እግዚአብሄር በምህረት በሚጎበኝበት ቀን (ዘመን) ትውልድ ተዘጋጅቶ ይጠብቅ ዘንድ ይፈለጋል፤ እግዚአብሄር መቼ ይሰራል? ለማን ይሰራል? እንዴት ይሰራል? የሚል ማስተዋል ያለበት ምርመራ ይገባልም። በእስራኤላውያን ዘንድ ዘመንን ማወቅ ትልቅ ስፍራ ስላለው ጠቢባን ያማክሩ ነበር፤ በንጉስ ዳዊት ዘመን ጊዜን የሚመረምሩና የሚያስተውሉ ከህዝቡ መሃል የተመረጡ ሰዎች ስለነበሩት የእግዚአብሄር ህዝብ ዘመኑንና በዘመኑ ላይ የሚገለጠውን የእግዚአብሄር ፈቃድ በመረዳት የህይወት ይዘታቸውን ያስተካክሉ/ይቃኙ …
Continue reading በሚሠራበት ቀን (2…)
Category:ቤተክርስቲያን
በሚሠራበት ቀን (1…)
እግዚአብሄር ወደ ሰው ልጆች ሲመለከት አብረሃምን አየና ከቤተሰቡ መሃል ለይቶ ጠራው፣ ለምን? እግዚአብሄር የአብረሃምን ማንነት ስላወቀ፣ መጀመሪያ ላይ መጨረሻውን ስላየ፣ የአህዛብ ወራሽ መሆን እንደሚችል መንፈሱን ስለመዘነና የእርሱን መለኮታዊ አሳብ መጠበቅና መፈጸም የሚችል ሰው እርሱ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ እንዲሁም የሰው ልጆች የእምነት አባት መሆን የሚችል እርሱ መሆኑን ስለወሰነ ነው። ያኔ በጥንት ዘመን በእግዚአብሄር ጊዜ ውስጥ የእግዚአብሄርን አላማ …
Continue reading በሚሠራበት ቀን (1…)
የወንጌሉ መሰረት (2…)
በኤፌ2:20፣3፡16 ላይ ቃሉ ሲናገር፦ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ …በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥… ይላል፡፡ ሀዋርያትና ነብያት መሰረት የሆኑት እውነተኛ የወንጌል አገልጋይ በመሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ኢየሱስ ክርስቶስ በእነርሱ አድሮ ለሚሰራው ስራ …
Continue reading የወንጌሉ መሰረት (2…)
የወንጌሉ መሰረት (1…)
የወንጌሉ መሰረት ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡ወንጌል የጌታን የማዳን ስራ የሚገልጥ መለኮታዊ አዋጅ ነው፤ ወንጌሉ የምስራች ሲሆን የወንጌል መነሻም መዳረሻም እሱ ሆኖ ለሰው ልጆች የማይነቃነቅና የጸና መሰረት በመሆን አስተማማኝነቱን አረጋግጦልናል፡፡ የአዲስ ኪዳን መሰረት የክርስቶስ የመስቀል ስራ ውጤት ስለሆነ ሰዎች ያን አውቀው በእምነት ይድኑ ዘንድ ለአለም ሊታወጅ የተገባው የጌታ አዋጅ ሆኖአል፤ ወንጌል የሰላም አዋጅ ስለሆነም እርሱ ተሰብኮ ሰዎች …
Continue reading የወንጌሉ መሰረት (1…)
እምነት፣ተስፋና ድርጊት(3…)
ስለ እግዚአብሄር ቃል ምንነት ባለን እውቀት በኩል የተቀበልነው ትልቅ ስጦታ ቢኖር ተስፋው ነው፤ በተስፋው በኩል እግዚአብሄር በዚህ ጊዜና በዚህ ስፍራ ይህን አደርጋለሁ ብሎ ለሰዎች ቃል ይገባል። ቃሉ በዘመን ብዛት አይለወጥ፣ አያረጅ፣ አይቀየር፣አይታጠፍ ወይም አይጠፋም። ስለዚህ ይህ የእግዚአብሄር ተስፋ ጸንቶ እንደተነገረበት አውድ ትውልዶችን አልፎና አሳልፎ እስኪከናወን ያለመለወጥ ሲጸና ይታያል። አንዳንድ የእግዚብሄር ባሪያዎች የተቀበሉት የተስፋ ቃል ከነርሱ …
Continue reading እምነት፣ተስፋና ድርጊት(3…)
ስለእርሱ ያልኩት ይህ ነበር (ዮሐ.1:15) – 2…
