋሉ አጥብቀው ተቃውመውታል፡፡ ገላ.1:7-8 “እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።ነገር …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,3..]

ቤተክርስቲያን – ማን ናት ?[church of the living God,1..]

ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ባስተማሩት ወንጌል ላይ መሰረትዋን የጣለች የክርስቶስ አካል ነች፡፡ክርስቶስን አምነው በጥምቀት የለበሱት፣ እርሱን በማወቅና በማደግ እስከ ሙላቱ ድረስ በቃሉና በመንፈሱ ለመታነጽ በአንድነት ተያይዘው የሚኖሩባት ማህበር ናት፡፡ይህች ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ከሚገኙት ቤተ እምነቶች በዋናነት የምትለየው ሰው ሁሉ ጌታ የሰጠውንና ሀዋርያት እንደተቀበሉት ያስተማሩትን ትምህርት ብቻ በመቀበልና በማመን መንግስተ ሰማይ እንደሚገባ ማመንዋ ነው፡፡ ኢየሱስ በገዛ …
Continue reading ቤተክርስቲያን – ማን ናት ?[church of the living God,1..]