ኢያሪኮ ፈርሶ እንደቀረ የተደመደመ ጉደይ ሆኖ ሳለ በአእምሮ ውስጥ ትዝታው አልለቅ ካለ የቀደመው ሀጢያት ከልብ ሊርቅ አልቻለም እንደማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ኢያሪኮን ለምን ረገማት? ኢያሪኮ ማለት ከተማዋ፣ አካባቢዋ ወይም የኑሮዋ ስርአት ብቻ ሳይሆን የአምልኮ ልማድዋን ተከትሎ የተፈጠረው ያልተገባ የህይወት አኑዋኑዋር ሁሉ ማለት ነው፡፡ ኢያሪኮ የአህዛብ ከተማ በመሆንዋ የአህዛብ ልማዶችን የተሞላች ስለመሆንዋ አያጠራጥርም፡፡ ልማዶችዋ እግዚአብሄርን የሚያስደስቱ አልነበሩም፡፡ …
Continue reading ኢያሪኮን መስራት? (2..)
Category:ቤተክርስቲያን
ኢያሪኮን መስራት? (1..)
• ኢያሪኮ ይፍረስ በሙሴ ዘመን የኢያሪኮ ከተማ የእግዚአብሄር ፈቃድ የሌለባት ስፍራና የአመጸኛ ህዝብ ምልክት የነበረች ነች፡፡ የአመጽ ልማድ የነገሰባት፣ ጣኦት የሚገዛባት፣ ስርአት የሌለባትና እግዚአብሄር የማይፈራባት ስፍራ ስለነበረች በርሱዋ ውስጥ የእግዚአብሄር ፈቃድ መገለጥ አይችልም ነበር፤ የከተማዋ ህዝብ እግዚአብሄርን ሳይሆን ጣኦትን የሚከተልና የሚያመልክም ነበር፡፡ ስለዚህ በርስዋ ያለ ምድር ከጣኦት የተነሳ የረከሰ ፣ ህዝቦችዋ ከእግዚአብሄር ጋር ሳይሆን ከአጋንንት …
Continue reading ኢያሪኮን መስራት? (1..)
እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
የጌታ ደቀመዛሙርት ቅድሚያ ሊሰጡዋቸው ከሚገቡ ነገሮች ፊት የሚገኘው (አውራና መሰረት የሆነው) የመንፈሳዊ ህይወት ጤንነት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወት እንደ ስጋ ያለ ቁመና፣ ፍላጎት ወይም ስሜት ስለማይኖረው የጤንነቱ መለኪያ በስጋ ከሚደረገው ጋር አይመሳሰልምና የተለየ መፍትሄ የሚሻ ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወታችንን የሚመረምርና የሚያክም የእግዚአብሄር መሳሪያ የሆነው ህያው ቃሉ ነው፡፡ ቃሉ ስለሚሰራው ስራ መጽሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ”የእግዚአብሔር …
Continue reading እየጠየቁ ያለመቀበል{3..}
እየጠየቁ ያለመቀበል{1..}
መዝ.4:2-8 ”እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባችሁን ታከብዳላችሁ? እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል። ተቈጡ፥ ነገር ግን ኃጢአትን አታድርጉ፤ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፤ ዝም በሉ። የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በእግዚአብሔርም ታመኑ። በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። አቤቱ፥ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ። በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ …
Continue reading እየጠየቁ ያለመቀበል{1..}
ሁሉን ትተን ተከተልን [2…]
እግዚአብሄር በፍቅሩ የጠራቸው ሰዎች የጠራቸውን አምላክ ታዝዘው በመውጣት ፈቃዱን ሲከተሉና ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ ጥሪውን ሰምተው ለመውጣት የፈቀዱ እነዚህ ታማኝ ሰዎች ታሪካቸው ለትምህርታችን እንዲነገር በቃሉ ውስጥ ተጠቅሰዋል፡፡ የጥቂቶችን ታሪክ አስቀድመን ያየን ሲሆን ከዚህ በመቀጠል ተጨማሪ ሰዎችን እናያለን፡- • አብረሃም ወገንና ቤተሰቦቹን ትቶ ወጥቶ ነበር አብረሃም እግዚአብሄር ወደ ነገረው ስፍራ ሲወጣ ሁሉን ነገር ትቶ በመከተል ነበር፡፡ ያኔ አብረሃምን …
