ለኛ የታሰበልን

በእግዚአብሄር ፈቃድ አካባቢ ያለውን የፍጥረት ስፍራ ሰው ማስተዋል ቢችል የምድር ፊት ዛሬ ላይ ምን ሊመስል ይችል ነበር? ሌላው ቀርቶ ሰው የታሰበለትን ቢረዳ፣ እግዚአብሄር ሲጣራ ቢሰማ፣ ለራሱ አሳብ ሳይሆን ለሰሪው ድምጽ ጆሮውን ቢያዘነብል የሰው ልጅ እንዴት ባለ ሰላምና ደስታ ይኖር ነበር? አለም መልኩዋም አሳቡዋም ምንም ቢያባብል በመጎተቻዋ ተጠልፈው እጅ ያልሰጡ ያተረፉት ነገር ብዙ ነው፤ በዚህ ሳያበቃ …
Continue reading ለኛ የታሰበልን

የምስራች ለሁሉ

ማር.1:1-4 “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፦ እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።” መጽሃፍ እንደሚል ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ በሰጠው የእግዚአብሔር ወንጌል አስቀድሞ ከጠራቸው ሐዋርያ አልፎ …
Continue reading የምስራች ለሁሉ

ጊዜ ጌታ? [3..]

– ጊዜ ፈራጁ? ጊዜ ፈራጅ ነው አንበል፣ ፈራጅስ ጌታ ነው፦ መዝ.50:5-6 ”ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።” የወቅትን ፈራጅነት ለማሳየት ጊዜ በሰው ላይ እንደሚሰለጥንም ለማመልከት ሰዎች በልማድ ያን ይሉታል፡፡ ግን እግዚአብሄር በጊዜያቱ ለሚሆኑት ነገሮች ባለቤት ከሆነ ጊዜ በነገሮቹ ላይ ስልጣን ሊኖረው አይችልም፤ ጊዜ ራሱ ጌታ ካለው የገዢነት ቦታ …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [3..]

ጊዜ ጌታ? [2..]

– ጊዜ ጌታ? የቀን ምንነት ለሚያሳስበውና ለሚመረምረው አንድ የሚታየው ጉልህ እውነት የነገው እለት ከዛሬው ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው፤ ቀን ቀለም የለው የትኛውም እለት አይወዳደርበትም፣ አንዱ ከሌላው ከፍና ዝቅ አይል እግዚአብሄር እኩል አድርጎና ወስኖ ፈጥሮታል፣ ሰው በእርሱ ላይ ተጽእኖ የለውም ስለዚህ እንደተፈለገው ሊዘወር አይቻልም… ሰለዚህ የትላንትናው ቀን የነበረው ሰአት ዛሬም አለው፣ ነገም ከነገ ወዲያም እንዲሁ፤ ዋናው …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [2..]

ጊዜ ጌታ? [1..]

  የሁሉ አምላክ እግዚአብሄር ስለእኛ ሲል ጊዜን ፈጥሮአል (ዘፍ.1.14-17)፡- ”እግዚአብሔርም አለ፡- ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፤ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ …
Continue reading ጊዜ ጌታ? [1..]

ለመመለስ መንቃት

የአምነት ጉዞንና የባህር ጉዞን የሚያመሳስሉ ሰዎች አሉ፤ ምክኒያታቸውን ሲያስረዱ አንድ ሰው የእምነት ጉዞን ሲጉዋዝ  አገኛለሁ ብሎ የሚጠብቀውን መንፈሳዊ ነገር ተስፋ አድርጎ እንጂ በእጁ ጨብጦ የሚጉዋዝ አለመሆኑ፣ በባህር ላይ የሚደረግ ጉዞም የሚታይ ነገር ከፊት ሳይኖር በእምነት ብቻ መዳረሻን አልሞ ወደተገመተ አቅጣጫ የሚቀዝፍበት መሆኑ ነው፤ ባህርተኛው በእምነት ከሆነ ጊዜ በሁዋላ እደርሳለሁ ወዳለው ሩቅ ስፍራ እንደሚደርስ በማሰብ የሚጉዋዝም …
Continue reading ለመመለስ መንቃት

የማንበቃበትን እክል መሻር

የማንበቃበት ነገር፡- በእግዚአብሄር መገኛ አካባቢ ይዘን የምንመላለሰው ነገርና አካሄዳችን በማንነታችን የሚደነቃቀፍ ሲሆን፣ የምንመራበት የህይወት መርህ ደካማ ሆኖ ያለን የህይወት ይዘት የማይበቃ ሆኖ ሲቆጠር፣ የእግዚአብሄር ቃል የሚቃወመው የህይወት ይዘት ሲኖረን፣ መርሀችን የተተወ/መታሰቢያ የማይገኝለት መርህ ከሆነ ያም ከአለም ልማድ እንዳንወጣ ካነቀን፣ ከመንፈሳዊ የህይወት ደረጃ የተጣለ/በአለም ብቻ ተቀባይነት ያለው ቃሉ ግን የሚኮንነው ልማድ ካለን፣ የተወገደ/በእኛ ቁጥጥር ስር የሌለ …
Continue reading የማንበቃበትን እክል መሻር

ወድጃችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር

ወድጃችሁዋለሁ የሚል የአምላክ ድምጽ እንዴት ያለ እረፍት፣ እንዴት ያለ ደስታ፣ እንዴት ያለ ሰላም የሚፈጥር መተማመኛ ቃል ነው? እንኩዋን የአምላክ ድምጽ የምንደገፈው ሰው እንኩዋን ይህን ቃል ቢያሰማን ልባችንን ያሞቀዋል፡፡ እግዚአብሄር የጠራውን ህዝብ ሊያጸናና በጉዞው መሀል ሊያበረታው እንዲህ ያለ ቃሉን ይልካል፡፡ አብራምን ስንመለከት እርሱ ተስፋ ቆርጦ ሳለ ቃሉ በዘፍ.15:1-6 ሲመጣለት እናያለን፡- ”ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ …
Continue reading ወድጃችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር

ስለ መስቀሉ ቃል ‹2..›

የመስቀሉ ቃል የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መቀበልና በሀይል ከሞት መነሳት የሚሰብክ የወንጌል ክፍል ነው፡፡ በዕብ.9:28 እንደተጻፈው፡- ”እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።” ይላል፡፡ የሚበላ የህይወት እንጀራ ክርስቶስ ህያው በሆነው ስጋውና ደሙ ሊቀድሰንና ህይወትን ሊሰጠን ተገልጦአል፡፡ ወንጌልን አስደሳች የሚያደርገው በእርሱ መከራ የእኛ ደህንነት በመረጋገጡ፣ …
Continue reading ስለ መስቀሉ ቃል ‹2..›

ስለ መስቀሉ ቃል ‹1..›

የእግዚአብሄር ቃል ስለ መስቀሉ ቃል በ1ቆሮ.1:18 ላይ እንዲህ ይላል፡- ”የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” በመስቀሉ ቃል እውቀት ላይ የሚቀርቡ አሳቦች ወይም የሚንጸባረቁ አቁዋሞች የአማኝን የእምነት ይዘት ይወስናሉ፣ ያም ብቻ አይደለም የዘላለም አድራሻውን ጭምር ይወስናሉ፡፡ ለሚያምኑት ቃሉ የእግዚአብሔር ኃይል ሲሆን ለማያምኑት ሞኝነት (ከንቱና የማይረባ አሳብ ብቻ) ይሆንባቸዋል፡፡ ሰዎች ከንቱና የማይረባ ብለው …
Continue reading ስለ መስቀሉ ቃል ‹1..›