በቀደመው ክፍል እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ በሚለው የምስራች ቃል ውስጥ ከሚገኙ ትኩረታችንን ከሚስቡ ነገሮች መሃል መድሃኒት፣ ስምና ጽንስ እንደሚገኙ (የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው ስለሚል) እነዚህ ሶስት ነገሮችም ሰማያዊ ምንጭ እንዳላቸው አይተናል፤ በተለይ መድሃኒትን በተመለከተ እግዚአብሄር በነቢያት በኩል አስቀድሞ እንደተናገረ እንዲያውም እርሱ ራሱ መድሃኒት ሊሆን እንደወሰነ ከቃሉ አይተናል። በእግዚአብሄር አሰራር የተገለጠ መድሃኒት ስጋና …
Continue reading ስለእርሱ ያልኩት ይህ ነበር (ዮሐ.1:15) – 2…
ስለእርሱ ያልኩት ይህ ነበር (ዮሐ.1:15) – 1…
ስለእርሱ ያልኩት ይህ ነበር (ዮሐ.1:15) – 1… ስለመድሃኒታችንና ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃሉ ምን ይላል? እርሱ ማን መሆኑን ለምንጠይቅ የእግዚአብሄር ቃል መልስ አለው። ቃሉ በዮሐ.1:30 እንደሚል፦ ‘’አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ ከእኔም በፊት ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።’’ ይላል፤ ስለዚህ ቃሉ ዛሬም ስለርሱ የሚለው አለውና ከርሱ እንስማ። – እርሱ ሕዝቡን …
Continue reading ስለእርሱ ያልኩት ይህ ነበር (ዮሐ.1:15) – 1…
ተስፋው ብርቱ ነው(2…)
የእግዚአብሄር ቃል በዕብ.11:3 ላይ ሲናገር፦ ‘’ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።’’ ይላል። የማይታይ አምላክ እግዚአብሄር በማይታይ ቃሉ የሚታዩ ነገሮችን ፈጥሮአል፤ ይህ በእምነት የምንቀበለው እውነት ነው፤ ይህ የማይታይ አምላክ የማይታይ እቅድ፣ አሳብ፣ ፈቃድና ትእዛዝ ሁልጊዜ አለው፤ ስለዚህ ከዚያ ውስጥ የሚወጣ አካል የሚሆን እቅድ በእግዚአብሄር ዘንድ አለ ብሎ ማመን ከሰው ይጠበቃል …
Continue reading ተስፋው ብርቱ ነው(2…)
ተስፋው ብርቱ ነው(1…)
የእግዚብሄር ተስፋ በእግዚአብሄር ላይ ላለን እምነት የጀርባ አጥንትና መሰረት ነው። እግዚአብሄርን የሚያምኑ እርሱን ተስፋ አድርገው ይጠብቃሉ፤ ተስፋ በሌለበት እምነት የለምና። ቃሉ የሚነግረን እንዲህ በማለት ነው፦ እብ.11:1-3 ‘’እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና። ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።’’ ተስፋ በማይታይ ግን ሊሆን ባለው …
Continue reading ተስፋው ብርቱ ነው(1…)
ያለጊዜው አትፍረዱ(2… )
ያለጊዜው ፍርድ ለምን? ‘’በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።’’ (1ቆሮ.4:5) ያለጊዜው ፍርድ አንድም ፈራጅ ሳይሆኑ በፍርድ ወንበር መሰየም ነው፣ ደግሞም የፍርድ ሰአት ሳይሆን ፈጥኖ ፍርድ ማኖር ነው። እውነታ ደግሞ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፍርድ የሚወጣበት ትክክለኛው ጊዜ ሳይደርስ በፊት ድምዳሜ …
Continue reading ያለጊዜው አትፍረዱ(2… )
