እግዚአብሄር ሁሉን የፈጠረው ነገሩ ከሚኖርበት ጊዜና ስፍራ አንጻር ነው፣ ስለዚህ ምንም በርሱ የተፈጠረ ነገር ይኑር እንደተጀመረ ሁሉ እርሱ ባለው ጊዜና በወሰነው ስፍራ ይፈጸማል፣ እርሱ በፈቀደው ስፍራ ይኖራል ያበቃልም ፣ ይህ የማይሻር እውነት አማኞች ሊጠብቁት የተገባ ነው፦ ‘’ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም …
Continue reading ያለጊዜው አትፍረዱ(1… )
Category:ቤተክርስቲያን
አለማዊነት(3..)
ስለ አለም ማወቅ ያለብንን ነገር ከመሰረቱ አንስቶ በሙሉ እውቀትና ማስረጃ ገልጦ የሚያሳውቀን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ብቻ ነው፤ የሚከተለው ቃል ታላቅ ነገር ይናገራል? ‘’ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።’’ (እብ. 11:3 ) ቃሉ ከአንድ በላይ ብዛት ያላቸው ዓለሞች እንዳሉ በማስረዳት እነርሱም በእግዚአብሄር ቃል እንደተዘጋጁ ያሳያል። እነዚህ አለማት የሚታዩ ፍጥረታት ሲሆኑ …
Continue reading አለማዊነት(3..)
አለማዊነት(2..)
በዳኑ ሰዎች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች በብዙ አቅጣጫ የሚታዩ ሲሆን ተግዳሮቶቹም በዋናነት ለመንፈሳዊ ህይወት ችግሮች ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ነፍሳት በጌታ ኢየሱስ ቤዛነት ብቻ ከጥፋት በመዳን ህያዋን ሲሆኑ ቤዛነትን በሰጣቸው ጌታ ታምነው መኖር እንዲገባቸው የዳኑበት መሰረት ያሳያል። ሰዎች ንስሐ ስንገባ፣ ኃጢአታችንን ስንተው፣ ክርስቶስን በልባችን ስንቀበልና በዳግም ልደት ከውሃና ከመንፈስ ስንወለድ በእውነት ድነናል፤ አሁንም ግን በህይወት ዘመናችን ስንኖር …
Continue reading አለማዊነት(2..)
አለማዊነት(1..)
እግዚአብሄር ሲመለከት አለማዊነትን ከሃጢያት አለያይቶ አይደለም፤ ያም ሆኖ ቤተክርስቲያን አለማውያንን ለማዳን ስትል በርዋን አስፍታ ከፍታ በርህራሄ እንድትቀበላቸው እግዚአብሄር ፈቅዶአል። ነገር ግን ቤተክርስቲያን ነፍስን ለማዳን ባቀደችው አካሄድ ውስጥ ልትጠነቀቅና አለማዊነት እንዳያጠምዳትና እንዳይረባባትም በመጠባበቅ ተልእኮዋን ልትፈጽም ተገቢ ነው፤ ሰይጣን ሾልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ አለማዊነትን ይዞ ስለሚገባ መንፈሳዊ ህይወትን በመበረዝ ቤተክርስቲያንን ያዳክማል። አለማዊነት የተቆጣጠራቸው አማኞች ሲበዙ ጽድቅ ጥያቄ …
Continue reading አለማዊነት(1..)