Continue reading ሁሉን ትተን ተከተልን [2…]
ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]
በጎውን፣ መልካሙንና የተሸለውን የጌታ ምህረት ለማግኘት የአለምን ፍቅር፣ የስጋን ምኞትና ሰይጣናዊ ልምምድን መተው፣ መሸሽና መጸየፍ ግድ ይላል፡፡ አመጽን ማቆም፣ ከክፉዎች መለየት፣ ወደተውነው ክፉ ልማድ ዳግም ያለመመለስ ውሳኔን በራስ ላይ ማሳለፍ አስፈላጊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከተከለን ስፍራ ያለመልቀቅ፣ ከክፋት መራቅ፣ የራስን ለርሱ አሳልፎ መስጠትና የጌታን ፈቃድ መከተል የፈለግነውን የጌታ ምህረት እንድንቀበል ያግዘናል፡፡ ጌታን መከተል፣ ቃሉን በፈቃደኝነት መቀበል፣ …
Continue reading ሁሉን ትተን ተከተልን [1…]
ራሳችሁን አትስሙ[4…]
ማምለጥ የምትፈልጉ የእግዚአብሄር ህዝብ! • የሚሰማኝ ትክክል ነው በሚል እርግጠኛ ሆናችሁ ለስሜታችሁ እጅ አትስጡ/ ሙሉ በሙሉ አትቀበሉ፡፡ በውሎአችሁ ውስጥ ስሜታችሁ ወዴት ይመላለስ ኖሮአል? የተነካችሁበት ሁኔታ እንደማይገዛችሁ እርግጠኛ ናችሁ? ወይስ የአሳባችሁ ክልል በማን ሲጎበኝ ነበር (በአለም፣ በስጋ፣ በተለያየ መንፈስም ሊሆን ይችላል)፣ ምንስ ሲይዝና ሲጨብጥ፣ የቱንስ መንፈስ ሲያስተናግድ ዋለ? • ውስጣችሁ የሚመላለሰውን ድምጽ በጥድፊያ አሜን አትበሉት፣ በተለያየ …
Continue reading ራሳችሁን አትስሙ[4…]
ምንስ ልስማ?[3…]
ብዙ የሚሰሙ ድምጾች በተለያየ አይነት መንገድ ከተለያየ ምንጭ ፈልቀው ወደ እኛ ይደርሳሉ፡፡ ቢሆንም ከሁሎቹም ድምጾች በተለየ የእግዚአብሄርን ድምጽ ቦታና ትኩረት ልንሰጥ የሚገባው ነው፡፡ ለዚህ ውሳኔ ዋናው ምክኒያት የሚሆነው የድምጹ ባህሪ ከሌሎቹ የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ድምጽ ከሌሎች ድምጾች የሚለይበት ዋና ባህሪያት አሉ፡- የእግዚአብሄር ድምጽ ማንኛውንም ድምጽ ይልቃል፣ ይሽራል፣ ያነሳል ያጠፋልም፤ ምክኒያቱም ድምጹ የፈጣሪ ድምጽ በመሆኑ፡፡ …
Continue reading ምንስ ልስማ?[3…]
ለማን ብዬ ልስማ?[2…]
ለማን ብዬ ልስማ – ለማን ብዬ ልሰማ ነው፣ ለራሴ ስል ካልሆነ፡፡የሚያጠፋኝ ብዙ ብዙ ነገር በአለም ውስጥ ስላለ እራሴን ለማዳን ስል ለራሴ ብዬ ቃሉን ልሰማ ተገቢ ነው፤ አለፍ ሲል ደግሞ ሌሎችን አድን ዘንድም ስለሚባለው ነገር ተጠንቅቄ ልሰማ ተገቢ ነው፣ ጠንቅቆ ያለመስማት ሰሚውንም አድማጩንም እኩል የሚያጠፋበት ጊዜ ስላለ ማለት ነው፡፡ በአለም ውስጥ የሚሰሙት እጅግ የበዙ፣ የተወሳሰቡና ሊያጠፉ …
Continue reading ለማን ብዬ ልስማ?[2…]
የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]
ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ በተባለበት አለም ውስጥ ስኖር ምን መስማት እንዳለብኝና እንደሌለብኝ ማስተዋል የለብኝምን? ለመንፈሳዊ ህይወቴ እንድጠነቀቅ የሚያሳስበኝ አምላክ የድምጾችን ምንጭና አቅጣጫ እንዲሁም ይዘትና ተጽእኖ ስለሚያውቅ ለእኔ ደካማ ሰው ጥንቃቄ ሲል ይህን ማሳሰቢያ አስተላልፎአልና፡፡ አለማችን ውስጥ የተለያየ መንፈስ ያላቸው ድምጾች ቢያንስ ቢያንስ በየሰከንዱ ይፈጠራሉ፤ ሰው ጆሮ የሚደርሱ፣ ተጽእኖ ያላቸውና የሰውን አስተሳሰብ ሊጫኑ የሚችሉ ድምጾችን እንደሰማሁ በግርድፉ …
Continue reading የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ[1…]