ቃለ መለኮት(4…)
ህያው የእግዚአብሄር ቃል ህይወትን ይሰጣል፣ ያም ብቻ አይደለም መንፈስን ያነቃል፣ ሃይልን ያጎናጽፋል። ‘’ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።’’ (ዘዳ. 8:3) የእግዚአብሄርን ቃል ድምጽ የሚያከብሩ ቅዱሳን አትኩሮታቸው ዘመናትን የሚሻገረው ግን የማይሻረው ህያው ቃሉ ላይ ነው። ሆኖም ብዙ ትውልድ …
Continue reading ቃለ መለኮት(4…)
ቃለ መለኮት(3…)
የህያው እግዚአብሄር ቅዱስ ቃል አመጸኛና ታዛዥ ላልሆኑ ሰዎች የትኩረት አቅጣጫ የተነፈገው፣ ቀዝቃዛ ስሜት በሚታይባቸው ቸልተኞች ተሸፍኖ ያለ፣ አሳቢነቱ ዝቅተኛና ትርጉሙ በማይሰማው ኢ-አማኝ አእምሮ ውስጥ ከንቱ የሚመስል ወይም ለፍጥረት ብዙም ፍላጎትና ጉጉት የማይፈጥርና የማይስብ ጉዳይ የሚመስል ነው። አለምም በማየት፣ በመዳሰስና በቀመር ስለምታምን በነዚህ ስጋዊ መታመኛ መሳሪያዎች የምትደገፍ ናት። እግዚአብሄር ግን ስለቃሉ በመናገር ያሳስባል፦ ‘’እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ …
Continue reading ቃለ መለኮት(3…)
ቃለ መለኮት(2…)
የህያው አምላክን ቃል የሚያስተውሉ አጥብቀው በቃሉ ይደገፋሉ፤ በቃሉ ላይ መዛነፍ እንደሌለ ማመናቸው ህያውነቱን አምነው እንዲቀበሉም ይረዳቸዋል። ‘’እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።’’ (ኢሳ. 45:22-23) ቃሉን ለኛ በምናስተውለው መንገድ እንደንሰማው …
Continue reading ቃለ መለኮት(2…)
ቃለ መለኮት(1…)
ቃለ-መለኮት ወይም የመለኮት ቃል የእግዚአብሄር ድምጽ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር ድምጹን ከራሱ አውጥቶ የሚናገር አምላክ ሲሆን ማስተላለፊያ መንገዱ ግን የተለያየ ነው፦ እግዚአብሄር በቀጥታ ድምጹን ለሰዎች ያሰማል፣ አሰምቶአልም፤ ድምጹን በመላእክት አንደበት ያስተላልፋል፣ አስተላልፎአልም፤ እንዲሁም የነቢያትን አንደበት ተጠቅሞ ወደ ህዝቡ ድምጹን ሲያሰማ ኖሮአል፣ አሁንም ያን ያደርጋል። ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ቃል ቀጥሎ እንመለከታለን፦ ‘’ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ …
Continue reading ቃለ መለኮት(1…)
ልክ ለልከኝነት(2…)
ልክ የመጠን ዳርቻ እንደመሆኑ ነገሮች ከልክ እንዳያልፉብን ብንጠነቀቅ ልክ ነን። የኛ የሆኑ ነገሮቻችንና የሌሎችም ነገሮች ጨምሮ ከልካቸው መስመር እንዳያልፉ እንደሚያሳስብ ቀጥሎም ማየት እንችላለን፤ በእርግጥ እነርሱን ማወቅ ለሚዛናዊ ህይወት ይጠቅማል፦ • የቅጣት ልክ 2ቆሮ.2:5-7 “ነገር ግን ማንም አሳዝኖ ቢሆን፥ እንዳልከብድባችሁ፥ በክፍል ሁላችሁን እንጂ እኔን ያሳዘነ አይደለም። እንደዚህ ላለ ሰው ይህ ከእናንተ የምትበዙት የቀጣችሁት ቅጣት ይበቃዋልና እንደዚህ …
Continue reading ልክ ለልከኝነት(2…)
ልክ ለልከኝነት(1…)
የህይወታችን መሰርት ጌታ ኢየሱስ ነው፣ ደግሞም የመንፈሳዊ ህይወታችን እድገት ልክም ነው፤ ወደዚያ ልክ ለመድረስ ሁሌም እየተሰራን እስከ ፍጻሜ እንጓዋዛለን። ወደ እርሱ ሙላት እንዘረጋለን እንጂ ሙላቱን የሚፈጽመው እርሱ ራሱ ነው። የጀርባ ታሪካችን የሚያውቅ፣ ልካችንና መድረሻችን የሚያይ አምላክ ትክክለኛው ደረጃ እስክንደርስ በመንፈሱ እየሰራ በጸጋው እየደገፈና እያስተካከለ ያኖረናል። የቃሉ ውሃ-ልክ የእኛን መንፈሳዊ ሚዛን የሚያስተካክልና ወደ ልኩ የሚወስድ ብቸኛው …
Continue reading ልክ ለልከኝነት(1…)
